እነ ጉርሜሳ አያና ብይን ለመስማት ለ6ኛ ጊዜ ተቀጠሩ

እነ ጉርሜሳ አያና ብይን ለመስማት ለ6ኛ ጊዜ ተቀጠሩ

/Ethiopia Nege News/፦ እነ ጉርሜሳ አያና ለግንቦት 30/2009 ተቀጥረው የነበረው አቃቢ ህግ ባቀረበው የሰው፣ የሰነድና የድምፅ ማስረጃዎችን መርምሮ ብይን “ለመስጠት”  የነበረ ቢሆንም የፌ/ከፍተኛ ፍ/ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት አሁንም በአቃቤ ህግና በተከሳሾች መካከል እርስ በእርስ ከ4 እስከ 5 ቀናት የሚሆን የቃል ክርክር ስለሚያስፈልግ በማለት ለ6ኛ ጊዜ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

አቃቤ ህግ “በእግሊዝኛና ኦሮምኛ” ቋንቋዎች ያቀረባቸውን የሰነድ ማስረጃዎች ወደ አማርኛ ተተርጉመው እንቀርቡ ፍ/ቤቱ ኢቢሲን ባዘዘው መሰረት ዛሬ ተሟልተው መቅረባቸውን ፍ/ቤቱ አረጋግጧል። ተከሳሾች በበኩላቸው የፍርድ ሂደቱን በጽኑ ተቃውመዋል።በዛሬው ችሎትም የሚከተለውን አቤቱታ አሰምተዋል።

አቶ በቀለ ገርባን (የኦፌኮ ም/ሊ/መንበር)  ጨምሮ በእነ ጉርሜሳ  አያኖ  መዝገብ “በሽብር ወንጀል”  የተከሰሱት 22 ሰዎች ፍ/ቤቱ  ሆን ብሎ  ሒደቱን እያጓተተብን  ነው በማለት  አማረዋል። ከተከሳሾቹ መካከል  አቶ አዲሱ ቡላላ ለፍርድ ቤቱ “መጉላላቱ አግባብነት የለውም፤ ከእናንተ ጀርባ የደኅንነት እጅ እንዳለ ይገባናል። እያከናወናችሁት ባለው ተግባር  እናንተንም አገራችንንም እንድንጠላ እያደረጋችሁን  ነው” ሲል ለፍ/ቤቱ ተናግሯል።  ፍ/ቤቱም ከስራ ሰዓት ውጭ ጭምር እየሰራ እንደሆነ በመግለጽ ለሰኔ 9/2009ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።    /Ethiopia Nege  8, 2017/

LEAVE A REPLY