የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ አስከሬን መነሳትን ተከትሎ የተፈጠረውን ውዥብር ለማጥራት፦

የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ አስከሬን መነሳትን ተከትሎ የተፈጠረውን ውዥብር ለማጥራት፦

በባለወልድ ቤተክርስቲያን ቅጥር- ግቢ ውስጥ የሚገኘው የሠብአዊ መብቶች ተከራካሪና የህክምና ሳይንስ ጠበብቱን የፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ሐውልት መፍረሱን ተከትሎ ባሳለፍነው ሳምንት አንዳንድ የመገናኛ ተቋማት የፕሮፌሰሩ ሐውልት ባልታወቀ ምክንያት በሌሊት መፍረሱን በመዘገባቸው፤ የበርካታ ኢትዮጵያዊያን ቁጣ መቀስቀሱ ይታወቃል። እኛም ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ግለሰቦችንና የፓርቲ መሪዎችን አነጋግረናል።

የባለወልድ ቤተክርቲያን ሀላፊዎች ቤተክርስቲያኗን ለማደስና ለማስፋት ባላቸው እቅድ መሰረት ፕ/ር አስራት አስከሬን ያረፈበትን ቦታ ጨምሮ ሌሎች ሀውልቶችም እንዲነሱ በመወሰኑ ምክንያት የፕሮፌሰር አስራት አፅም ወደ ሥላሴ ካቴድራል በክብር ለማዘዋወር አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን አነዚሁ ምንጮች ገልጸውልናል።

ከመኢአድ፣መአህድ፣ሰማያዊ ፓርቲና ከቤተሰብ የተውጣጣ 9 አባላት ያሉት ከሚቴ የተዋቀረ ሲሆን አስፈላጊው ክፍያም በቤተሰብ በኩል እንደተፈፀመ ታውቋል።

ሐውልት የማፍረሱንና ዓፅም የማውጣቱ ስራ የሚያከናውነው ባለሙያም ከ18 አመታት በፊት ሐውልቱን በገነባው ሰው መሆኑ የታወቀ ሲሆን በሚቀጥለው ሳምንት ዓፅም የማውጣቱ ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ፤ የዛሬ ሣምንት እሁድ ማለትም ሰኔ 18/2009ዓ.ም በከፍተኛ ድምቀት ለሀገር ከፍተኛ አስተዋዕፆ ያደረጉ ሰዎች ስርዓተ- ቀብራቸው ወደ ሚፈፀምበት “መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል” እንደሚዘዋወር እቅድ መያዙን ለማወቅ ተችሏል።

ፕሮፌሰር አሥራት የዛሬ 18 ዓመት “በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል” ስርዓተ- ቀብራቸው እንዳይፈም በአቶ መለስ ቀጭን ትዕዛዝ መተላለፉን ተከትሎ ወዳጆቻቸውና የፓርቲያቸው አባላት በሥላሴ ካቴድራል እንቀብራለን በማለታቸው በተቀሰቀሰ ግጭት ፖሊስ ሁለት ወጣቶችን ተኩሶ መግደሉ የሚታወስ ነው።

ፕሮፌሰር አስራት በ1984ዓ.ም አማራው ዘር ላይ በአርባጉጉ፣በደኖ፣አሰቦት ገዳም፣በአሩሲ ነገሌና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሲገደል፣ እስከነ ነፍሱ ገደል ሲጣልና እጅግ አሰቃቂ የሆነ ሰብአዊ ጥሰት ሲፈጸምበት “ እሳት ለማጥፋት” በማለት የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት(መአህድ)ን መሰረቱ። በኋላም ወያኔ/ኢህአዴግ አማራውን ለአመፅ አነሳስተዋል በማለት በተደጋጋሚ ክስ መሰረተባቸው። በወቅቱ አለም በቃኝ እየታባለ በሚጠራው ከርቸሌ በጨለማ ቤት ታስረው የተለያየ የጤና እክል ገጠማቸው። ህክምናም እንዳያገኙ ተከለከሉ። በመጨረሻም ህመማቸው ሲጠና አሜሪካን ሀገር ሄደው እንዲታከሙ ተደረገ። ህይወታቸውን ማትረፍ ሳይቻል በዚያው አሜሪካን ሀገር በ70 ዓመታቸው ግንቦት 6 ቀን 1991ዓ.ም አረፉ።

LEAVE A REPLY