በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ የኮንግረስ ኮሚቴ ስምምነት ደረሰ /ቪ.ኦ.ኤ/

በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ የኮንግረስ ኮሚቴ ስምምነት ደረሰ /ቪ.ኦ.ኤ/

ዋሺንግተን ዲሲ — የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብቶች ይዞታና አጠቃላይ አስተዳድር ከዩናይትድ ስቴትስ ፖሊሲ ጋር ለመቃኘት ያለመ ረቂቅ ህግ ዛሬ በህግ አርቃቂው የኮንግረስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ፊት ቀርቦ ድምፅ እንዲሰጥበት ሙሉ በሙሉ ስምምነት ተደርሶበታል።

ለሙሉ ኮሚቴው ከቀረቡት ዘጠኝ የሕግ ረቂቆች አንዱ የሆነው ውሣኔ 128 የኒው ጀርሲው እንደራሴ ክሪስ ስሚት እና ከሃምሣ በላይ የኮንግረስ አባላት የደገፉት ነው።

የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴው የአፍሪካ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት እንደራሴው ክሪስ ስሚዝ ባሰሙት ቃል “ኢትዮጵያ ጠቃሚ ወዳጅና በዓለም አቀፍ ሰላም ጥበቃ ውስጥም አጋር ብትሆንም እየቀጠሉ ያሉት የሰብዓዊ መብቶች ረገጣዎች ፈፅሞ ተቀባይነት የላቸው” ብለዋል።

“በፀጥታ ኃይሎች የሚፈፀሙ የዘፈቀደ እሥራቶች፣ ግድያዎችና የማሰቃየት አድራጎቶች፣ በመናገርና በመደራጀት ነፃነቶች ላይ እየተጣሉ ያሉ እገዳዎች፣ በተቃዋሚዎችና በጋዜጠኞች ላይ የሚካሄዱ በፖለቲካው የሚመሩ የፍርድ ሂደቶች፣ የማዋከብና የማሸማቀቅ ድርጊቶች …. ሪፖርቱን ስታነብቡት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የቀረበ ክሥ ዓይነት ነው” ብለዋል ሊቀመንበሩ አክለው።

LEAVE A REPLY