የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የውሀ ሀብት ሚኒስትሮች የአባይ ግድብን እየጎበኙ ነው ተባለ

የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የውሀ ሀብት ሚኒስትሮች የአባይ ግድብን እየጎበኙ ነው ተባለ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ የኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ የውሀ ሀብት ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ የተጀመረውን የአባይ ግድብን እየጎበኙ ነው ተባለ።የሦስቱ ሀገራት ሚኒስትሮች ግድቡን ዛሬ ከጎበኙ በሗላ ነገ በአዲስ አበባ ስብሰባም እንደሚቀመጡ የግብጽ የሚዲያ ተቋማት እየዘገቡ ነው።

ኢትዮጵያ እየገነባች ያለቸው የአባይ {ህዳሴ} ግብድ ግንባታ በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ የሚያመጣው ተጽዕኖ ካለ በሚል ጥናት እንዲያደርጉ ለሁለት የፈረንሳይ ኩባንያዎች መሰጠቱ የሚታወስ ሲሆን በነገው የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ታውቋል።

በኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ እ.ኤ.አ 2015 የተመረጠው የጥናት ቡድኑ በአስራ አንድ ወራት ጨርሶ ጥር 2016 ጥናቱን እንዲያስረክብ ስምምነት የነበረ ቢሆንም በተደጋጋሚ በማራዘም ከዚህ ደርሷል።በተለይም ግብጽ ግድቡ ተጠናቆ የውሀ ሙሌት ሲጀመር ከ1000 ሜትር ኩብ ወደ 600 ሜትር ኩብ ይቀንስብኛል በማለቷ ጉዳዩን የበለጠ ውስብስብ አድርጎታል።

LEAVE A REPLY