የቴዲ አፍሮ መፈክር በኦቦ ለማ መገርሳ አንደበት… “ፍቅር ያሸንፋል!!” /ያሬድ ሹመቴ/

የቴዲ አፍሮ መፈክር በኦቦ ለማ መገርሳ አንደበት… “ፍቅር ያሸንፋል!!” /ያሬድ ሹመቴ/

የቴዲ አፍሮ መፈክር በኦቦ ለማ መገርሳ አንደበት ተጠርቷል
“ፍቅር ያሸንፋል!!”

ኢትዮጵያዊነት ከደም አልፎ በልብ ውስጥ የተቀመጠ የተከበረ ማንነት ነው- ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው።
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ

‹‹ኢትዮጵያዊነት ምን እንደሆነ ዛሬ ባየነው ትዕይንት ትርጉሙ ገብቶኛል፡፡ኢትዮጵያዊነት ልዩ ነው፡፡ አትዮጵያዊነት ሱስ ነው፡፡ከደም አልፎ ልቡ ውስጥ እንዳለ ዛሬ አይተነዋል፡

ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የትም ይሁን የት ፣ምን ያህል የኢትዮጵያዊነት ርሀብ እንዳለበት በመላው ዓለም የሚገኙ ሁሉ መምጣታችንን ሲሰሙ ምን ያህል በውስጣቸው እንዳደረ አይተናል፡፡ችግሮቻችንን በጋራ እየፈታን ለእድገታችን የምንሰራበት ጊዜም ነው ብለዋል፡፡

ለዚች ሀገር ህይወቱን አሳልፎ የሰጠው ይህ ህዝብ ለሀገሩ ፣ለአንድነቱ ነው፡፡ትናንት በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ደሙን የገበረው ለኢትዮጵያ ነው፡፡ለሀገራችን አሁንም መስራት ይጠበቅብናል፡፡ወደ ኋላ እያየን ወደፊት ልንጓዝ አንችልም፡፡ያለፈውን እንርሳው ፡፡ለሀገራችን አንድነት በጋራ እንቁም ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ዛሬ አማራ ክልል የተገኘነው እንደምስታፈልጉን ፣እንደምናስፈልጋችሁ ስለምናምን ነው፡፡ለኢትዮጵያችን ሁሉም ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ያስፈልጓታል፡፡ፍቅር ያሸንፋል፡፡ብሄሮች በጋራ ሊቆሙላት ይገባል፡፡ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ላይ ነው ያለነው፡፡በጎረቤቶቻችን ላይ ያለውን መመልከት ያስፈልጋል፡፡ለምናደርጋቸው ነገሮች ሀላፊነት ሊሰማን ይገባል፡፡

አቶ ለማ አክለውም የሀገሪቱ ተረካቢ ለሆነው ወጣት ስራ ልንፈጥርለት ይገባል፡፡ትውልዱን ለመቅረጽ ደግሞ ቅድሚያ የሚወስደው ቤተሰብ ነው፡፡በመቀጠልም ማህበረሰብ ፤ስለሆነም ለስነ-ምግባር ጉዳይ ቅድሚያ ልንሰጥ ይገባል፡፡አባቶች ፣አባ ገዳዎች ፣የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ስነ-ምግባርን በተመለከተ ትኩረት ልትሰጡት ይገባል ብለዋል ፡፡

LEAVE A REPLY