የ“ህዳሴው ግድብ” ለኢትዮጵያዊያንም እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

የ“ህዳሴው ግድብ” ለኢትዮጵያዊያንም <ህይወት ወይም ሞት> እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ ኢትዮጵያ እየገነባችው ያለችው የአባይ ግድብ(ህዳሴ ግድብ) ለኢትዮጵያዊያንም “ህይወት ወይም ሞት” መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም አስታወቁ።

ግድቡን የሚስቆም አዳችም ሀይል የለም ሲሉ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል። የግብጹ ፕሬዚዳንት ጄነራል አብደል ፋታህ አል-ሲሲ “የአባይ ጉዳይ ለግብጽ ሞት ወይም ህይወት ነው።” በማለት በቅርቡ በተደጋጋሚ ለሰጡት ማስጠቀቂያ ምላሽ በሚመስል መልኩ የ“ህዳሴውን ግድብ የሚያስቆም ማንም ሀይል የለም” ብለዋል። ግድቡን በተመለከተ የግብጽ ሚዲያዎች የሚያናፍሱት ወሬም ተገቢ አለመሆኑን ጠቅሰዋል።

የግብጹ ፕሬዚደንት አል-ሲሲ የ”ህዳሴውን ግድብ” በማስመልከት ባለፉት ሳምንታት ባደረጓቸው ንግግሮች የዓባይ ወንዝ ለግብፃውያን “የህይወትና ሞት ጉዳይ ነዉ” ሲሉ ኢትዮጵያን ማስጠቀቃቸውን ዘግበናል። የግብጹ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም የ“አባይ ግድብ” ጉዳይ ለሀገራቸው እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ ለአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሬክስ ቲለርሰን ማክሰኞ እለት ማሳወቃቸው ተገልጿል።

ግድቡን በተመለከተ የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና ግብጽ የመስኖ ሚኒስትሮች ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አስራ ሰባት ጊዜ የተገናኙ ቢሆንም ስምምነት ላይ አለመድረሳቸው ይታወቃል። ግብጽ በቅኝ ጊዜ የነበረው የውሀ ሀብት አጠቃቀም ተጨምሮ ተግባራዊ እንዲሆን መጠየቋ ለልዩነቱ ሁነኛ መንስኤ እንደሆነ ከኢትዮጵያ በኩል እየተጠቀሰ ነው። የዛሬው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ እንደጠቆመው ከሆነ“ፍትሃዊ ያልሆኑ ውሎችን ከዚህ በፊት ያለፉት የኢትዮጵያ መንግስታት እንዳልተቀበሉት ሁሉ አሁንም ልንቀበል አንችልም” በማለት አስረድተዋል።

LEAVE A REPLY