የህዝብና ቤቶች ቆጠራ በድጋሜ እንዲራዘም ተጠየቀ በአንድ ዓመት እንዲራዘም ተጠየቀ

የህዝብና ቤቶች ቆጠራ በድጋሜ እንዲራዘም ተጠየቀ በአንድ ዓመት እንዲራዘም ተጠየቀ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ በየዓስር ዓመቱ ሚካሄደውን የህዝብና ቤቶች ቆጠራ በድጋሜ እንዲራዘም ተጠየቀ።መደበኛ መርሃ ግብሩ ባለፈው ህዳር ወር የነበረው ቆጠራ በጸጥታ ምክንያት ወደ የካቲት 2010ዓ.ም ተራዝሞ ነበር። የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በየካቲት ወር ሊደረግ የነበረውን አራተኛውን የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ወደ ሚቀጥለው ዓመት እንዲተላለፍለት ጥያቄ ማቅረቡን ሪፖርተር ዘግቧል።

በአገሪቱ በተፈጠረው አለመረጋጋት፣ በተለይም በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች ባጋጠመው ግጭት ምክንያት በርካታ ዜጎች በመፈናቀላቸው ምክንያት ቆጠራውን በዚህ ዓመት ማድረግ እንደማይቻል፣ የኤጀንሲው ኃላፊዎች እምነት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የህዝብ ቆጠራውን የማራዘም ስለሌለው ጉዳዩ ለፓርላማ ቀርቦ እንዲጸድቅ ተጠይቋል።ፓርላማው ጥያቄውን ተቀብሎ የሚያራዝመው ከሆነ በሚቀጥለው ህዳር 2011ዓ.ም ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተጠቁሟል።

LEAVE A REPLY