ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አንዷዓለም አራጌና ሌሎች 746 እስረኞች እንዲለቀቁ ተወሰነ

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አንዷዓለም አራጌና ሌሎች 746 እስረኞች እንዲለቀቁ ተወሰነ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ የ18 ዓመት ፍርደኛው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ የእድሜ ልክ የተወሰነበት አንዷለም አራጌና ሌሎች 746 እስረኞች እንዲለቀቁ መወሰኑን ለስርዓቱ ቅርብ የሆኑ ‎የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ዘገቡ።

ከተለቀቁት መካከልም በግንቦት ሰባት፣ በኦነግ፣ በሀይማኖት አክራሪነትና በህዝባዊ ተቃውሞ ወቅት ክስ ተመስርቶባቸው የታሰሩ መሆናቸው ታውቋል።

ጠቅላይ አቃቤ ህግ እንደገለፀው ከተለቀቁት እስረኞች መካከል 119 የሚሆኑት በአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ መሆናቸውን ገልጿል። የሚለቀቁት የእስረኞች ዝርዝር በይቅርታ ቦርድ ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ቀርቦ ከጸደቀ በሗላ “የተሀድሶ” ስልጠና እንደሚወስዱም ተገልጿል።

የአውራምባ ታይምስ ምክትል አዘጋጅ የነበረውና 14 ዓመት ተፈርዶበት በዝዋይ እስር ቤት የሚገኘው ጋዜጠኛ ውብሸት ታየ ከሚፈቱት መካከል ይካተት አይካተት ለማወቅ አልተቻለም።

LEAVE A REPLY