እነ እስክንድር ‎ በውሸት አንፈርምም አሉ፤ ዮናታን ተስፋየ በዚህ ዙር ከሚፈቱት አለበት...

እነ እስክንድር ‎ በውሸት አንፈርምም አሉ፤ ዮናታን ተስፋየ በዚህ ዙር ከሚፈቱት አለበት ተባለ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ ከሰባት መቶ በላይ እስረኞች እንደሚፈቱ በተገለጸ ማግስት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ፖለቲከኞቹ አንዷለም አራጌ እና አበበ ቀስቶ የግንቦት 7አባል ነበርን ብላችሁ ፈርሙ በመባላቸው እና እነሱ ያልሆነውን ነን አንልም በማለታቸው ሳይፈቱ መቅረታቸው ተገለጸ፡፡

በእርቅና ይቅርታ ይፈታሉ የተባሉት እነንሁ ታሳሪዎች ጉዳይ አለም አቀፍ ተቂአማትንና መገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስበወንደንበር የሚታወቀ ነው፡

የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ህ/ግንኙነት ሀላፊ የነበረው ዮናታን ተስፋየ በዚህ ዙር ከሚፈቱት የፖለቲካ እስረኞች መካከል ስሙ መጠቀሱን የአዲስ ጋዜጣ ምንጮች አረጋግጥዋል።

ታህሳስ 2008ዓ.ም ታስሮ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት “የጸረ-ሽብር” አዋጁን አንቀጽ 6ን በመተላለፍ በማለት 6 ዓመት ተኩል ተፈርዶበት እንደነበረ ይታወቃል። ዮናታን ይግባኝ ጠይቆ ከ“ሽብር ክስ” ወደ መደበኛ ወንጀል ህግ 257(ሀ) ክሱ ተሻሽሎ ከ6 ዓመት ተኩል ወደ 3 ዓመት ዝቅ እንዲልለት መወሰኑም ይታወቃል። ዮናታን ለእስር ያበቃው የተለያዩ ሀሳቦችን የሚያጸባርቁ ፁሁፎችን በፌስ ቡክ ገፁ ላይ በመልቀቁ እንደሆነም በወቅቱ ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም በ2001ዓ.ም በመፈንቅለ መንግስት ተጠርጥረው በግፍ ታስረው የሚገኙት እነ ጄኔራል አሳምነው ጽጌ፣ጄኔራል ተፈራ ማሞ፣ወይዘሮ እማዋይሽ አለሙና ሌሎች ም በዚህ መዝገብ የተካተቱት እስረኞች ከሚፈቱት መካከል እንደተካተቱ ቤተሰቦቻቸው ፍንጭ እንዳገኙ የገለጹልን ሲሆን አፈታታቸው ግን በምን ቅድመ ሁኔታ ሊሆን እንደሚችል የታወቀ ነገር የለም።

LEAVE A REPLY