በየመን ባህር ተገፍትረው የተጣሉ 25 ኢትዮጵያዊያን የደረሱበት አልታወቀም

በየመን ባህር ተገፍትረው የተጣሉ 25 ኢትዮጵያዊያን የደረሱበት አልታወቀም

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ የተባበሩት መንግስታት የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) ትናንት ማምሻውን እንዳስታወቀው 25 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደ ባህር ተገፍትረው ከተጣሉ በሗላ የደረሱበት እንዳልታወቀ ገለጸ።

በየመን በአራት ጀልባዎች ሲጓዙ ከነበሩ 600 በላይ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች መካከል 25 የሚሆኑት ወደ ባህር ተገፍትረው እንደተጣሉ የአይ.ኦ.ኤም (IOM) ቃል አቀባይ ጆኤል ሚልማን ተናግረዋል። ቃል አቀባዩ እንደገለጹት ወደ ብህር ተገፍትረው የተጣሉት 25 ኢትዮጵያዊያን በህይወት ይኖራሉ ብለው እንደማያምኑም ጨምረው ገልጸዋል።

ባለፈው ዓመት ብቻ 87 ሺህ ስደተኞች ከጅቡቲ በመነሳት የእርስ በእርስ ጦርነት ቀጠና በሆነውና 8 ሚሊዮን ህዝቧ የተራበባትን የመንን እንደ መሸጋገሪያነት እንደተጠቀሙ የአይ.ኦ.ኤም ቃል አቀባይ ገልጸዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያዊያን ጨምሮ ከአፍሪካ የሚነሱ በርካታ ስደተኞች ሜዲትራሊያን ባህር በማቋረጥ ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ በአሸጋጋሪዎቻቸው ወደ ባህር እየተገፈተሩ ህይወታቸውን እንደሚያጡ ሲዘገብ ቆይቷል።

LEAVE A REPLY