ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የአማካሪነት ቦታ እንዲሰጣቸው ተወሰነ

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የአማካሪነት ቦታ እንዲሰጣቸው ተወሰነ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡ – ሰሞኑን 3 ሚሊዮን ብር የሚገመት መኪና ከኦህዴድ የተበረከተላቸው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፤ ወርሃዊ ደመወዝ የሚያገኙበት የአማካሪነት ቦታ እንዲሰጣቸው መወሰኑም ታውቋል፡፡

ባለፈው ረቡዕ የካቲት 14፣ በኦህዴድ ጽ/ቤት ተገኝተው፣ ኒሳን 2018 ሞዴል መኪና የተረከቡት ዶ/ር ነጋሶ፤ “ኦህዴድ ቃል የገባውን ሁሉ ፈፅሞልኛል፤ የደሞዝ ጉዳይም ሆነ የህክምና ጉዳይ እየተመቻቸልኝ ነው፣ በተደረገልኝ ሁሉ ደስተኛ ነኝ” ሲሉ መግለፃቸውን አዲስ አድማስ ዘግቧል።

“በአማካሪነት የምሰራበትን ቦታ ነግረውኛል፤ እርግጠኛ ስሆን የተመደብኩበትን እገልፃለሁ” ያሉት ዶ/ር ነጋሶ፤ “የደመወዜ መጠንም የሚታወቀው ይህን የአማካሪነት ስራ ስጀምር ነው” ብለዋል፡፡

ዶ/ር ነጋሶ አሁን ካሉበት የተቃውሞ ፖለቲካ ጋር የቀረበላቸውን የማማከር ስራ እንዴት ሊያጣጥሙት እንደሚችሉ የተገለጸ ነገር ባይኖርም አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ እየታየ ላለው የፖለቲካ ውጥንቅጥ ሁነኛ የመፍትሄ ሃሳቦችን በመስጠት ሃገሪቱን ወደተሻለ ጎዳና ለመምራት አስተዋጾ ያበረክታሉ ተብሎ ይገመታል የሚሉ ተንታኞች ዶ/ር ነጋሶ በተለያዩ ጎራወች ያሉ የፖለቲካ ምልከታዎችን ለማየት እድሉን ያገኙ እንደመሆናቸው መጠን አስተዋጾዋቸው የሚጠበቅ መሆንኑን አስምረውበታል፡፡

ዶክተር ነጋሶ በኦህዴድ በኩል ለተደረገላቸው ሁሉ አመስግነው በህግ የተሰጣቸውን መብቶችና ጥቅማ ጥቅሞች የፌደራሉን መንግስትም እንዲያከብርላቸው መጠየቃቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY