ህውሀት መራሹ ኢህአዴግ ዶ/ር አብይ አሕመድን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት መረጠ

ህውሀት መራሹ ኢህአዴግ ዶ/ር አብይ አሕመድን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት መረጠ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡ – ረጅም ጊዜ የወሰደው የህወሀት መራሹ የኢህአዴግ ፓርቲዎች ስብሰባ ዶ/ር አብይ አህመድን የግምባሩ ሊቀመንበር አድርጎ በመሾም ተጠናቀቀ።

ጭቅጭቅ የበዛበት መሆኑ የተነገረለት ይሄው ስብሰባ በተለይ መሪውን ለመምረጥ ውዝግቦች ተከስተው እንደነበር ተዘግቧል።

ዶ/ሩ ወንበሩን እንደተረከቡ በርካታ ቅድመ ስራዎች  እንደሚጠበቅባቸው የተገለጸ ሲሆን በተለይም በከፍተኛ ውጥረት ላይ የሚገኘውን የሃገሪቱን ፖለቲካ  መፍተሄ  ለመስጠት የሚወስዱት እርምጃ ለራሳቸውም ሌጋሲ ሆነ ለሃገሪቱ መጻኢ እድል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ተገምቷል።

የሚያበረክቱትን መልካም አስተዋጾ በአሉታዊም ሆነ በአዎንታዊ መልኩ ለመቅረጽ ቁርጠኝነትና ውሳኔ መስጠት የሚያስችላቸውን ብቃትና መስመር የማስጠበቅ ከፍተኛ ክህሎት እንደሚጠበቅባቸው ይጠበቃል።

ድርጅቱ በአሁኑ ሰዓት የገባበት የፖለቲካ ውጥረትና የህዝባዊ እምቢተኛነት ተቃውሞ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን የሚስማሙ በርካቶች ሲሆኑ ስርነቀል ለውጥ ካልመጣ ድርጅቱ በሚያደርገው ጥገና የሚያመጣው ለውጥ እንደሌለ የሚናገሩ አስተያየት ሰጪዎች አሁንም ሀገሪቱን በተረጋጋ መልኩ ለመምራት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በአፋጣኝ ማንሳት፣ እስረኞችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት፣  ከሁሉም ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ይፋዊ ድርድር ማድረግ፣ ምርጫ ቦርድን አፍርሶ በሕዝብ በታመኑ ባለሙያዎች መተካት፣ ግልጽና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማድረግ በሚያስችል መልኩ መገናኛ ብዙሃንን ነጻነት ማረጋገጥ ሁነኛ እርምጃዎች መሆናቸውን ያመላክታሉ።

LEAVE A REPLY