አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር መወያየታቸው ተገለፀ

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር መወያየታቸው ተገለፀ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር መወያየታቸው ተገለፀ። ትናንት ከእስር የተለቀቁት የአርበኞች ግንቦት 7 ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር ዛሬ ከሰዓት በሗላ በጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ተገኝተው ወይይት ማድረጋቸው ታውቋል።

የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ  ዛሬ ማምሻውን በቲውተር ገፃቸው ላይ እንደገለጹት አቶ አንዳርጋቸው ከዶክተር አብይ ጋር መገናኘታቸውን በፎቶ አስደግፈው ገልጸዋል።

በምን ጉዳይ ላይ እንደተወያዩ ባይገለጽም አቶ አንዳርጋቸው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የነበራቸው ቆይታ ተስፋ ሰጭ እንደነበር መግለፃቸውን ያገኘነው መረጃ ጠቁሟል።

 

LEAVE A REPLY