ዶ/ር አቢይ በደቡብ ክልል የአራት ዞንና ወረዳ አመራሮች በአስቸኳይ ከስልጣን አንዲወርዱ አዘዙ

ዶ/ር አቢይ በደቡብ ክልል የአራት ዞንና ወረዳ አመራሮች በአስቸኳይ ከስልጣን አንዲወርዱ አዘዙ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በደቡብ ክልል የሲዳማ፣ ወላይታ፣ ጉራጌና ከምባታ የዞንና የወረዳ አመራሮች በአስቸኳይ ከስልጣን እንዲወርዱ ማዘዛቸው ተገለጸ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰሞኑን በሀዋሳ፣ወላይታ ሶዶ፣ወልቂጤና ሌሎች ቦታዎች ለተከሰተው የርስ በርስ ግጭት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ምክንያት የዞንና ወረዳ አመራሮች በአስቸኳይ ስልጣን እንዲለቁ ያዘዙ ሲሆን በህግ እንደሚጠየቁም ተጠቁሟል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደቡብ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ሰሞኑን በተቀሰቀሰው የርስ በርስ ግጭት ዙሪያ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ከሀይማኖት አባቶችና ከሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እያካሄዱ ሲሆን ዛሬ በወልቂጤ በነበራቸው ውይይት በሀዋሳ፣ወላይታ ሶዶ፣ቀቤና እና በሌሎች ቦታዎች ለተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት ከስልጣን የሚለቁት አመራሮች ሙሉ ሀላፊነት እንደሚወስዱም ዶክተር አብይ አህመድ መጠቆማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ ገልጸዋል።

 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ትናንት ከሀዋሳና ወላይታ ሶዶ ነዋሪዎች ጋር ውይይት ያካሄዱ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ከጠዋት ጀምረው ከወልቂጤና አካባቢው  ነዋሪዎች ጋር ውይይት በማድረግ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በፍቸ ጨበላላ ዓመታዊ በዓል ሲከበር የተቀሰቀሰው ግጭት ወደ ሌሎች ቦታዎችም በመዛመት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማስከተሉ የሚታወስ ነው።

LEAVE A REPLY