በመስቀል አደባባይ በህዝብ ላይ በተጣለው ቦንብ እጃቸው አለበት የተባሉ የፖሊስ ኮሚሽነሮች ተያዙ

በመስቀል አደባባይ በህዝብ ላይ በተጣለው ቦንብ እጃቸው አለበት የተባሉ የፖሊስ ኮሚሽነሮች ተያዙ

የተለያዩ ሀገራትና ተቋማት ድርጊቱን አውግዘዋል።

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በመስቀል አደባባይ በህዝብ ላይ በተጣለው ቦንብ እጃቸው አለበት የተባሉ የፖሊስ ኮሚሽነሮች ተያዙ።የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ 9 የፌዴራልና የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽነሮች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ኢቲቪ ዘግቧል።

 በቦንብ ጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው በተለያዩ ሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዘውዲቱና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታሎች ተገኝተው ጎብኝተዋል።

በሌላ በኩል

የአውሮፓ ህብረት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አጋርነት ለማሳየት በመስቀል አደባባይ በወጣው ህዝብ ላይ የተፈፀመው ጥቃት ፍፁም ተቀባይነት የሌለው ነው ብሏል።በሰልፉ ላይ የደረሰው ጥቃት መልዕክቱ ግልፅ ቢሆንም በጠቅላይ ሚኒስትሩና በጓዶቻቸው የተጀመረው የለውጥ ሂደት ሊስተጓጎል አይችልም ሲል ህብረቱ አስታውቋል።

 የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ተሀድሶ በማገዙም ኩራት እንደሚሰማው በመግለጫው አስታውቋል።

የአፍሪካ ህብረት፣ሶማሊያ፣ኬንያ፣ኤርትራ፣ጅቡቲና የተባበሩት ኤምሬቶች አዲስ አበባ ላይ በደረሰው የቦንብ ጠቃት እጅግ ማዘናቸውን ገልፀው ሁሉም ከኢትዮጵያ ህዝብና ዶክተር አብይ ጋር እንደሚቆሙ አስታውቀዋል።

  አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ም የተፈጠረውን ለውጥ ለማስቀጠል፣ለማድነቅና ምስጋና ለማቅረብ አደባባይ ላይ በተገኙት ዜጎች ላይ የደረሰውን ጥቃት ተቀባይነት የለውም ብሏል።

LEAVE A REPLY