/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በራያ የተለያዩ ቦታዎች የተቃውሞ ሰልፎች ሲካሄዱ ውለዋል። በዋጃና ጥሙጋ በተባሉ አካባቢዎች የማንነት ጥያቄ በሚጠይቁ ነዋሪዎችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል ላለፉት ሁለት ሳምንታት የተፈጠረው ግጭት ዛሬም ቀጥሎ ውሏል።
የመከላከያና የትግራይ የደህንነት አባላት በወጣቶች ላይ ግድያ፣እስራትና ድብደባ እየፈሙ መሆኑም ታውቋል። ባለፉት ሦስት ቀናት ብቻ ቢያንስ ሁለት ወጣቶች መገደላቸውንና ሌሎች በርካታ ወጣቶች ለእስር ተዳርገዋል።
በዋጃና ጥሙጋ በተባሉ ቦታዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ወደ አደባባይ በመውጣት የተቃውሞ ሰልፍ ሲያካሂድ ውሏል። ዛሬ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከተሰሙ መፎክሮች መካከልም “በአፍ መፍቻ መማርና መዳኘት ተፈጥሮዊ መብታችን ይከበር። የትግራይ ህዝብ አምሳላችን፤የወሎ ህዝብ ደግሞ አካልና ደማችን ነው።”የሚሉት ይጠቀሳሉ።
የህዝቡን ከፍተኛ ተቃውሞ ተከትሎም ታሰረው የነበሩ ወጣቶች ዛሬ ከሰዓት መፈታታቸውን ያገኘነው መረጃ ጠቂሟል።
በሌላ በኩል የኢንጂነር ስመኘው በቀለን ግድያ ተከትሎ ለተቃውሞ ወደ አደባባይ ከወጡ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች መካከል ሁለት ወጣቶች ቆስለው ለህክምና ሆስፒታል ገብተዋል። ጎንደር ከሰዓት በሗላ አንፃራዊ መረጋጋት ቢታይባትም የንግድና ትራንስፖርት እንቅስቃሴ አልተጀመረም።