በቄሌም ወለጋ ዞን የደምቢ ዶሎ ከተማ ነዋሪዎች አድማ ላይ ናቸው

በቄሌም ወለጋ ዞን የደምቢ ዶሎ ከተማ ነዋሪዎች አድማ ላይ ናቸው

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በምዕራብ ኢትዮጵያ በቄሌም ወለጋ ዞን የደምቢ ዶሎ ከተማና የአካባቢው ነዋሪዎች ከቤት ያለመውጣት አድማ ላይ መሆናቸው ተገለጸ።

የአድማው ምክንያትም  በከተማው እየተፈፀሙ ያሉ ግድያዎችን በመቃወም ሲሆን ከትናንት ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚቆይ ከቤት ያለመውጣት አድማ መጀመሩ ታውቋል።

ከቤት ያለመውጣት አድማው ከደምቢ ዶሎ በተጨማሪም በተለያዩ የወረዳ ከተሞች እየተደረገ ይገኛል። በቄሌም ወለጋ ዞን በአብኛው ወረዳዎች የትራንስፖርት፣የንግድና ሆቴል አገልግሎቶች መቋረጡ ታውቋል።

በደምቢ ዶሎ ከተማ ባለፈው ሰኞ ሌሊት ለመውለድ ሆስፒታል በመሄድ ላይ የነበረች እናት የኦሮሚያ የልዩ ሀይል ፖሊስ አባላት ተኩሰው መግደላቸውን ተከትሎ በአካባቢው አለመረጋጋት ተፈጥሯል።ጥቃቱን አድርሰዋል የተባሉ አራት የልዩ ሀይል ፖሊስ አባላት በማግስቱ ማክሰኞ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ማስታወቁ ይታወሳል።

LEAVE A REPLY