ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈፃሚ የነበሩት ኢንጅነር አዜብ አስናቀ ከሀላፊነታቸው ተነሱ

ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈፃሚ የነበሩት ኢንጅነር አዜብ አስናቀ ከሀላፊነታቸው ተነሱ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የድርጅቱን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር አዜብ አስናቀን ከሀላፊነት አነሳ። በአምባሳደት ግርማ ብሩ የሚመራው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የዳሬክተሮች ቦርድ በትናትናው ዕለት ባደረገው ስብሰባ ከወሳኔ ላይ መድረሱን ካፒታል የእንግሊዝኛ ጋዜጣ(Capital) ዘግቧል።

ካፒታል እንደዘገበው ዶክተር አብረሃም በላይ ኢንጅነር አዜብን ተክተው የሀላፊነት ቦታውን እንደሚረከቡ ይጠበቃል። ዶክተር አብረሃም በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (INSA) ስር የሚገኝ የማሰልጠኛ ተቋም ዳሬክተር መሆናቸው ተገልጿል።

ወ/ሮ አዜብ አስናቀ ባለፉት በርካታ ዓመታት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይልን በዋና ስራ አስፈፃሚነት ሲመሩ የቆዩ ሲሆን ከከባድ ሙስና ጋር ስማቸው በተደጋጋሚ ሲነሳ መቆየቱ ይታወሳል።

LEAVE A REPLY