የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የልማት ተቋም አማካሪምክር ቤት

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የልማት ተቋም አማካሪምክር ቤት

... ነሐሴ 24, 2018

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የልማት ተቋም አማካሪ ምክር ቤት (ምክርቤት) የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር /ቤት ... ነሐሴ 9 ቀን 2018 . ባወጣው መግለጫ መሰረት በማድረግየኢትዮጵያ ዲያስፖራ በልማት ተሳትፎ ጥረቶችንለማበረታታትና ለማስተባበር ዝግጁ መሆኑን በደስታ ይገልፃል።

በተለያዩ አጋጣሚዎች ጠቅላይ ሚኒስትር / አቢ አህመድየዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን በዩኤስ 1ዶላር በመለገስ በኢትዮጵያወሳኝ አስፈላጊና ያልተሟላ የልማት ፍላጎቶችን እንዲያሙዋሉጠይቋል. በተጨማሪም እንዳሉት የታቀደው የልማት ገንዘብየመንግስት በጀት አካል አይሆንም። በራሱ በራሱ ቦርድይተገበራል።

ለጠቅላይ ሚኒስትር / አብይ ተግዳሮት ምላሽ በኢትዮጵያዲያስፖራ ውስጥ ከፍተኛ አጠቃላይ አዎንታዊ አግኝቷል።

የካውንስሉ አባላት ለተዋጣው ስኬታማ ውጤት ለማረጋገጥየተለያዩ ልዩ ልዩ እውቀታቸውን እና ችሎታቸውን በመጠቀምይጥራሉ። ይህ በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ እና አማካሪካውንስል ብቻ የሚያከናዉኑት ነገር አይደለም። ነገር ግንሁላችንም ሀገራችንን ለማገልገል ባደረግነው ጥረቶች እናግዴታዎች የሚወሰን ነው። በቅርቡ ምክር ቤቱ ተጨማሪአባላት ስራዉን ለመርዳት ይሰየማሉ።

ካውንስሉ አንደኛው ትኩረት የሚሰጠው ወሳኝ ተግባርለድርጅቱ ሁሉን አቀፍ ጠንካራ ተጠያቂነት እና ግልጽነትአሰራር ስነስርዓት መዘርጋት ነው። ለዚህም ገንዘቡንየሚያበረክቱት አስተዋፅኦዎች ተጠቃሚዎች እና ሌሎችባለድርሻዎች ስለ ፈንዱ አስተዳደርና አስተገባበር ያላቸዉንአስተሳሰብ ለማካተት ይጥራል።  

የዲያስፖራው ኢትዮጵያውያኞች አንዳንድ ቦታ ለምን አሁኑኑገንዘብ መዋጮ አንሰጥም የሚል ጥያቄ ያነሳሉ።  

ካውንስሉ ስለፈንዱ ለኢትዮጵያ ዲያስፖራው አንዳንድ  የህግእና የቁጥጥር እውነታዎች እንዲያውቅ ይፈልጋል።

በዲያስፖራው ኢትዮጵያውያን ለሚያደርጉት አስተዋፅኦከፍተኛውን የተጣራ ገቢ እንዲኖር በዓለም ዙሪያ ከበርካታየፋይናንስ ተቋማት ጋር አሰራር ዘዴ እያመቻቸን ነው። ይህንንየምናደርገው የኢትዮጵያን ጨምሮ ለሁሉም ሀገራት ሕጋዊመስፈርቶች መሟላት በማረጋገጥ ለሀገሪቷ ትክክለኛ ሂደቶችእና መቆጣጠሪያዎች መኖራቸውን ለማረጋገጥ ነው። ይህቅንብር በቅርብ ጊዜ ባስቸኳይ መደረግ እንዳለበት ካዉንስሉይረዳል። ይህን ለማድረግ ትንሽ ጊዜ ስለሚጠይቅ የኢትዮጵያዲያስፖራዎችን ትዕግስት እንጠይቃለን።

ካውንስሉ የአሜሪካ ፌዴራል እና የግዛት ህጎችን ማሟላትአለበት። እንዲሁም የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ክዋኔዎችንለማስተዳደር የወጡትን ድነጋጌዎች ማሟላት ያስፈለገዋል።

ካውንስሉ ለድርጅቱ የአስተዳደር መዋቅሮችን እና ሂደቶችንጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ነው

የዲያስፖራው የኢትዮጵያ ህብረተሰብ በትዕግስት ከእኛ ጋርመቆየቱን እንዲቀጥል እንጠይቃለን። በተቻለ ፍጥነት ሁሉንምስራ ለመስራት ዝግጁ ነን።  

ምክር ቤቱ በቀጣዩ ወር መግለጫ እስኪሰጥ ድረስየኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ ደጋፊዎች ወርሃዊ መዋጮለመስጠት ያቀዱትን ለጊዜው እንዲይዙ በአክብሮትይጠይቃል።

ምክር ቤቱ በየጊዜው በድረገፅና በሌሎች የመገናኛ ዘዴዎችኦፊሴላዊ መረጃዎችን ይሰጣል።

ካውንስሉ የተለያዩ  ግለሰቦች እና ቡድኖችን የግል ገንዘብመዋጮ ለፈንዱ ለመሰብሰብ እንደተሰማሩ ያውቃል።  ነገር ግንእነዚህ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች ከካዉንስሉ ጋር የሚሰሩአይደሉም።  ወደፊት ፈንዱ መተገበር ሲጀምር ከካዉንስሉ ጋርእንደሚተባበሩ ተስፋ እናደርጋለን።

ምክር ቤቱ በመጀመሪያ ጊዜ ጥራት ያለው ስራ መስራት ይሻላልወደህዋላ ተመለሶ ከመጠገን በሚለው ሃሳብ ይመራል።

ኮሚሽኑ ለመላው የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ፈንዱን ለመደገፍላሳዩት ከፍተኛ ጉጉት ድጋፍና በጎ ፈቃድ ምስጋናዉን ያቀርባል።

የካውንስሉ ሰብሳቢ /  አለማየሁ ገብረማርያም

እውቅያ: EDTF2018@gmail.com

LEAVE A REPLY