አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ የወርቅ ሽልማት ተበረከተለት

አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ የወርቅ ሽልማት ተበረከተለት

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ የወርቅ ሽልማት እንደተበረከተለት የአማራ ቴሌቪዥን ዘገበ። ዛሬ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ታማኝ በየነ በከተማው ነዋሪዎች 150 ግራም የሚመዝን ወርቅ እንደተበረከተለት ገልጿል።

 ከአማራ ክልል መንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም ከባህር ዳር ከተማ የተውጣጡ ነዋሪዎች በአቫንቲ ብሉናይ ሪዞርት የእራት ግብዣ ተደርጎለታል ተብሏል።

የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማህበር ደግሞ በስሙ የተሰራ ጭራ ሲያበረክቱለት፣ ለባለቤቱ አርቲስት ፋንትሽ በቀለም የአካባቢውን የሚገልጽ የባህል ልብስ እንደተበረከተላት ታውቋል።

አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ከ22 ዓመታት የስደት ህይወት በሗላ ቅዳሜ ዕለት ሀገሩ መግባቱ ይታወሳል።

LEAVE A REPLY