የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በውጭ ሀገር ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያየ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በውጭ ሀገር ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያየ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል በቅርቡ ወደ ሀገር ቤት ከገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያየ። የቦርዱ ሰብሳቢ አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ በወይይቱ ላይ እንደገለጹት ሀገሪቱ በለውጥ ሂደት ውስጥ እንደምትገኝ ጠቅሰው፤ ቦርዱም የተለያዩ የማሻሻያ (ሪፎርም) ስራዎች በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በምርጫ ህግ፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝግባ አዋጅና ፓርቲዎች ምዝገባ ሲያካሂዱ ማሟላት ስለሚገባቸው መስፈርቶች እንዲሁም የፓርቲዎች መብትና ግዴታ ላይ ያጠነጠነ ፅሑፍ በቦርዱ የህግ አገልግሎት ዳይሬክተር በኩል ቀርቦም ውይይት እንደተደረገበት ተገልጿል።

 የሚቀጥለው ምርጫ ስላማዊ፣ ነፃ እና ተዓማኒ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እንደተጀመረና የተለያዩ ግብዓቶች እየተሰበሰቡ እንደሆነም  አምባሳደር ሳሚያ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በዘመነ ኢህአዴግ አምስት ያህል ምርጫዎችን ያካሄደች ሲሆን በድህረ ምርጫ ወቅት በሚነሳ ግጭት በርካታ ዜጎች ለሞት፣ እስራት እና ስደት መዳረጋቸው የሚታወስ ነው። በየአምስት ዓመቱ የሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በ2012 ዓ.ም ይካሄዳል ተብሎም ይጠበቃል።

LEAVE A REPLY