ስለ ኢንጂነር ስመኘው ግድያ የተሰማኝ… /በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ/

ስለ ኢንጂነር ስመኘው ግድያ የተሰማኝ… /በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ/

[መነበብ ያለበት – ሙያዊ ዳሰሳ]

እራሱን ነው ያጠፋው ወይስ በሰው ነው የተገደለው..? የሚለው ጭቅጭቅ ውስጥ መግባት አልፈልግም…ፖሊሶቹ ካቀረብት የተሻለ መረጃ የሚሰጠኝ ሰው እስካገኝ ድረስ የተሰጠውን መግለጫ እቀበላለው….

እኔ መናር የምፈልገው ከሜቴክ ጋር ስለተገናኘው ነገር ነው…በአባይ ግድብ ደራጃ ባይሆንም በመንግስት የግንባታ ፕሮጀክቶች ከ6 ዓመት በላይ ከሳይት ኢንጂነርነት እስከ ስራ-አስኪያጅነተ የስራ መደብ ባሉት ቦታዎች ሰርቼያለው…ስለሆነም የፕሮጀክት ክፍያ እንዴት እንደሚከፈል በቂ ሞያዊ ዕውቀት አለኝ ብዬ አማናለው…
*******
አንድ የፕሮጀክት ክፍያ ቴክኦፉ(Takeoff )የእያንዳንዱ የተሰራ ስራ ልኬት የሰፈረበት ሰነድ በኮንትራክተሩ ተሰርቶ ለኮንሰልታንት(ተቆጣጣሪ መሀንዲስ )ቀርቦ ትክክል መሆኑን ዲዛይኑን እና መሬት ላይ በትክክል የተሰራውንም ስራ በማገናዘብ በጥራትም፤ በመጠንም ትክክል መሆኑን እርግጠኛ ከተሆነ ብኃላ ሰመሪ (Summery sheet ) የእያንዳንዱ ስራ ዝርዝር የዋጋ መጠን በኮንትራክተሩ እና በባለቤቱ መካከል ተስማምተው በፈረሙት ህጋዊ ዶክመንት መሰረት መሰራቱን ተረጋግጦ ለኮንሰልታንቱ የበላይ ተቋጣጣሪ ሲኒዬር መሀንዲሶች ቀርቦ ከእንደገና ክሮስ-ቼክ ተደርጓ ስህተቶች ከተገኙበት ከእንደገና ወደታች ተመልሶ እንዲስተካከል ይደረግና እርግጠኛ ከተሆነ ቡኃላ Payment Certifecet ይሰራለትና በደብዳቤ ከኮንሰልታንቱ ለፕሮጀክቱ ባለቤት ይላካል.. የፕሮጀክቱ ባለቤትም ከመክፈሉ በፊት በራሱ መሀንዲሶች ቢያንስ ሰመሪውንና ሰርተፍኬቱን በራሱ መሀንዲሶች አረጋግጦ ይሄ ተሰርቶ የተላከልኝ የክፍያ ሰነድ ከተሰራልኝ ስራ ጋር ሳስተያየው ትክክል ነውና የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን እከሌ ለተባለው ኮንትራክተር ይከፈለው ብሎ ለፋይናንስ ክፍል ሸኚ ደብዳቤ ይፅፋና ከሙሉ ሰነዶች ጋር በዋናነት ክፍያውን ለሚፈፅሙ የፋይናንስ ክፍል በግልባጭ ኮንትራክተሩን ጨምሮ ለሚመለከታቸው ተቆጣጣሪ መስሪያ ቤቶች ሁሉ ይላካል..
ይሄ የመጨረሻው ክፍያው ይከፈለው የሚለው ደብዳቤ የሚፈረመው በባለቤቱ ስራ አስኪያጅ ማለትም የኢንጂነር ስመኘውን ወንበር በያዙ ሰዎች ነው….(የተለየ እኔ የማላውቀው ከሞያ ያፈነገጠ በፓለቲካ ውሳኔ የተዘረጋ አሰራር ከሌለው በስተቀር)

*******
እዚህ ላይ አንዳንዴ ከመጀመሪያ ቅድመ ክፍያ በተጨማሪ መሀል ላይ ኮንትራክተሩ የገንዘብ ችግር ካጋጠመው እና ያ ደግሞ በፕሮጀክቱ ፍጥነትና የስራ አፈፃፀም ላይ ችግር እንደሚያመጣ ሲታመንበት ኮንትራክተሩ ስራውን ሳይሰራም በብድር መልክ ለኮንትራክተር ገንዘብ እንዲከፈለው የሚፈቅድ አሰራር አለ….

(አብዛኛው ለሜቴክ የተከፈለ የባከ ብር በዚህ መንገድ የወጣ ይመስለኛል)ይሄም ቢሆን ያ ብድር አስፈላጊ መሆኑንና ኮንትራክተሩ ገንዘቡን ወዲያውኑ ስራው ላይ ያውለዋል የሚል ሙሉ እምነት ስራ አስኪያጁ ሲኖረውና ያንንም በፊርማው ሲያረጋግጥ ብቻ ነው ፋይናንሶች ክፍያውን ሊያከናውኑ የሚችሉት፡፡ (በመጀመሪያው መንገድ ኮንሰልታንቱ ዋና ተጠያቂ ሲሆን በተዋረድ ወደ ዋና ስራ-አስኪያጅ ይመጣል…በሁለተኛው መንገድ የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ዋና ተጠያቂ ይሆናል)
በአጠቃላይ በዚህም አለ በዚያ ዋናው ስራ-አስኪጅ ወይም እሱ ፍቃድ ላይ ቢሆን እንኳን በህጋዊ መልክ የወከለው ሰው ሳይፈርምበት ከፋይናንስ ወጥቶ ለማንም የሚከፈል ገንዘብ መኖሩን እጠራጠራለው፡፡

****
እና በክፍያ ጊዜ ህጋዊ ባይሆንም ሁለት እና ሶስት ፐርሰንት ዝቅም ከፍም ሊል የሚችልበት አጋጣሚ ብዙ ነው…ይሄንን ምን አልባት ቀጥታ ተቆጣጣሪ መሀንዲሱ ብቻ የሚያውቀው ይሆናል፡፡ በስራ-አስኪያጅ ደረጃ ለማወቅ እያንዳንዱን ቴክ ሆፍ ቼክ ምድረግ ስለሚጠይቅ ያን ለማድረግ ደግሞ ጊዜውም ኃላፊነቱም የእሱ ስላልሆነ ለዛ ስራአስኪያጅን ተጠያቂ ማድረግ ይከብዳል…እኔም እነደዛ ገጥሞኝ ያውቃልና…፡፡

*****
ብዙ ጊዜ ግን የተሰራው ስራ የሚበልጥበት ዕድሉ ነው በጣም ሰፊ ፡፡ምክንያም በሂደት ላይ ባለ ፕሮጀክት ክፍያ በኮንትራክተሩ ተጠይቆ በየደረጃው ባሉ መሀንዲሶች ተረጋግጦ ክፍያ ደራጃ እስኪደርስ በርካታ ቀናቶች ይወስዳሉ..በዛ ቀናት ውስጥ ደግሞ ስራው በፊት ከነበረው ተጨማሪ ስራዎች(በክፍያ ያልተካተቱ) እንደሚሰሩ ባለሞያም ያልሆነ ሰው በእርግጠኝነት መገመት አያቅተውም ….

******
እና ወደ ኢንጂነር ስመኘው ጉዳይ ስንመለስ በተለይ ለሜቴክ ተከፈለ የሚባለው ክፍያ ከስራው በእጥፍ ፐርሰንት የበለጠ ነው፡፡አቶ ስመኘው ደግሞ ዝም ብሎ የፓለቲካ ሹመኛ ስራ አስኪያጅ ሳይሆን ሲኒዬር እኒጂነር ነው..ይሄንን ሁሉ ብር ባለሞያዎች ሰርተው ያስተላለፉለትን ባለማወቅ ተሸውዶ በመፈረም ገንዘቡ እንዲከፈላቸው አደረገ ብዬ አላስብም…ምን አልባት ፖለቲካዊ ጫና አድርገውበት ሊሆን ይችላል….አስፈራርተውት ነው ሊባል ይችላል፡፡እንዴት አንድ ልምድ ያለው መሀንዲስ ይሄንን ያህል የሀገር ብር ባልተሰራ ስራ ላይ ፊርማውን አኑሮ ዘራፊዎች እጅ እንዲገባ ያደርጋል….?ለወራት ባስብም መልሱ ሊመጣልኝ ያልቻለም….::

ጫናው እና ማስፈራሪያው በዝቶበት ከሆነ እንኳን ስራውን መልቀቅ ይችል ነበር…. ለቅቄ አያኖሩኝም ካለ ከሀገር ተሰዶ መውጣት ይችል ነበር..ያም ካልተቻለው አሁን ያደረገውን ማድረግ ይችል ነበር…. እንሱ በቦታው ሌላ ሰው መድበው ብሩን መብላታቸው አይቀርም ብንል እንኳን እሱ ግን ከህሊናም ሆነ ከታሪክ ተጠያቂነት ይድን ነበር እላለው፡፡

****
ሜቼስ ማለትና መገመት ቀላል ነው፡፡ እሱ በሕይወት ኖሮ የነበረበትን እና የሆነውን ነገር በአንደበቱ ቢነግረን እኛንም ከመላምት ይገላግለን ነበር፡፡ ቢያንስ አሁን ከበተናቸው ሰባት ፖስታዎች አንዱ እንኳን እንዴት ስለእነደዚህ አይነት ነገር መራጃ አይኖረውም…?፡፡

ብዙ ከምናውቀውም ከምንገምታውም የረቀቀ እና የጠለቀ ሚስጥር ከጀርባ ያለ ይመስለኛል….. ይሄው ነው የተሰማኝ፡፡

LEAVE A REPLY