በካርቶን የታሸገ 3 ሚሊየን 5መቶ ሺህ የኢትዮጵያ ብር እና 61400 የአሜሪካ ዶላር...

በካርቶን የታሸገ 3 ሚሊየን 5መቶ ሺህ የኢትዮጵያ ብር እና 61400 የአሜሪካ ዶላር ተያዘ

/ጌጡ ተመስገን/

የከተማችን አዲስ አበባ የጥቁር ገበያ በርካታ ቁጥር ያላቸውን የገንዘብ ኖቶች እንደሚያንቀሳቅስ እያየን ነው፡፡

የ2010 ዓ/ም ማጠቃለያና የአዲሱ ዓመት መባቻ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥቆማዎች ይደርሳሉ፤

የቻይና ዜግነት ያላቸው ሁለት ግለሰቦች ከቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ማታ ማታ በካርቶን የታሸጉ ብሮች እንደሚወጡ፤ ፖሊስ ጥብቅ ክትትል አድርጓል፤

ከአስራ አምስት ቀን በላይ የፈጀ፤ ነሀሴ 28 ቀን 2010 ዓ/ም መነሻውን ከቦሌ ሻላ ያደረገው ፕራዶ መኪና ወደ ቦሌ ሩዋንዳ ጉዞ ያደርጋል፤

የኮሚሽኑ የክትትልና ኦፕሬሽን ክፍል አባላት መኪናዋን በቅርብ ርቀት መከታተል ይጀምራሉ፤

ቦሌ ሩዋንዳ ከአንድ ሰዋራ ቦታ ይደርሳል፤

ከአንድ ነጭ ዶልፊን መኪና ጋር ይገናኛሉ፤

በካርቶን የታሸጉት የገንዘብ ኖቶች ወደ ሌላኛው መኪና ሲሸጋገሩ በክትትል ቡድኑ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ይደረጋል፤

ገንዘቡም 3 ሚሊየን 5 መቶ ሺህ የኢትዮጵያ ብር እና 61400 የአሜሪካ ዶላር ነበር፡፡

ሁለቱ የቻይና ዜጎች ከአንድ ኢትዮጵያዊ ጋር ተይዘዋል፤ ሰዓቱ ምሽት ስለነበር ተጠርጣሪዎቹ ለፖሊስ አባላቱ 2000000.00 ( ሁለት ሚሊየን ) ብር ሰጥተናችሁ ልቀቁን ሲሉም ተማፅነው ነበር፡፡

የክትትልና ኦፕሬሽን ክፍሉ አባላት ቀጥታ ጉዳዩን ለኃላፊዎች በመንገር ከእነ ኤግዚቢቱ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውለዋል፡፡

አሁንም ወደ ፊትም ለቆሙለት ህዝባዊ ዓላማ እንደሚተጉም ተናግረዋል፡፡

LEAVE A REPLY