ጠ/ሚትር አቢይ በዳቮስ፣ ስዊዘርላንድ ያደረጉት ንግግር የተወሰደ | ጌጡ ተመስገን

ጠ/ሚትር አቢይ በዳቮስ፣ ስዊዘርላንድ ያደረጉት ንግግር የተወሰደ | ጌጡ ተመስገን

እየተካሄደ ባለው የዓለም የኢኮኖሚ ጉባኤ ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች

• በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ለውጥ መደመር በተሰኘ ፍልስፍና ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

• ፍልስፍናው በ3 ምሰሶዎች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

• የመጀመሪያው ዲሞክራሲን ማስፋፋት ሲሆን በዚህም ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች ከመፍታት ጀምሮ በርካታ ገንቢ እርምጃዎችን ወስደናል፡፡

• በአገሪቱ ማራሚያ ቤት በአሁኑ ጊዜ አንድም የታሰረ ጋዜጠኛ የለም፡፡

• በወሰድናቸው የለውጥ እርምጃዎች ምክንያት ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድም የፖለቲካ እስረኛ የለም፡፡

• የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ የነበሩትን ጨምሮ በርካታ ተቃዋሚዎች አገር ቤት ገብተዋል፡፡

• በአገሪቱ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ተደርጓል፡፡

• ባለፉት 9 ወራት በሺዎች የሚቆጠሩ ታራሚዎች ከማራሚያ ቤት ተለቀዋል፡፡

• ሁለተኛው ኢኮኖሚን ማበልጸግ ሲሆን በዚህ ሂደትም የግሉን ዘርፍ በስፋት እናሳትፋለን፡፡

• የወጣቶችና ሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንሰራለን፡፡

•ኢትዮ ቴሌኮምን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን እና ሌሎችንም የኢኮኖሚ አውታሮች ለውጭ ኢንቬስትመንት ክፍት እያደረግን ነው፡፡

• የምህረት አዋጅን የመሰሉ ሕጎችን አውጥተን አሳሪ ህጎችን እየቀየርን ነው

• ሴቶችን በ50 በመቶ በውሳኔ ሰጪነት በማሳተፍ ላይ እንገኛለን፡፡

• የመከላከያ ሚኒስቴር፣ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት፣ በቅርቡ የተቋቋመ የሰላም ሚኒስቴርና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛና ሌሎች ቁልፍ ቦታዎች በሴቶች እንዲያዙ ተደርጓል፡፡

• የኢትዮጵያ ለውጥ በተቋማዊ እና የሕግ ማሻሻያዎች የታገዘ ነው፡፡

• ቀደም ሲል ለውጭ ባለሃብቶች ዝግ የነበሩ የኢኮኖሚ ዘርፎችን በመክፈት ላይ እንገኛለን፡፡

• ሶስተኛው ምሰሶ ቀጣናዊ ውህደት ሲሆን ይህም ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ብቻ ሳይሆን ሰላምን ጭምር እንደሚያረጋግጥ እናምናለን፡፡

• ኢትዮጵያ ትልቅ ራዕይ ሰንቃ በለውጥ ላይ የምትገኝ አገር ናት፡፡

• ችግሮች ቢኖሩም ህዝቡ ከጎኔ እስካለ ድረስ የምፈራው ነገር የለም፡፡

• ይህ ለውጥ ወደ አገራችን ትልቅ ካፒታል ይዞልን ይመጣል ብለን እናምናለን፡፡

• እስክ 2021 የአገሪቱ ኢኮኖሚ ከ8 በመቶ በላይ ዕድገት እያስመዘገበ እንደሚቀጥል ይጠበቃል፡፡

LEAVE A REPLY