ዘውጌ ዝም ስትለው አናትህ ላይ ይወጣል | አቤል ዋበላ – አዲስ አበባ

ዘውጌ ዝም ስትለው አናትህ ላይ ይወጣል | አቤል ዋበላ – አዲስ አበባ

ስለዚህ አንዳንድ ፋክቶችን ማስታወስ ወደድኩኝ፡፡ የኦሪት ዘዳግም አይነት ማስታወሻ ናት፡፡ ለማያውቅ እንዲማርበት ለዘነጋው ደግሞ ማስታወሻ ይሆናል፡፡ የዘውጌ ልሂቅ ከግል ጥቅም ውጪ በታሪክ ከወያኔ ጋር ጸብ ሆኖ አያውቅም፡፡

ወያኔ በስልጣን ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ብልግናውን እንዲተው በቻይነት መንፈስ ሲታገለው ሲመክረው የኖረው የኢትዮጵያ ልሂቅ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሲባል የኢትዮጵያ ነው፤ ልዩነት የለም፡፡

በአንጻሩ የዘውጌ ልሂቅ ለስልጣን፣ ለዘረፋ፣ ለግል ጥቅም ወያኔን ሲያገልግል ነው የኖረው፡፡ ኩርፊያው ህዝብ ለምን ተበደለ ሳይሆን እኔ ለምን እንዳሻኝ አለመዘበርኩም የሚል ነበር፡፡

የዘውጌ ልሂቅ ሽምቅ ተዋጊውን ጨምሮ ርዕይ የሌለው ከራሱ አንድ ጋት አርቆ የማያስብ፣ የጂኦፖለቲክስ ግንዛቤ የሌለው አራሙቻ ነበር፡፡

ኢትዮጵያዊ ልሂቅ ኃይሉን አሰባስቦ፣ ህዝብ እንዳይጎዳ፣ ሀገር እንዳይፈርስ በኃላፊነት መንፈስ ምርጫ 97 ላይ ወያኔን ዘርሮት ነበር፡፡ በመሣሪያ ኃይል እና ከትግራይ ባልሆኑ ሌሎች ልሂቆች ድጋፍ ከሞት አፋፍ ተርፏል፡፡

ወያኔም ትምህርት ወስዳ በአፋኝ ህግ ቀንበሩን ብታከብደውም እነብርቱካን፣ እነእስክንድር፣ እነአንዷለም ራሳቸውን ሰውተው በዚህ ሀገር የነጻነት መንፈስ ተቀብሮ እንዳይቀር አድርገዋል፡፡ ብዙዎች የእነርሱን ፈለግተከተለው በሀገርም፣ በውጭም በዱርም ለሰውነት ክብር ዋጋ ስለከፈሉ የነጻነት ቀን ቀረበች፡፡

መለስ ዜናዊም በአበበ ገላው ቁርጠኛ እና የተጠና ተቃውሞ ድባቅ ተመታ፡፡ በወቅቱ የአበበ ንግግር የሰውዬው ጤና ላይ የፈጠረው ተጽእኖ ሰፊ ክርክር ተደርጎበታል፡፡ በረከት ስምኦን በስልት ያስራጨውን ፕሮፖጋንዳ ወደጎን ብናደርገው አበበ ጭራቁን ሰውዬ ለማሰናበት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

በመቀጠል የኢትዮጵያ ሙስሊም መብቱን ለመጠየቅ ወጥቶ በሰላማዊ ትግል የወያኔ እና ተለጣፊ ልሂቃንን የሚመሩት ስርዓትን በእጅጉ ፈተነው፡፡ አቡበከር ለደሴ ሙስሊም ሳይል፣ አህመዲን ለጅማ/ኦሮሞ ሙስሊም ሳይል፣ በድሩ ለጎንደር ሙስሊም ሳይል፣ ነገር ግን በአንድነት የኢትዮጵያ ሙስሊም ሰብዓዊም ሆነ ሐይማኖታዊ መብት ይገባዋል ብለው በአንድ ጥላ ታገሉ፡፡

ማኀበራዊ ሚዲያ የመንግሥትን መረጃን በሞኖፖል የማሰራጨት መብት ሸርፎ ለዜጎች እንደሰጠው ለኢትዮጵያውያን የነጻነት ትግል እርዳታን አበርክቷል፡፡

ከዚያ በኋላ ተለጣፊ ዘውጌ የራሱን ጥቅም የበለጠ ለማደራጀት ተዳክማ በቅርብ ያያት ወያኔ ላይ የወጣት ተቃውሞን አነሳሳ፡፡ በአዳማ እና በጎንደር ታሪክ እስኪቀየር ድረስ ከመንደር ወመኔነት የዘለለ እንቅስቃሴ አልነበረም፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊባል በሚችል መልኩ የዘውጌ ልሂቅ በጎን ከማጉረምረም ወጥቶ የኢትዮጵያ ሊሂቅ በኃላፊነት ወደሚያቀነቅነው ኢትዮጵያዊነት መጣ፡፡ ወያኔም ወደ መቀለ አፈገፈገ፡፡ Ethiopians won tribally organized nihilist elites. We won. We are crippled victors.

ዐቢይ አሕመድ ጋር የደረስነው እንዲህ ነው ለማለት ነው፡፡

LEAVE A REPLY