ከታሪክ ማህደር – ኮሪያ | መስፍን ማሞ ተሰማ

ከታሪክ ማህደር – ኮሪያ | መስፍን ማሞ ተሰማ

ሠላም ለናን ይሁን!

መቼም የኢትዮጵያ ታሪክ እንደ ሳይንስ የሚያመራምር እንደድንቅና ውስብስብ ልቦለድ ታሪክ ውሉን ለማግኘት ታሪኩየሚመስጥ በዚህች ምድር ላይ ሌላ መሰል ታሪክ ያለው ሀገርይኖር ይሆን? በ1950ዎቹ (እአአ) ኢትዮጵያ የምትደዳደረውበዘውዳዊው (ሞናርኪ) ሥርዐት ኢኮኖሚያዊ መሰረቷምፊውዳላዊያም ሆኖ ከራሷ ጂኦግራፊያዊ ክልል አልፋአህጉራዊና ዓለም ዓቀፋዊ ተቀባይነትና ግዝፈት ያላት ሀገርገራሚ ነው!!  ለማንኛውም ኮርያ እንዝመት

ዘመኑ 1950 እስ 1953 (እአአ) ነውየኮርያ ጦርነትበኪም ኢል ሱንግ የምትመራዋ ሰሜን ኮርያ በሲንግማን ሪህየምትመራዋን ደቡብ ኮርያ ወረረችሰሜኖች ኮሙኒስትደቡቦች ካፒታሊስት ሥርዐት ተከታዮችከሰሜን ኮርያ ጎንቻይና እና ሶቪየት ህብረት በግንባር ቀደምትነት  ሲሰለፉከደቡብ ኮርያ ጎን ደግሞ አሜሪካና የምዕራብ ዲሞክራሲሀገራት ተሰለፉ

በዘውዳዊው የግርማዊነታቸው መንግሥት በፊውዳላዊኢኮኖሚ የምትደዳደረው ኢትዮጵያችን የተባበሩትመንግሥታት ድርጅት አባል ነበረችእነሆ ከተመድ መሥራችሀገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ኮሙኒዝምን ልትዋጋከዲሞክራሲያዊ ሀገራት ጎን ተሰለፈች። በ1951 (እአአ) ቃኘው ሻለቃ ጦር ወደ ኮርያ ዘመተ

እነሆም በሩቅ ምሥራቁ ጉደኛ ጦርነት ተዓምረኛ ተዋጊዎችየተባሉት የቃኘው ሻለቃ ጦር የኢትዮጵያን የጀግኖች ማማነትበደማቅ የደም ቀለም በዓለም ዐውደ ውጊያ አስፃፈ

ቃኘው ሻለቃ ጦር በዚያ የጦር ዐውድ በተለያዩ ግንባሮች 238 (ሁለት መቶ ሰላሳ ስምንት) ጊዜ ከሰሜኖቹየተባበበረው የኮሙኒስት ጦር ጋር ተዋግቷልአስደናቂውና ኮሙኒስቱንም ሆነ ዲሞክራሲውን ግንባርያስደመመው ቃኘው በየትኛውም የጦር ዐውድ ተሸንፎአለማወቁ ነው!!

በኮርያ ጦርነት ኢትዮጵያ ከስድስት ሺህ በላይ ሠራዊትያሰለፈች ሲሆን በጦርነቱም 121 (አንድ መቶ ሃያ አንድ) የጦርአባላቷን ህይወት ስትገብር 536 (አምስት መቶ ሰላሳ ስድስት) ቁስለኞች ሆነውባታል

በጦርነቱ ማብቂያ ከአሜሪካ ወገን ሆነው ከተዋጉት ሃያአንድ ሀገራት መካከል ሁሉም በኮሙኒስቶች እጅ የወደቁምርኮኛ እስረኞች ሲኖሯቸው አንድም ምርኮኛ ያልተያዘባትብቸኛ ሀገር ኢትዮጵያ ናት አኩሪ ነው!! ለዚህም ነበር  የዚያዘመን የጥበብ ሰዎች የኮርያን ዘማቾች ሲያወድሱ<አጨደው ከመረው ወቃው እንደ ገብስየኢትዮጵያ አርበኛኮርያ ድረስ> በማለት የዘመሩላቸው

አዎ! <ሰኔና ሰኞ> ተጋጠሙና በለስ የቀናው ወያኔ ኢህአዴግበ1983 አዲስ አበባን ሲቆጣጠር <የጠላት ጦር> በማለትበትኖ ለረሀብና ለልመና የዳረገው ይህንን የኢትዮጵያ ጦርነበር

ኢትዮጵያ ዛሬም በተፈጠሩና በሚፈጠሩ ጀግኖች ልጆቿበነፃነትበአንድነትና በክብር ትኖራለች!

በታኞች ራሳቸው ይበተናሉ! ኢትዮጵያ መቼም አትበተንም!!

የካቲት 2011 ዓ/ም (ፌብሩዋሪ 2019)

ሲድኒ አውስትራሊያ

LEAVE A REPLY