የእነ አቶ በረከት የኢንተርኔት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

የእነ አቶ በረከት የኢንተርኔት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና | እነ በረከት ስምዖን የጠየቁት የስልክና የኢንተርኔት ጥያቄ የባህርዳር ከፍተኛ ፍርድ በተ ውድቅ አደረገ።

የቀድሞ የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ኃላፊና ከፍተኛ ባለስልጣን አቶ ታደሰ ካሣ እና በመጥፋቱ የሚታወቀው የመለስ ዜናዊ አስተዳደር ዋነኛ ፈላጭ ቆራጭ በረከት ስምኦን ያቀረቡትን የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት ጥያቄ ውድቅ ያደረገው የባህርዳር የከፍተኛ ፍርድቤት እንደማንኛውም እስረኛ የሚሰጣቸው አገልግሎት እንዳይገደል ትዕዛዝ አስተላልፏል።

 ለዘመናት በርካቶችን በፍርደ ገምድል አገዛዝ ሲያስሩ ብቻ ሳይሆን በቀጭን የወረቀተና የስልክ ትዕዛዝ ሲያስሩና ሳያሰውሩ የነበሩ ባለስልጣናት የኢንተርኔትና እና የስልክ ወደ እስር ቤት ይገባልን ጥያቄ መነሻነት ብዙዎችን ያነጋገረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የሰጠው እንደማናቸውም ታራሚዎች የሚገባቸውን አገልግሎት እንዲያገኙ መፍቀዱ የፍትህ ስርአቱ መስመር የሚያዝበት አመልካች ነው ሲሉ አስተያየት ሰጨወቸ ገለጸዋል።

እነ አቶ በረከት ለቀጣይ የፍርድ ቤት ውሎ ለመጋቢት 2 /2011 ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተቀጥረዋል።

 

LEAVE A REPLY