ውሃ ለመቆጠብ ቢራ ጠጣ | በማሕሙድ እንድሪስ

ውሃ ለመቆጠብ ቢራ ጠጣ | በማሕሙድ እንድሪስ

ጠብ
ጠብ
ጠብ
ጠብ
ውሀን ለመቆጠብ 
ቢራ ጠጣ የሚል ማስታወቂያ አይቼ
ናላየ እስከሚዞር
ጠጥቼ ተጥቼ
ተግቼ ተግቼ
እየተንገዳገድኩ እየተለፋደድኩ ከቤቴ ገብቼ
ረስቼው ተኛሁ
በሰከረ መንፈስ እጄን ለመታጠብ ቧንቧየን ከፍቼ
በጥዋት ስነቃ

በስም የለሽ ባህር
ክፍሌ ተጥለቅልቃ
አየ ማስታወቂያ
አይ ውሀ ቁጠባ …… ወይ ውሀ ጥበቃ !!

LEAVE A REPLY