ዶ/ር አምባቸው መኮንን አዴፓን  በመምራት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተመረጡ

ዶ/ር አምባቸው መኮንን አዴፓን  በመምራት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተመረጡ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ዶክተር አምባቸው አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን በመተካት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው መሾማቸው ታወቀ።

ዶክተር አምባቸው በአዴፓ 12ኛ መደበኛ ጉባኤው በራሳቸው ፍቃድ ስልጣናቸውን የለቀቁትን አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን በመተካት ክልሉን ለማስተዳደር በዘሬው ዕለት ቃለ መሀላ በመፈፀም ሀላፊነታቸውን ተረክበዋል።

ክልሉን በርዕሰ መስተዳድርነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በዛሬው እለት መልቀቂያ አስገብተው መልቀቂያቸው ተቀባይነት በመገኘቱ ነው ዶክተር አምባቸው መኮንንን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ የሾማቸው።

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት አማካሪ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር አምባቸው ክልሉን ለአምስት አመታት የመሩትን አቶ ገዱን በመተካት ወደተሻለ ደረጃ ከፍ ያደርጉታል ተብሎ ታምኖባቸዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አባይ በባህርዳር በተካሄደው የአዴፖ ስብሰባ መዝጊያ ስነስርአት ላይ በመገኘት የዶክተር አምባቸውን መምረጥ አስመልክተው ሲናገሩ “ዶክተር አምባቸው በአምቦና በመቀሌ ጉዞ በማድረግ የሰላም ተልእኮውን እንደሚወጡ እተማመናለሁ ብለዋል።

 

LEAVE A REPLY