የሊቅ ዐቢይ አስቸጋሪ ምርጫ። የግል አስተያየት | ፕሮፍ. ኀይሌ ላሬቦ

የሊቅ ዐቢይ አስቸጋሪ ምርጫ። የግል አስተያየት | ፕሮፍ. ኀይሌ ላሬቦ

የሊቅ ዐቢይና የነለማ ቡድን ተብሎ የሚጠራውን አንጃ ደጋፊዎች፣ አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊነትን የሚያራምዱ የአንድነት ጐራ ናቸው ብል ስሕተት አይመስለኝም። የነለማ ቡድን ግን ሁሉም የኢሕአዴግ አባላት ናቸው። የዚህ ቡድን ደጋፊዎች ያልተገነዘቡት ነገር ቢኖር፣ ኢትዮጵያዊነትና ኢሕአዴግ በመልካም እንተርጉም ካልን ሆድና ጀርባ፣ በመጥፎ እናስመስል ከተባለ ደግሞ እባብና ርግብ መሆናቸውን ነው። ምንም ብንመኝ፣ ሁለቱ በፍጹም አብረው ሊኖሩም ሊደመሩም አይችሉም። “መደመር” የሚለው የሊቅ ዐቢይ ፈሊጥ ለነዚህ ሁለቱ በፍጹም አይሠራም። ባንድ አልጋ እንኳን ቢተኙ፣ ሕልማቸው ተጻራሪ ነው። ኢትዮጵያዊነት ዘመን ተሻጋሪና ለማንም የማይበገር፣ ሌላውን ጐረቤቱንም ሆነ አካባቢውን እያሰፋና እያቀፈ የሚሄድ፣ እንከን የለሽ ስብጥርና ጒንጒን ማንነት ነው። ኢትዮጵያም ሆነ ኢትዮጵያዊነት የሚታወቁት በተፈጥሯቸው ማንንም አስተናጋጅና ዐቃፊ በመሆናቸው ነው።

የኢትዮጵያዊነት ዐቃፊነት፣ ኢትዮጵያ ከተባለው ግዙፍ ምድር መጥቆ ወሰኑንና ድንበሩን ዐልፎ፣ ለሌላውም ዓለምና ሕዝብ ተትረፍርፏል። የዓለም፣ በተለይም ጭቁንና ጥቊር፣ ሕዝብ በምዕራባውያን መብቱ ተጨፍልቆ ይኖር በነበረበት ወቅት፣ የነፃነትና የእኩልነት ትግሉን ድምፅ፣ በያለበት ሲያክላላው፣ ሲያስተጋባው፣ ሲያክለውና ሲያንረው ቈይቶ፤ የኋላ ኋላ ግቡን ለመምታት የበቃው
በኢትዮጵያዊነት ዙርያ በመሰለፍና በመሰባሰብ ነው። ኢሕአዴግ በተቃራኒ በባሕርዩ ከፋፋይ፣ በልዩነት ላይ ያተኰረ፣ በጥላቻ መሠረት ላይ የተካበ፣ የጐጠኞችና የአገር ከሓጂዎች ጥርቅማጥርቅም ነው ማለት ይቻላል። ብዙዎች የሚሳሳቱት ኢሕአዴግን እንደፖለቲካ ድርጅት እያዩ ነው። ኢሕአዴግ የተፈጠረው የኢትዮጵያን ጥፋት ከኋላ ሁነው ይሸርቡ በነበሩት በውጭ ኀይሎች ሤራና ምክር ሲሆን፣ በእጁ ጠፍጥፎት ህልውና የሰጠው ግን፣ የታላቂቷ ትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት ሕዝባዊ ሓርነት ወያኔ (ሕወአት) ነው። ሕወአት በኢትዮጵያ ጥንታዊነትና ታላቅነት አያምንም።

ለሕወአት ከራሱ ዐልፎ ዓለምን ያደነቀው፣ የመላው ዓለም ጥቊርና ጭቁን ሕዝብ የሚኰራበት፣ የኢትዮጵያ ታሪክ የሚጀምረው፣ የ’አማራ’ ንጉሥ ብሎ ከሚጠራው ከአፄ ምኒልክ ዳግማዊ ነው። የቀረው የሰካራሞቹ፣ የባለምትሐቶቹና የባለአስማቶቹ ደብተሮች የፈጠራ ሐተታ ነው። ከስድስት ሺ ዓመታት በላይ ያስቈጠረውን፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ የርስበርስ መወላለድ፣ በአምቻና በጋብቻ መተሳሰር፣ በባህልና በሀብት መሰበጣጠር፣ በቋንቋና በሃይማኖት መወራረስ፣ ሕወአት አጥብቆ ይክዳል። በሕወአት ትርክት መሠረት፣ ኢትዮጵያ “አንድ አማራ በተባለ ጨቋኝ ብሔረሰብ ወረራ የተቋቋመች፣ መቶ ዓመት የማይሞላ ታሪክ ያላት አገር ናት።

በተጨማሪ፤ ኢትዮጵያ፣ አማራው በሁሉም ዘርፍ የበላይነቱን ይዞ ይገዛት የነበረ፣ አማራ ያልሆነው ብሔረሰብ ግን፣ በግፍና በገፍ የሚማቅባት እስር ቤት ናት።” የሕወአት ሕልምና ምኞት ይህችን ኢትዮጵያን አፍርሶ፣ ጨቋኝና ተጨቋኝ በሌለበት መልኩ፣ በድርጅቱ አምሳል በአዲስ መልክ መገንባት ነው። ይኸንን ግብ
ለመምታት የሕወአት ዋና ዓላማ ‘አማራን’ ማጥፋት ነው። በሠለጠነ ቋንቋ በመተርጐም ሕወአቶች ተልእኳቸውን በመሪያቸው ስም “የመለስ ራእይ” ይሉታል። የሕወኣት ከፍተኞች መሪዎቻቸው የድርጅታቸውን ዓላማ ለማሳካት እንዲያመችላቸው ሲሉ፣ የአማርኛ ተናጋሪውን ሰብኣዊነት ለመካድ በየጊዜው ተናገሩት ተብለው በየቦታው የሚጠቀሱትን ንግግሮች ከዚህ በታች አስቀምጫለሁ። ፍርዱንና ኂሱን ለአንባቢው ልተወውና ወደዋናው ጉዳይ ልለፍ።

ኢሕአዴግ፣ ሕወአት በራሱ ኀይል ብቻ ግቡን ለመምታት ስለሚሳነው፣ ድርጊቱን እግብር ለማዋል ታስቦ የተፈጠረ ግንባር ነው። በተሻለ አገላለጥ የሕወአት ሥራ አስፈጻሚ አካል ቢባል ይቀላል። ኢሕአዴግ በሕወአት ተሸንሽኖ በተሰጠው ክልል፣ አማርኛ ተናጋሪውን በቋንቋ መስፈርት ብቻ እየፈረጀ፣ “ነፍጠኛ”፣ “የምኒልክ ሰፋሪ”፣ “ጨቋኝ” ወይንም “የጨቋኝ መደብ” እያለ በማሳበብ፣ ልሕቅና ደቂቅ፣ ወንድና ሴት፣ ሕፃንና ሽማግሌ፣ ነፍሰጡርና አሮጊት ሳይለይ በጅምላ ልዩልዩ ስልትና መሣርያ በመጠቀም ሲገድል፣ ሲጨፈጭፍ፣ ሀብቱንና ንብረቱን ሲነጥቅ፣ ሲያፈናቅል ኑሯል። ልክ በአውሮጳ ከጀርመን ቊጥጥር ሥር
የነበሩ ግዛቶች በናዚዎች የተዛባና የሐሰት ስብከት ተመርተው፣ በአይሁዶች ላይ የፈጸሙትን ግፍ፣ ኢሕአዴግም፣ በአማርኛ ተናጋሪው ሕዝብ ላይ ከዚያ የማይተናነስ ኢሰብኣዊ ጭካኔና የዘር ማጽዳት ተግባር እንደፈጸሙ መታወቅ ይገባል። ስለዚህ በሰብእናውም ሆነ በጠባዩ ኢሕአዴግ በአውሮጳ ከታየውና ዓለምን ለአሰቃቂ ከፍተኛ ዕልቂት ከዳረጉት ከመንታው ፋሽስትና ናዚ አይለይም።
ሕወኣት ለኢሕአዴግ አባልነት ከፈለፈላቸው ዋናውና ከፍተኛ ሚና ከተጫወቱት አንዱ ትናንትና የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት [ኦሕዴድ] በመባል፣ ዛሬ ደግሞ የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ስም የሚጠራው ነው።

ኦሕዴድ ኦሮሞኛ ተናጋሪ ብሔረሰብ ከቀረው የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ለዘመናት
በመወላለድ፣ ባህልና ቋንቋ በመወራረስ፣ ድር ማጉ ኢትዮጵያዊ መሆኑንና፣ አብዛኛው አሁን ላለበት አካባቢ (አዲስ አበባን ጭምር) መጤና አዲስ ሰፋሪ መሆኑን የረሳ ይመስላል። ከደቡብ ከኬንያ ጠረፍ ተነሥቶ እስከመሃል ኢትዮጵያ ያለውን ሰፋፊ መሬት ይዞ የሚገኘው፣ ከፊቱ ያለውን እያጠፋ፣ እንደሀዲያ፣ ከምባታና ጉራጌ የመሳሰለውን ኀይለኛውን ብሔረሰብ ደግሞ አልፎት እየሄደ፣ ጸጥለጥ ብለው የገበሩለትን ብሔረሰቦች ግን ጉዲፈቻ፣ሞጋሳ [ሞገሳ]፣ ገበር የተባሉ ሥርዐቶቹን በመጠቀም፣ ባህላቸውንና ቋንቋቸውን ደፍጥጦ፣ ሰብእናቸውን ጨፍልቆ፣ በኦሮሞነት እንዳጠመቃቸውና፣ በሁለተኛ ደረጃ ዜግነት ይገዛቸው እንደነበረ ዘንግቷል ማለት ይቻላል። ኦሕዴድም (እንደሱም “የኦሮሞ ሕዝብ ወኪልና ነፃ አውጪ” ነኝ ብሎ ራሱን በራሱ የሾመው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ))፣ እወክላለሁ ያለው ሕዝብ ራሱ “የሉባ” ሰፋሪ ሁኖ እያለ፣ አማርኛ ተናጋሪውን፣ ሕግና ሥርዐት አስጠባቂውን (በዱር በገደል ለኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት የሞተውን ኦሮሞን ጭምር) “መጤ”፣ “ነፍጠኛ”፣ “የምኒልክ ሰፋሪ” እያለ በመብራት እየፈለገ፣ በጥይት እየረሽነ፣ ከነሕይወቱ እየቀበረ፣ ለዘመናት ከኖረበት ቤቱና አካባቢው እያፈናቀለ፣ ከፍተኛ ግፍና በደል እንደፈጸመ ይነገርለታል ብቻ ሳይሆን፣ ሁለቱም አሁንም ቢሆን በዚህ ተግባር እንደተሰማሩ ናቸው።

ሊቅ ዐቢይ እንግዴህ የዚህ ግፈኛ ድርጅት ማለትም የኦዴፓ አባል ብቻ ሳይሆን ሊቀመንበሩም ነው። ግን ኢትዮጵያዊነትን፣ አንድነትንና ፍቅርን በመስበኩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጫፍ እስከጫፍ በየሄደበት በሆሆታና በእልልታ ተቀብሎታል። ይሁንና የሊቅ ዐቢይ ሥራ እስካሁን ድረስ ተከታዮቹንና ደጋፊዎቹን በቃላት ከማሞኘት ዘልሎ የሄደ መስሎ አይታየኝም። በቅርቡ በአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ስብሰባ ሥነሥርዐት ላይ ባደረገው ንግግሩ፣ የኦዴፓ መሪዎች በለገጣፎና በአዲስአበባ ዙርያ፣ ጽንፈኞቹ ናቸው የተባሉት ደግሞ ወኪልና ደጋፊ አፍ ባጣው በጌዴዎ ሕዝብ ላይ፣ እየፈጸሙ ባሉት ግፍ፣ ጭፍጨፋና ፍንቀላ እስካሁን ድረስ አንዲትም ቃል ትንፍሽ አላለም። አንዱን ጐሣ በክልሌ መኖር አይገባህም ብሎ ማጽዳት የኢሕአደግ መሠረታዊ እምነቱ ስለሆነ፣ ሊቅ ዐቢይ ለነዚህ ጉዳዮች ደንታም ያለው አይመስልም።

ሊቅ ዐቢይ ብዙ ደጋፊዎች እንዳሉት ይገባኛል። ለእኔ ግን አያያዙ ገና ከመጀመርያው አልጣመኝም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ካንድ መሪ ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል ለብዙ ጊዜ ስላልሰማና፣ ቃሉ በአንድ መሪ አፍ ተደጋግሞ ሲጠራ ማየቱ በጣም ስለጠማው፣ ሊቅ ዐቢይ በየጊዜው “ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” ሲል በሚያስተጋባው ጩኸቱና ማር በተቀባ ንግግሩ የብዙዎቹን ዐይን እያሳወረ የሄደ ይመስለኛል። ይሁንና በኔ አስተያየት እስካሁን ድረስ አንድም መሠረታዊ የሆነ ለውጥ አላመጣም። ኢሕአዴግና ሕገመንግሥቱ እንዳሉ ናቸው። ይልቅስ ሊቅ ዐቢይ፣ ሕወአት ኀይል በመጠቀም እግብር ላይ ለማዋል ያልቻለውን የጐሣ የክልል ሥርዐት፣ ተቃዋሚውን በማፍዘዝና በማደንዘዝ እያጠናከረው ይገኛል ብቻ ሳይሆን በሰላማዊ መንገድ በጥብቅ ሥር እያስያዘውም ይገኛል። ደጋፊዎቹ የረሱት ነገር ቢኖር፣ ኢትዮጵያን ማሞገስ ከማንኛውም የአገር መሪ የሚጠበቅ መሆኑን ነው። እስረኞችንም መፍታት እንደትልቅ ነገር አድርጎ መቊጠሩ እጅግ
የተሳሳተ አመለካከት እንደሆነ መታወቅ ይገባል። እስረኞቹ የፈጸሙት ምንም ዐይነት ወንጀል የለም።

ይልቅስ ሰዎቹ ከመጀመርያውኑ መታሰር የማይገባቸው፣ የኢሕአዴግ የግፍና የጭካኔ ሰለባና መግለጫ ናቸው። የታሰሩትም ሊቅ ዐቢይ ራሱ አሁን የሚያሞግሳትን የኢትዮጵያን ስም ስለጠሩ፣ እየመራ ያለውን የኢሕአዴግን የጐሣ ፖለቲካ ስለተቹ ብቻ ነው። ሊቅ ዐቢይ ግን ደጋግሞ የኢትዮጵያን ስም ቢጠራም፣ አጠንክሮ እየደገፈና እያራመደ ያለው የጐሣን ፖለቲካ ነው። ሊቅ ዐቢይ ተጨማሪ ጉዱ በየጊዜው ብልጣብልጥ/ሸዋጅ ለመሆን መሞከሩ ነው። የብዙዎቹን ብሔረሰቦች መፈናቀልና መገደል እስካሁን ድረስ በሕወአት እያሳበበ ቈይቷል። የራሱ ወገን ሲያደርግም በሕወኣት ተተናኩለው ነው እስከማለትም ደርሷል። በቅርቡ የለገጣፎን ሕዝብ ያፈናቀለችው እሱ ራሱ ሊቀ መንበር ሁኖ የሚመራው የራሱ ድርጅትና ወገንና ሹም ናት። ርግጠኛ አይደለሁም እንጂ ራሱ ወይንም አቶ ለማ የሾማት ሳትሆን አትቀርም ብዬ አምናለሁ። ሊቅ ዐቢይ ስለጉዳዩ ሲጠየቅ የሰጠው መልስ፣ ካንድ ዱርዬ/ሸዋጅ እንጂ፣ በፍጹም ከአንድ ጤናማ የአገር መሪ (ያውም ለኖቤል ሽልማት ይታጭ እየተባለ ካለ) አይጠበቅም። ይኸንን በተመለከተ፣ ከሁሉም ይበልጥ የገረመኝና ማመን ያቃተኝ ድርጊቱን አለማውገዙ ብቻ ሳይሆን፣ እንደአንድ አገር መሪ ለተፈናቀሉትም ሆነ ለአፈንቃዮቹ አንድም ነገር አለማለቱና ምንስ ዐይነት እርምጃ እየተወሰደ እንዳለ አለመናገሩ ነው።

ሊቅ ዐቢይ ደጋግሞ የሚሰብክልን የመደመር ፖሊቲካ መሠረቱና ዐምዱ ፍትሕ፣ ነፃነትና እኩልነት መሆኑን የተረዳ አይመስልም። ከመንግሥት ፍቅር መጠበቅ ሞኝነት ነው። ፍትሕ፣ ነፃነትና እኩልነት ግን የመንግሥት ግዴታው ነው። እነሱ ከሌሉ መንግሥትየለምና። የሊቅ ዐቢይ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ጨዋታው በዚህ ብቻ አላበቃም። በየጊዜው የአገሩን ችግር እንዲቀርፉ ሲል የሚያቋቁማቸው ኮሚቴዎች፣ በሥራው እንዲያግዙት ሲል የመረጣቸው አጋሮቹ ሚኒስትሮች ግልጥ አድርገው ደጋግመው የሚያመለክቱት ሊቅ ዐቢይ ያከበረውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ምን ያህል የሚያላግጥበት መሆኑን ነው ብዬ አምናለሁ። ሚኒስትሮቹን ብንመለከት፣ አጋሮቹ ሳይሆኑ ከእሺ ጌታዬ ከማለት ውጭ ሌላ ፋይዳ ያላቸው ሰዎች አይመስሉም።

በየመስኩና በየአስተዳደሩ ዘርፍ ለሚታዩት ለአገሩ ችግሮች መፍትሔ እንዲያመጡ የሚመርጣቸውና የሚሾማቸው ሰዎች፣ ነፃና ገለልተኛ የሆኑ አይደሉም፤ በጉዳዩም ዕውቅና ያላቸውም ናቸው ማለት ያዳግታል። ይልቅስ ከመነሻው የችግሮቹ ጠንሳሾች፣ ፈጣሪዎችና አራማጆች ናቸው ማለቱ ይቀላል። ለይስሙላ፣ አለበለዚያም ለሽወዳና ከተጠያቂነት ለማምለጥ ካልሆነ በስተቀር፣ ማንም ጤናማና ቅንነት ያለበት ሰው፣ አገሯ ያላት የከባድ ችግሮች መፍትሔ በምንም መልክ ከነዚህ ዐይነት ሰዎች ይመጣል ብሎ እንደማያስብና እንደማይጠባበቅ ርግጠኛ ነኝ። ይኸ ዐይነቱ ፍርዴና አስተያየቴ የሊቅ ዐቢይ አማካሪዎቹን ጭምር ይመለከታል። በቅርቡ ስለአዲስ አበባ ባለቤትነት ጉዳይ ላይ ለውይይት መነሻ ሲል ስሙን ሳይገልጽ ራሱን የጠቅላይ ሚኒስቴር የሕግ አማካሪ
በማለት ለሊቅ ዐቢይ የሰጠው የኢትዮጵያ ታሪክ ግንዛቤው የሹሙን ዕውቀት የሚገልጥ ከሆነ፣ ሊቅ ዐቢይ ራሱን ያጀበው በጅሎችና በጥራዘነጠቆች መሆኑን ያመለክታል።

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ በነእንደዚህ ዐይነቶቹ ሰዎችና አማካሪዎች የተከበበና የሚመከር ከሆነ፣ እሱም ጠፍቶ ኢትዮጵያንም ሊያጠፋ ይችላል የሚል ጥብቅ እምነት አሳድሮብኛል1። በሌላው በኩል ደግሞ ሊቅ ዐቢይን ብቻ መውቀሱ ሚዛናዊነት ያጣ ፍርደገምደልነት መስሎም ይታየኛል። የአንድነት ኀይል ነን ባዮች፣ ወይንም የጐሣ ሥርዐት ይደምሰስ የሚሉ ኀይሎች ርስበርስ ከመነታረክና ቁሞ ከመመልከት በዘለለ፣ የመደራጀት ፍላጐትም ጥረትም እስካሁን ለማሳየት አልቻሉም። “ኢትዮጵያ አትጠፋም፣ ለዘላለም ትኖራለች፣ ወይንም ትኑር” ከማለት አልፎ ያሳዩት ትብብርና ተጨባጭ ተግባር የለም።

የሚጠብቁት ሊቅ ዐቢይ የጐሣንና የጐጥን ሥርዐት በተአምርም በዐዋጅም ቢሆን ገርስሶ፣ የአንድነትን መና ከሰማይ አውርዶ እንዲመግባቸው ነው፣። የትግል መንገዱንም ተአምራዊ በሆነ ኀይሉ ጠራርጎ እንዲያቀናላቸው እንጂ እንደጽንፈኞቹ አጠንክረው መታገልና በየቦታው የተበታተኑትን እንደአሸን የፈላ
ደጋፊያቸውን ባንድጋ ማሰለፍ ግዴታቸው እንደሆነ የተገነዘቡ አይመስሉም። እነሱ ራሳቸው ባንድ አፍለመናገርም ሆነ፣ የጽንፈኞቹን ድርጊት አጠንክረው ለማ ውገዝ ሲሞክሩ አልታዩም። ለምሳሌ ሌላው ቀርቶ በአዲስ አበባ ያለው ሕዝብ እንኳን፣ ጥቅሙና ህልውናው በጽንፈኞቹ እየተነካና እየተጐዳ እያለ፣ ከተማዋ 1 የሕግ አማካሪው የአዲስ አበባን ባለቤትነት በተመለከተ ለምን ታሪክ ላይ መመሥረት እንደማያስፈልግ ምክንያቱን ሲገልጥ፣ “የኢትዮጵያ ታሪክ ብለን እስከዛሬ ስንጠቀምባቸው የነበረው የአንዳንድ ብሔሮችን ገድል ብቻ የሚዘክር እንጂ፣ አብዛኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ታሪክ፣ በተለይም የኦሮሞችን ታሪክ የማይወሳ በመሆኑ ይህንን አግላይ “ታሪካዊ መረጃ” ለክርክር መርቻ ዋቢ” አድርጎ ለማቅረብ እንደማያምንበት ይናገራል። አንባቢው እንዲረዳ ያህል ላሳስብ የምወደው፣ ከማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ይበልጥ በሰፊ የተጻፈለት ብሔረሰብ ቢኖር የኦሮሞ ብቻ ነው ማለት ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ የሁሉም አገር (የምዕራባውያን ጭምር) ታሪክ የተጻፈው ለገዢው ክፍል በገዢው ክፍል ስለገዢው ክፍል እንጂ የተራው ሕዝብ አይደለም። የኢትዮጵያም ታሪክ ከዚህ የተለየ አይደለም።

ብዙ የተማረና የነቃ ኀይል ቢኖራትም፣ በሷ ላይ የሚደረገውን ደባና የተሸረበውን የጥፋት ምዝበራ የሚቋቋምና የሚመክት ኀይል ለማደራጀት አልቻለም። ታዲያ ጽንፈኞቹ ቢያይሉበትና ፍላጎታቸውን ለማርካት ለስለስ ቢል፣ ሊቅ ዐቢይን ብቻ መውቀሱ ፋይዳ ያለው አይመስለኝም። ይበልጥ መወቀስ ያለበት ጡንቻው እያለው ሊቅ ዐቢይ ሲደበደብ፣ ጥቅሙና ህልውናው ሲደፈር ዝም ብሎ ተመልካቹ የከተማው ነዋሪ ነው ባይ ነኝ።

ይኸ ማለት ግን፣ ሊቅ ዐቢይ አላፊነቱን ሊወጣ ካልቻለበት ምክንያቶች እንዳንዱ ሁኖ ሊታይም ሊቀርብም አይገባውም። በአገር ውስጥም ሆነ፣ ከአገር ውጭ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ማንም ሳይገፋው፣ በገዛ ፈቃዱ፣ በነቂስ ወጥቶ ‘የኢትዮጵያ ኔልሶን ማንዴላ” እስከማለት የዘመረለት፣ ድጋፉን አለአንዳች ማመንታት የለገሠለት፣ ቢያንስ ለግማሽ ዘመን በአገሪቷ ታይቶ ያልታወቀ መሪ አሰኝቶታል።

በኢትዮጵያውያን ዘንድ ብቻ አይደለም ሊቅ ዐቢይ አድናቆቱን ያተረፈው። በአፍሪቃና በአብዛኛውም ዓለም እንጂ። በሱ መነሣት፣ ከግማሽ ዘመን በላይ ተዋርዶና ተሽቈልቁሎ የነበረው ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያ ወደጥንታቸው ክብርና ማዕርግ ተመልሰዋል። ዓለም በሙሉ ተገርሟል። ኢትዮጵያዊ መሆን ቡራኬና ምርቃት መሆኑን ብዙዎች ተሰምቷቸዋል። ብዙዎቹም ሊቅ ዐቢይ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪቃም ትንሣኤ መሪ ነው እስከማለት ደርሰዋል።

ሊቅ ዐቢይ ግን ይኸንን አለአንዳች ልፋት ያገኘውን ሕዝባዊ አመኔታና ክብር፣ ሞገስና ልዕልና ጠቃሚ ነገር ለመሥራት እንደመጠቀም ፈንታ አንድ ዓመት እንኳን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በከንቱ አባከነው ማለት ይቻላል። ሁናቴውን ሳይጠብቅ በድንገት የአንድ ቢሊዮን ብር ሎተሪ ካሸነፈ፤ ኋላ ግን ምንም ሳይሠራበት በጥቂት ጊዜ ውስጥ እንዳባከነው ሰው ማምሰል ይቻላል። ዐቢይም ያደረገው ይኸንኑ ብል ስሕተት አይመስለኝም።

ከተቀበለው ሕዝባዊ ደጋፍና አንጻር ስንመለከት፣ ሊቅ ዐቢይ እንኳን አገሩን ኢትዮጵያን ቀርቶ፣ በዙርያዋ ያሉትን ኤርትራንም፣ ጂቡትንም፣ ሱዳንና ሱማሌን ጭምር አጣምሮ አንድ አገር ለማድረግ ዕድል ነበረው ማለት ይቻላል። ግን እንደድንገተኛ ሎተሪ አሸናፊው፣ እሱም ዕድሉን ሳይጠቀመው እያባከነው ይገኛል ብቻ ሳይሆን በከንቱ አባክኖታልም። የዚህም ምልክት፣ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ወቀሳና ስድብ ከየአቅጣጫው አድናቂው ከነበረው ሕዝብ ሲዘንብበትና ሲጐርፍበት ማየቱ ነው።

ለታላቅ ታሪክ የታጨ ሰው ሁኖ እያለ፣ ሊቅ ዐቢይ ተኰትኩቶ ካደገበት ከኢሕአዴግ የአስተሳሰብ ቁም ሣጥን ሊወጣ አልፈለገም። የኢሕአዴግን የጐሣና የተዛባ ርእዮተ ዓለም የሙጥኝ ብሎ የያዘና ከሱም ሊላቀቅ ያዳገተው ይመስላል። ከዚህም የተነሣ፣ ከወዲያ ማዶ ያለውን ሰፊውንና የደስ ደስ ያለበትን፣ ለምለሙንና ታላቁን አድማስ ለማየት አልታደለም። እንደገባኝ፣ የጐጥና የጐሣ ርእዮተ-ዓለም ራእዩን አሳውሮታል። ወይንም ተኰትኩቶ ያደገውም ሆነ፣ ተከቦና ተወጥሮ ያለው ይኸንን ርእዮተ ዓለም በሚያቀነቅኑ ኀይሎችና ሰዎች በመሆኑ፣ ዐልፏቸውም ሆነ ጥሏቸው ለመጓዝም ሆነ፣ አንድነት፣ ነፃነትና እኩልነት ከጠማው ከሚወደው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ሁኖ ለመገሥገሥ ፍላጎትም፣ ጥረትም አላሳየም።

“መንግሥተ ሰማይን ላላየ፣ ገሃነም ድንቁ ነው” ወይንም “ዐባይን ያላየ ምንጭ ያደንቃል” የሚለው አባባል በሊቅ ዐቢይ የተፈጸመ ይመስላል። ይኸም ሁኖ ግን ሊቅ ዐቢይ አዝማሚያውን ለመቀልበስ አሁንም ዕድሉ ሰፊ ነው ብል ስሕተት አይመስለኝም። ከፊቱ ያለው ምርጫ ግን ሁለት ብቻ ነው። ሁሉንም ዐቃፊ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ወይንም ርስበርስ ከፋፋይ ኢሕአዴግና ጐጥነት። መካከለኛ መንገድ ያለ አይመስለኝም። በመኻል ቁሞ ቢቀር በሁለቱም ሳይተፋ እንደማይቀር አያጠራጥርም።

LEAVE A REPLY