ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ሳይታሰብ ባደርጉት ጉዞ ከአክሱም ህዝብ ጋር ተውያዩ

ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ሳይታሰብ ባደርጉት ጉዞ ከአክሱም ህዝብ ጋር ተውያዩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሰሞነኛውን የአክሱም ዩኒቨርስቲ ችግር ተከትሎ ጉዳዩን በቅርበት ለማጤንና በችግሮቹ ላይ መፍትሔ ለማበጀት እንዲሁም የመፍረስ አደጋ የትጋረጠበትን የአክሱም ሐውልት ዙሪያ ከህዝብና ከክልል ባለስልጣናት ጋር ለመነጋገር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ሰኔ 3 2011 ዓ.ም ማለዳ አክሱም ከተማ ገብተዋል፡፡

ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አህመድ አክሱም ሲደርሱ የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ በቅርቡ የአክሱም ዩንቨርስቲ ተማሪ የሆነው ወጣት በአሰቃቂ ሁኔታ በድንጋይ ተደብድቦ የተገደለበት ክሰተት ብዙ ኢትዮጵያውያንን ከማሳዘኑ ባሻገር ክፉኛ ማስቆጣቱ ይታወሳል፡፡

በዩኒቨርስቲው የሚማሩ የአማራ ተወላጆችና ሌሎች ማህበረሰቦች ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና ለመንግስት “እኛም የሚፈልገን ቤተሰብ አለና፣ በአስቸኳይ ከዚህ አካባቢ አውጡን” ሲሉ ያስተላለፉት መልዕክት በብዙዎች ዘንድ እያነጋገረ ይገኛል::

ወደ አክሱም የተጓዙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ በአክሱም ቆይታቸው በዩኒቨርሲቲ ከተፈጠረው ችግር ባሻገር በአሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የአክሱም ሐውልት፣ የነዋሪዎች የውሃ አቅርቦት፣ የመብራትና ሌሎች የመሰረተ ልማት ጉዳዮችን በተመለከተ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ጥልቅ ውይይት እንዳደረጉ ለማወቅ ተችሏል::
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአክሱም ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ግጭት የሚፈልግ ሀይል አለ እሱን ለመቋቋም መንግስትና ሀዝብ በጋራ መስራት ይኖርባችዋል ብልዋል::

LEAVE A REPLY