አመሌን አልሸጥም || ወለላዬ ከስዊድን

አመሌን አልሸጥም || ወለላዬ ከስዊድን

በሚመካ ሳዝን      

በአሽቃባጩ ሳፍር

በአስመሳይ ስሳቀቅ

ከወሬኛ ስርቅ

አሉባልታን ስሸሸ

በሃሚት ስንገሸገሽ

ስናደድ አይተሽኝ

ግትር ነህ እንዳልሽኝ

ያኔ እንደታዘብሽኝ

ዘመን ቢለወጥም

ነገር ቢቀየጥም

ከአመሌ አላመልጥም

አመሌን አልሸጥም

               

LEAVE A REPLY