ኢ/ር ታከለ ኡማ በጥቁር አንበሳ ት/ቤት የ10ኛ ከፍል ፈተናን ሂደት ታዘቡ

ኢ/ር ታከለ ኡማ በጥቁር አንበሳ ት/ቤት የ10ኛ ከፍል ፈተናን ሂደት ታዘቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ትናንት ሰኔ 3 ቀን 2011 ዓ.ም የተጀመረው የዘንድሮው የ10ኛ ክፍል ፈተና በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑ ተነገረ፡፡ የአዲስ አበባ መስተዳድር ጊዜያዊ ም/ከንቲባ ታከለ ኡማም የፈተናውን ሂደት ለመቃኘት በከተማዋ ከሚገኙት የመፈተኛ ጣቢያዎች አንዱ በሆነው በጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተገኝተዋል፡፡

ሰሞኑን በአዲስ አበባ የክረምት መርሃ ግብርና በት/ቤቶች ግንባታ ዙሪያ በየቦታው በመገኘት መግለጫዎችን
በመስጠት ላይ የሚገኙት ኢንጅነር ታከለ ኡማ፤  የጥቁር አንበሳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት፣ በተለያዩ ክፍሎች ተዘዋውረው የፈተናውን ሂደት በግልፅ ታዝበዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ፈተናዎች አሰጣጥ ላይ በከንቲባ ደረጃ ትልቅ ባለስልጣን በቀጥታ የፈተናውን ሂደት በአካል በመገኘት ሲከታተል ኢንጅነሩ የመጀመሪያው ከፍተኛ አመራር መሆናቸው ተገልጿል::

በአዲስ አበባ በ81 የመፈተኛ ጣቢያዎች 57 ሺህ 447 ተማሪዎች ፈተናውን እየወሰዱ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY