የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ሐምሌ 26 ቀን 2011 ዓ.ም

የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ሐምሌ 26 ቀን 2011 ዓ.ም

ነራል ሰዓረ ገዳይ ምንም ዓይነት መረጃ ማግኘት አልተቻለም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአማራ ክልል ባለስልጣናት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ላይ ከደረሰው ጥቃት ጀርባ ታስቦ የነበረው መፈንቅለ መንግስት በፍጥነት መቆጣጠር ባይቻል ኖሮ አስከፊ ነገር ይዞ ይመ  እንደነበር ትናንት ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ ላይ ገልዋል፡፡

መንግስት የሰዎችን ድምፅ የማፈን ፍላጎት የለውም፣ እንደውም ከዚህ ቀደም በመንግሥ ተዘግተው የነበሩ መገናኛ ብዙሃን እንከፈቱ ማድረጉ ለእዚህ በቂ ማሳያ ነው ያሉት ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበለፀጉት ገራት ሰዎች ኢንተርኔትን ለበጎ እንደሚጠቀሙበት ጠቁመው በእኛ ሀገር ካለው የመረጃ አቀራረብ አኳያ የሰዎችን ህይወት እና ንብረት ከጥቃት ለማትረፍ አስፈላጊ ሆኖ እስከተገኘ ድረስ ለሳምንት ሳይሆን እስከወዲያኛው ሊዘጋ እንደሚችል አረጋጠዋል፡፡

ሞከራሲያዊ ስርዓት እንዲስፋፋ መንግስታቸው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የሚናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰብዊ መብት አያያዝን በተመለከተ መንግስት እየተተቸ ያለበትን ሂደትም አጣጥለዋል፡፡ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አሁን ጨለማ ቤት የታሰረ የለምሰው አይገረፍምጥፍርም አይነቀልም ሲሉ ነው እማኝነታቸውን የሰጡት፡፡

ከሰኔ 15ቱ መፈንቅለ መንግሥት ጋር በተያያዘ ነራል ሰዓረመኮንን ገድሏል ተብሎ የተጠረጠረው ግለሰብ በህይወት እንዳለ አንገቱ ላይ በጥይት በመመታቱ የህክምና እርዳታ እየተደረገለት እንደሚገኝም ገልዋል፡፡ በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት ግለሰቡ መናገር ባለመቻሉ ከእርሱ የሚፈለገውን በቂ መረጃ እስካሁን ድረስ ማግኘት እንዳልተቻለም ይፋ አድርገዋል፡፡

ተጠርጣሪው ግለሰብ በስልክ ሲገናኛቸው የነበሩ ሰዎችን በሕግ ጥላ ስር በማዋል ከእነርሱ ብዙ መረጃ ሰብስበናል ያሉት ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተጨማሪ ነራሎችን ለመግደል እንቅስቃሴ ሲደረግ እንደነበር የሚያረጋግጥ መረጃ መገኘቱንም በጋዜጣዊ መግለጫው ተናግረዋል፡፡

ቻይና ለኢትዮጵያ የስንዴና  ሩዝ እርዳታ አደረገች

የኢትዮጵያ ቢዝነስ ሙሉ ለሙሉ ለማለት በሚያስችል መልኩ የተቆጣጠረችውና ባለፉት በርካታ ዓመታት በብዙቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ገሪቱ የሰበሰበችው ቻይና በሰብዓዊ ዕርዳታ ብቅ ብላለች፡፡

ከፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ብቻ የምትታወቀው ቻይና ለኢትዮጵያ 9 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ ነው ያደረገችው፡፡

ይህ የሠብዓዊ እርዳታ በተለያዩ ግጭቶች ለተፈናቀሉእንዲሁም በኤንሊኖ (የአየር መዛባት) ምክንያት ችግር ላጋጠማቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚውልም ተገልጿ፡፡

በዛሬው ዕለት ከቻይና መንግስት የተበረከተው ዕርዳታ ስንዴና ሩዝ ሲሆንምርቱ በገንዘብ ሲሰላ 7 ሚሊዮን 201 ሺህ 300 የአሜሪካ ዶላር ያወጣል፡፡

የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳና የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አድማሱ አበበ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ከሆኑት ሚስተር ታን ያን እጅ እርዳታውን ተቀብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልጃገረዶች ጨዋታ”ን በዩኔስኮ ለማስመዝገብአማራና ትግራይ ማሙ

በአማራ እና በትግራይ ክልሎች ለዘመናት ሲከበር የቆየውን ሻደይእና አሸንዳ በዓልን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የትግራይና የአማራ ክልሎች ከስምምነት ላይ ደርሰው አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸው ታወቀ፡፡

በቅርቡ ሕወሓት ሰኔ 15 ቀን ለደረሰው ከባድ አደጋና ግድያ .. ሓላፊነቱን ወስዶ በይፋ ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል ሲል ያወጣው መግለጫና ከአማራ ክልል አስተዳዳሪ ..ፓ የተሰጠው ምላሽ በሁለቱ ክልሎች ሕዝብ መሐል ያለውን ቅራኔ ያሰፋዋል የሚል ስጋት በብዙዎች ዘንድ አሳድሮ ነበር፡፡

ይሁንና በአማራና ትግራይ ክልሎች በተለያዩ ቦታዎች የሚከበሩትን ሻዴ አሸንዳ በዓሎች፣ “የኢትዮጵያ ልጃገረዶች ጨዋታበሚል ስያሜ በመንግስታቱ ድርጅት የትምህር ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ቅርስነት ለማስመዝገብ ሁለቱ ክልሎች በጋራ እየሰሩ መሆኑን የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ  አስታውቋል፡፡

ዩኔስኮ በዓሉን ለመመዝገብ በሂደት ላይ መሆኑን የጠቆሙት የቢሮው ሓላፊ አቶ ግዛት አብዩየሴቶች እኩልነት፣ ነጻነትና አንድነት ተምሳሌት የሆነው የሻደይና የአሸንዳ በዓል ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ከታሪካዊ አመጣጥና አከባበሩ በመነሳት አስረድተዋል፡፡ የትግራይ ክልል ከሁለትና ሶስት ዓመት በፊት ይህንን ታሪካዊ በዓል በብቸኝነት በክልሉ ስም ለማስመዘገብ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ኬንያ ውስጥኢየሱስ ታየየተባለው ሀሰት መሆኑ ታወቀ

ሰሞኑን በኬንያ ውስጥኢየሱስ ታየ በሚል ከማህበራዊ ሚዲያዎች እስከ ተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ድረስ በፍጥነት የተዛመተው ወሬ ሀሰት መሆኑን የሚያረጋግጡ ትክክለኛ ማስረጃዎች በአሁኑ ሰዓት እየወጡ እንደሚገኙ ታወቀ፡፡

ኪሴሪያንተብላ በምትጠራውና ከኬንያ ዋና መዲና ናይሮቢ በደቡብ ምዕራብ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኝ ሥፍራ ነው ኢየሱስ ታየ የተባ፡፡

ታየቱ ማረጋገጫ ነው በሚል ከዜናዎች ጋር በስፋት ምስሉ የተሰራጨውና አነጋጋሪ ሆኖ የሰነበተው ግለሰብ፤ ማይክል ጆብ ሲሆን አሜሪካዊው ጆብ በሙያው የፊልም ተዋናይና ሰባኪ ነው፡፡ ከዚህ በመነሳትም በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ላይ ንግግር እንዲያደርግ ተደጋጋሚ ግብዣዎች ይቀርቡለታል፡፡

ከተለያዩ ገራት በሚቀርቡለት የ“እንፈልግሃለንጥያቄዎች ራሱንህያው የመጽሐፍ ቅዱስ ሙዚየምብሎ የሰየመውና በኦርላንዶ ፍሎሪዳ  የሚኖረው ማይክ ጆብ “ዘሊላንድ ኤክስፒሪያንስበሚል ፊልም እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆኖ ተውኗል፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ዓይነት የአለባበስ ስልት በመጠቀም፣ የተለያዩ ቪዲዮዎችንና ፎቶግራፎችን በመልቀቅ የሚታወቀው ይህ ግለሰብ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ወጣው ቪዲዮ፤ ኬንያ ውስጥ ያሉ የግብርናና የቤት ቁሳቁሶች የሚሸጡባቸው ሱቆች መታየታየቱ “ኢየሱስ በኬንያ ታየየሚለውን ሀሰተኛ ወሬ ፈጥሯል፡፡ ቦታውን ከደቡብ አፍሪካ ሱቆች ጋር በማመሳሰልመሲሁ በማንዴላ ገር ተከሰተየሚሉ መረጃዎች በስህተት መሰራጨታቸው የመገናኛ ብዙሃን  ይፋ አድርገዋል፡፡

ሲኖትራክ አስመጣለሁ በሚል 73 ሚሊዮን ብር የዘረፉት ግለሰብ ተፈረደባቸው

ለበርካታ ሰዎች የሲኖትራክ ተሸከርካሪዎ በሶስት ወራት ለማስመጣት ከ73 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ተቀብለው በመሰወር ክስ የቀረበባቸው የዙና ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ዘሪሁን ጌታሰው የ14 ዓመት ፅኑ ዕስራትና የ300 ሺኅ ብር ቅጣት ተወሰነባቸው፡፡

በአንድ ወቅት በመላ ገሪቱ የመነገጋገሪያ ርዕስ ሆኖ የነበረውን የማጭበርበር ተግባር የፈፀሙት ግለሰብ አን ድመቶ ዘጠኝ ሰዎች የሰበሰቡ ገንዘብ ይዘው ከተሰወሩ በኋላ፣ ሁለት ዓመት በፊት ከተደበቁበት ዱባይ በኢንተርፖል ተይዘው ለኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠታቸው ይታወቃል፡፡

የዙና ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ዘሪሁን ጌታሰው ከባድ መኪናዎችን አስመጣለሁ በማለት በሙሉ ክፍያና  ግማሽ ክፍያ 73 ሚሊዮን ብር ተቀብለው ተሰውረዋል በማለት ዓቃቤ ሕግ 122 ክሶችን መስርቶባቸው ሲከራከሩ ነበር፡፡

ግለሰቡ ባደረጉት የክርክር ሂደት ከ13 ክሶች ው 109 ክሶችን ማስተባበል ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ዓቃቤ ህግ እንደ ክሱ ዓይነት በሰነድና በሰው ባቀረበባቸው ክሶች ጥፋተ ተብለዋል፡፡

ጉዳዩን ሲመረምር የከረመው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት አቶ ዘሪሁን በ14 ዓመታት ፅኑ እስራትና በ300 ሺኅ ብር እንዲቀጡ ማክሰኞ ሐምሌ 23 ቀን 2011 ዓ.ም ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

ዙና ትሬዲንግ በሪልስቴትየግብርና ምርቶችን ወደ ውጭ ገር  ኤክስፖት ማድረግአውቶ ሞቢሎችንና የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን በማስመጣ ዘርፍ የሚሰራ ድርጅት ነበር፡፡

LEAVE A REPLY