የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ሐምሌ 27 ቀን 2011 ዓ.ም

የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ሐምሌ 27 ቀን 2011 ዓ.ም

በጽንፈኛ ብሔርተኞች የሚደርሱ አዳዲስ የሰብኣዊመብት ጥሰቶች ለለውጡ ዕንቅፋት ሆነዋል

የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተቃርኖ የሞላበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ በፍትህ ስርዓቱ ላይ መሰናክሎችን ከመፍጠሩ ባሻገር ለውጡ በታሰበለት ፍጥነት እንዳይሄድ በማድረጉ ረገድም ችግሮችን እያስከተለ እንደሚገኝ አስታውቋል፡

ሐምሌ 26 ቀን 2011 ዓ.ም የፌደራልና የክልል ፍትህ ተቋማት ሓላፊዎች በተገኙበት በተደረገው ሰፊ ውይይት የፌደራል ዐቃቤ ህግ ያከናወናቸውን ተግባራት የሚያሳይ ሪፖርት ቀርቧል፡፡

ግጭቶች እንዲከሰቱ ምክንያት ሆነዋል በሚል የተጠረጠሩ ሰዎችን ለህግ የማቅረቡ ስራ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ እንደሆነም ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ተናግረዋል፡፡

በግለሰቦች ላይ ጥፋት እንዲፈፀም የማቀነባበርና የተሳትፎ ሚና የነበራቸውን ሰዎች ለፍርድ የማቅረቡ ስራም መ/ቤቱ ያከናወነው ሌላኛው ስራ እንደሆነም ተሰምቷል፡ ሕዝቡ የሚፈልገውን ለውጥ በአፋጣኝ ተግባራዊ አለማድረግ፣ የአቅም ውስንንት በምክንያትነት ሲቀመጥ፤ መሻሻል የሚገባቸው ህጎችና ተቋማት መብዛትም ሌላኛው ችግር እንደሆነ የገለጹት ምክትል ዐቃቤ ሕጉ፣ ያለፉት ጥፋቶችን ለማረም ጥረት በሚደረግበት ወቅት፣ የአዳዲስ ግጭቶች መከሰት የተቋሙን ስራ እያደናቀፈው እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡

“ያለንበት ፖለቲካ አውድ እጅግ ፈታኝ ነው፤ በጣም ተቃርኖ የበዛበት፣ የተቃርኖው ጡዘትና ጽንፍ መርገጥ እጅግ በከረረበትና ይህ ሁሉ ችግር በታጨቀበት ፖለቲካ ውስጥ ለውጡን ተግባራዊ ለማድረግ ሲሞከር አስቸጋሪ ሁኔታዎች እየገጠሙን ነው” ሲሉም ዶ/ር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ ሀቁን ቁልጭ አድርገው አስቀምጠውታል፡፡

ያለፈውን ጥፋት ለማስተካከል በሚሰራበት ወቅት ከሃገሪቱ ወቅታዊ ፖለቲካ አኳያ አዳዲስ ግጭቶች፣ አዳዲስ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች በተለያየ ቦታዎች መከሰታቸው፣ ዜጎች መፈናቀላቸው፣ ሀብትና ንብረታቸው ላይ ጉዳት መድረሱ ብዙዎች የምንገጓጓለትን ለውጥ እውን እንዳይሆን በእጅጉ ዕንቅፋት ፈጥሮብናልም ብለዋል፡፡

መስመሩን የሳተ ብሔርተኝነትም ሌላኛው ችግር መሆኑ ተሰምቷል፡፡ በጣም በጦዘ፣ ፈር በለቀቀ ብሔርተኝነትና በዛመስመር በሚሄዱ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች፣ የሓላፊነትንና የነፃነትን ስርዓት ሚዛን ባልጠበቀ መልኩ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ለውጡን ወይም ሽግግሩን አስተጓጉሎታል የሚሉት ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ፤ እንዲህ ዓይነት ክፍተቶችን ለመሙላት ግን ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

በድሬደዋ በሥነ ምግባር ጉድለት የተባረሩ 114 ፖሊሶች ወደ ስራ ተመለሱ

በድሬደዋ በሥነ ምግባር ጉድለት የተባረሩና ብዙኃኑ ሕብረተሰብ በተወሰደባቸው ዕርምጃ የተሰማማባቸው ፖሊሶች ወደ ስራ እንዲመለሱ መደረጉ ታወቀ፡፡

ቀደም ሲል ሥራ ላይ በነበሩበት ወቅት በድሬደዋ ከተማ ከቀን ቀን ወንጀሎች እንዲበራከቱ ከማድረግ ባሻገር፣ ራሳቸውም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በወንጀል ተሳታፊ በመሆናቸው ምክንያት ተባረው የነበሩት ፖሊሶችን የድሬደ ዋከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን፣ በአሁኑ ሰዓት ወደ ሥራ እንዲመለሱና የፖሊስ ሠራዊቱን እንዲቀላቀሉ ማድረጉ በበርካታ ነዋሪዎች ዘንድ ቅሬታን ፈጥሯል፡፡

“እነዚህን በወንጀልና በሥነ ምግባር ጉድለት የተጥለቀለቁሰዎችን ወደ ሥራ መመለስ፣ ያንን አስከፊና አስጨናቂ የነበረውን የወንጀል ጊዜ መመለስ ነው” በማለት ለአዲስ ማለዳ አስተያየታቸውን የሰጡ የድሬደዋ ከተማ ነዋሪዎች ለደሕንነታቸው ጭምር በእጅጉ እየሰጉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ፖሊሶቹ ቀደም ሲል የተለያዩና ተደጋጋሚ የሥነ ምግባር ጉድለቶች ታይቶባቸው እንደተቀነሱ ያስታወሱት የድሬደዋፖሊስ ኮሚሽን ሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ ዋና ሳጅን ባንተዓለምግርማ፤ በኅብረተሰቡ ከፍተኛ ወንጀሎችና የተደራጁ ስርቆቶች ላይ ተሰማርቶ የተገኘ ፖሊስ በመሀላቸው አልተገኘም ሲሉ ለነዋሪዎቹ ወቀሳ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

“ከጥፋታችን ታርመናል፣ ሕዝብንም ለመካስ ተዘጋጅተናል” በሚል የይቅርታ ደብዳቤ ካስገቡ 174 ተቀናሽ ፖሊሶች ውስጥ 114 የሚሆኑት ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ በዚህ መሰረት ወደ ማሰልጠኛ የገቡት ተመላሽ ፖሊሶች መሐል ወታደራዊና የንድፈ ሃሳብ ስልጠናዎችን በሚወስዱበት ጊዜ ብቃታቸው እየተመዘነ ሊሰናበቱ የሚችሉበት አጋጣሚ እንደሚኖር ዋና ሳጅኑ ጠቁመዋል፡፡

የሰኔ 15ቱ ተጠርጣሪዎች በሽብር ህጉ መከሰሳቸው ስሕተት ነው ተባለ

የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በሰኔ አስራ አምስቱ ግድያና ሁከት ተጠርጥረው የተያዙት ሰዎችን በሽብርነኝነት መክሰሱ ትልቅ ስህተት መሆኑ ተነገረ፡፡

የፍትህ ወርን አስመልክቶ በሽግግር ወቅት የመደበኛ ፍትህዕ ድሎችና ተግዳሮቶች ላይ ትኩረቱን ባደረገው ውይይት ላይየተለያዩ አስተያየቶች ተደምጠው ነበር፡፡ በፌደራል ጠቅላይፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ጋባዥነት በፍትህ ስርዓቱ ላይ ያላቸውን ትዝብት እንዲናገሩ ዕድሉ የተሰጣቸው የሕገ መንግስት ባለሙያና መምህሩ አቶ ሙሉጌታ አራጋው የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግን በግልጽ ተችተዋል፡፡

“ዐቃቤ ህግ በሰኔ አስራ አምስቱ ግድያ የተጠረጠሩ ሰዎችን በጸረ ሽብር ህግ መክሰስ ተገቢ አይደለም” ያሉት የሕገ መንግስት ባለሙያው፤ ጸረ ሽብር ህጉ በአሁኑ ሰዓት ሊሞት ሆስፒታል ውስጥ ባለበት ሰዓት፣ እሱን የሚተካ ሌላ ህግ ጥናትተደርጎ ተግባራዊ ሊሆን አብዛኛው ነገር በተጠናቀቀበት ጊዜ እንዲህ ዓይነት አሰራር መከተል እጅግ አሳፋሪ መሆኑን ጭምር ይፋ አድርገዋል፡፡

“ዐቃቤ ሕጎች ለምን ይህንን አደረጉ? እነዚህ የጠረጧቸውሰዎች ረዥም ዘመን እንዲታሰሩ ይፈልጋሉ? ሞት እንዲፈረድባቸው ፈልገው ነው? ወይስ አስረው ያለ ምንም ጥያቄ ማስቀመጥ ስለፈለጉ ነው? ” በማለት የክልልና የፌደራልዐቃቤ ሕግ አመራሮችን የጠየቁት አቶ ሙሉጌታ አራጋው፤ በዚህም ክንያት ተጠርጣሪዎች በርካታ የምርመራ ጊዜ እየተጠየቀባቸው በመሆኑ ፍርድ ቤቶችም ቆም ብለው ራሳቸውን ቢፈትሹ ጥሩ ነው ሲሉ መክረዋል፡፡

አንድ እስረኛ ተይዞ ፍርድ ቤት ሲቀርብ ዐቃቤ ህግ “ገና እያጣራሁ ነውና 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ” ብሎ ሲጠይቅ፣ አንድ ዳኛ መጀመሪያያ ሰው ለምን እንደታሰረ መጠየቅ እንዳለበት በመጥቀስ በተግባር ያለውን የፍትህ አሰራሩን የታዘቡት ባለሙያ አስረድተዋል፡፡ “ዐቃቤ ሕግ ተጨማሪ ጊዜ እፈልጋለሁ ብሎ የተከለከለበትን ጊዜ በዕድሜዬ ሰምቼ አላውቅም” ያሉት የሕገ መንግስት ባለሙያና መምህሩ አቶ ሙሉጌታ፤ እስረኞች ከወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር እንዲገናኙ ነፃነት ሊሰጣቸው እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ጠበቃና ዕስረኛን ወይም ዕስረኛና ቤተሰብን ማገናኘት ከባድ ስራ ሆኖ ነው ወይስ ከጀርባ ሌላ ዓላማ ኖሮ ይህንን ማድረግ ያልተቻለው? በማለት የሚሞግቱት አቶ ሙሉጌታ ይህንን መሰል የፍትህ ተቋማት ችግሮች ለመፍታት የፖለቲካ ቁርጠኛነት እንደሚስፈልግም ከተጨባጭ ዕውነታው በመነሳት ለማሳየት ሞክረዋል፡፡

በአርባ በስልሳ ኮንደሚኒየም ቤቶች ዕግድ፣ 400 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ደረሰ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዕጣ ለተጠቃሚዎች ካስተላለፋቸው የአርባ በስልሳ ኮንደሚኒየም ቤቶች ዘጠና ስምንቱ በፍርድ ቤት ዕግድ ስለ ፀናባቸው የአራት መቶ ሚሊዮን ብር ኪሳራ እንደደረሰበት አስታውቋል፡፡

የተወሰኑ ዕግዶችን በይግባኝ በማስነሳቱ የኪሳራው መጠን በአንድ ቢሊዮን ብር ሊቀንስለት እንደቻለ ነው የተነገረው፡፡ የአዲስ አበባ መስተዳድር ገንብቶ ለነዋሪዎች ካስተላለፋቸው 18.576 የአርባ በስልሳ ቁጠባ ቤቶች ላይ ፍርድቤት ዕግድ አስተላልፎ ነበር፡፡ በዚህ ዕግድ ምክንት 1 ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር የሚደርስ ገንዘብ ሊከስር የነበረው መስተዳድሩ የእግድ ይነሳልኝና ሌሎችም መከራከሪያዎችን አድርጎ የ478 ቤቶች እግድ እንደተነሳለት፣ የከተማው አስተዳደር የ2011 ዓ.ም የስራ ክንውን ሪፖርት በቀረበበት ወቅት ይፋተደርጓል፡፡

ቀሪዎቹ ዘጠና ስምንት ቤቶች ዕግዳቸው እንደፀና ሲሆንበዚህም ምክንያት አራት መቶ ሚሊዮን ብር የአዲስ አበባ መስተዳድር የቤቶች ልማት ኤጀንሲ እንደከሰረ ለማወቅተችሏል፡፡ “አስቀድመን በገባነው ውል መሠረት ሙሉውን ክፍያየፈጽመን ቢሆንም በዕጣ አወጣጡ ላይ ቅሬታ አለን” ያሉየአርባ በስልሳ ቤት ተመዝጋቢዎች ጉዳዩን ፍርድ ቤት አድረሰ ውለወራት ሲከራከሩ መቆየታቸው የሚታወስ ነው፡፡

በፖለቲካው ትኩሳት ሳቢያ የኢትዮጵያ የወርቅ ገበያበእጅጉ ወርዷል ተባለ

ከቡና ቀጥሎ ከፍተኛ የነበረው የወርቅ ንግድ ከጊዜ ወደጊዜ ቁልቁል እየወረደ መሆኑ ተነገረ፡፡በ2006 ዓ.ም 430 ሚሊዮን ዶላር ያስገኝ የነበረው የወርቅ ንግድ ወደ 32 ሚሊዮን ዶላር ማሽቆልቆሉ ነው የተሰማው፡፡

ኢትዮጵያ ወርቅ፣ ሳፋየር፣ ኦፓል፣ታንታለም፣ እምነበረድና ሌሎች ማዕድናትን በማምረት ለውጭ ገበያ ስታቀርብ መቆየቷ ይታወቃል፡፡ ይሁንና እነዚህ ምርቶች እጅግ አስደንጋጭ በሆነመልኩ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የውጭ ሽያጫቸው ወርዷል፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ሃገሪቱ እያስተናገደች ያለችው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ዘርፉን በከፍተኛ ሁኔታ እየጎዳው ነው ተብሏል፡፡ ያለፉትን ስድስት ወራት የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ሁኔታ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ያቀረቡት የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ፤ ከቡና ቀጥሎ የሃገሪቱ ከፍተኛ ገቢ የነበረው የወርቅ ገበያ በፍጥነት ቁልቁል እየወረደ በመሆኑ ሁኔታውበዚህ ከቀጠለ ከዘርፉ የምናገኘው ገቢ አለ በሎ ለመናገር በእጅጉ አስቸጋሪ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

LEAVE A REPLY