ትዝ ይልሻል አብረን ሳለን? || ማሕሙድ አሕመድ

ትዝ ይልሻል አብረን ሳለን? || ማሕሙድ አሕመድ

ትዝ ይልሻል አብረን ሳለን?
እንደዛሬው ሳንላያይ
በስስት እየተያየን በፍቅር ቃል ስንወያይ ? በችኩል እሳቤ ግፊት
እንደዛሬው ሳንሆን በፊት
በክፉ ምኞት ሽንገላ ደስታችንን ሳንነጠቅ በብቼኝነት ስቃይ ውስጥ ተራርቀን ሳንደበቅ

ያኔ … ያኔ ….
ከጨረቃ ውበት ሰርቀን
በወርቃማው ብርሀን ደምቀን
በተፈጥሮ ግርማ ሞገስ ባምላክ ጥበብ ተመስጠን
በቃልኪዳን ኮረብታ ላይ ጎን ለጎን ተቀምጠን
ልዩ ደስታ ስንቋደስ ያለ ገደብ ያለመጠን …

ዛሬም ብቻየን ሁኜ
ተለያይተን ተራርቀን በትካዜውስጥ መንኜ እዚያው እቦታችን ላይ ብቻየን እቀመጣለሁ
እተክዝ እተክዝና ወደ ሰማይ ቀና እላለሁ
እናም ድምቡል ቦቃ ውስጥ ውብ ምስልሽን አየዋለሁ

በማራኪ ጥምረታችሁ ቀን በቀን እመሰጣለሁ ።
ከዚያም አስብ አስብና
ምላሽሽን ባላገኝም —ጥያቄየን አቀርባለሁ …
በለስላሳው ልዝብ ውበት በጨለማው ድባብ
ደምቃ
ምሽታችንን ልታስውብ ስትወጣ ወቅቷን ጠብቃ
በእቅፏ የምትይዝሽ ላንቺ ምንሽ ናት ጨረቃ ?

LEAVE A REPLY