በችግሮች የተከበበው የኢህአዴግ አደረጃጀት የኦሮሞ ህዝብና የኢትዮጵያ ህዝቦች ጥያቄዎችን ለመመለስ የማይመች ነው-...

በችግሮች የተከበበው የኢህአዴግ አደረጃጀት የኦሮሞ ህዝብና የኢትዮጵያ ህዝቦች ጥያቄዎችን ለመመለስ የማይመች ነው- ኦዴፓ

ኢቢሲ || የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ODP) በችግሮች የተከበበው የኢህአዴግ አደረጃጀት የኦሮሞ ህዝብና የኢትዮጵያ ህዝቦች ጥያቄዎችን ለመመለስ የማይመች መሆኑን ገልጿል፡፡

ፓርቲው በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ያገኙት የኖቤል የሰላም ሽልማት ማግኘትን ተከትሎ የአገሪቱ ህዝቦች ደስታና ድጋፍ በልዩ አድናቆት ይመለከታል፡፡

ትናንት እንደ ፓርቲ አሸናፊ ሆነን እዚህ ደረጃ የደረስነው የኦሮሞ ህዝብ ይዘንና ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሆነን ነው ያለው የፓርቲው መግለጫ፣ አሁንም ከኦሮሞ ህዝብ እና ከኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር በመሆን አሸናፊ ሆነን እንደምንሻገር ጥርጣሬ የለንም ብሏል ፓርቲው፡፡

ፓርቲው በተለያዩ የአመራር እርከኖች ላይ ያሉ አመራሮች በአመለካከትና በተግባር በአንድነት እንዲሰሩ ለማድረግ እንደምሰራ ገልጿል፡፡

እስከ አሁን ምላሽ ያገኙ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄን መነሻ በማድረግ እስከ አሁን ምላሽ ላለገኙ የህዝብ ጥያቄ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል አቅጣጫ እንደተቀመጠ ፓርቲው ገልጿል፡፡

በርካታ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ቋንቋዎች፣ ባህሎች ባሉበት አገር ውስጥ የፌዴራሊዚም ስርዓት አማራጭ የሌለው ስርዓት ስለሆነ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ብዝሃነትን ማዕከል ያደረገ እውነተኛ ፌዴራሊዝም እንዲገነባና የኢትዮጵያ ህዝቦች እኩልነትና ነፃነት እንዲከበር የማያወላዳ አቋም እንዳለው ፓርቲው ገልጿል፡፡

በተለያዩ ችግሮች የተከበበው የኢህአዴድ አደረጃጀት የኦሮሞ ህዝብና የኢትዮጵያ ህዝቦች ጥያቄ ለለመለስ የማይመች መሆኑ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ውይይት ካደረገበት በኋላ ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡

የኢህአዴግ አደረጃጀትን በመዘመን በዘመናዊ አሰራር የሚመራ ፓርቲ ለመመስረት የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ሀሳብን በመደመር ሀሳብ ለመተካት ውይይት ሲደረግበት መቆየቱን ያስታወሰው ፓርቲው፣ የመደመር ሀሳብ ከዚህ ቀደም የነበሩት ስኬቶችን ይበልጥ ለማጠናከርና ያሚታዩ ችግሮችን መፍታት የአዲስ ትውልድ መብትና ጥቅም ያስከብራል ብሎ ፓርቲው እንደሚያምን ተገልጿል፡፡

ህዝቡ ፓርቲው ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ህዝቡ ያገኘውን መብቶች አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችሉ በመሆናቸው ማህበረሰቡ ለተፈፃሚነቱ ትብብር እንዲያደርግ ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል፡፡

LEAVE A REPLY