የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ህዳር 10 ቀን 2011 ዓ.ም

የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ህዳር 10 ቀን 2011 ዓ.ም

ጃዋርን ሲጠብቁ የሰነበቱ ተማሪዎች፤ ዛሬ በ6 ኪሎ ዮንቨርስቲ ግጭት ለመቀስቀስ ሞከሩ

የጽንፈኛ ቄሮ አባላት የሆኑና ቀደም ባሉት ጊዜያት አዲስ አበባ ላይ የተለያዮ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን እና ኢትዮጵያዊነት ይዘት ያላቸውን ስብሰባዎች በመረበሽ የሚታወቁ የጃዋር መሐመድ ተላላኪዎች ዛሬ በአዲስ አበባ 6 ኪሎ ዮንቨርስቲ ግቢ ውስጥ ለመፍጠር የሞከሩት ብጥብጥ በፌደራል ፖሊስ ከሽፏል::

በአዲስ አበባ ዮንቨርስቲዎች ውስጥ ተማሪ በሆኑና ከአሁን በፊት በተደጋጋሚ የባላደራውን ጋዜጣዊ መግለጫና የኢዜማን ስብሰባ በመረበሽ ረገድ ዋነኛ አስተባባሪ በሆኑ ቄሮዎች የሚመራው ቡድን በ6 ኪሎ ዮንቨርስቲ ውስጥ ረብሻ የማስነሳት እንዲሁም በአማራና ኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ተማሪዎች መሀል ግጭት ለመፍጠር ውስጥ ውስጡን ሢሠራ መሰንበቱን በሥፍራው ተገኝቶ ሁኔታውን የተከታተለው የኢትዮጵያ ነገ ሪፖርተር ዘግቧል::

ጥቂት የዮንቨርስቲው ተማሪ የሆኑና በግልፅ የፊንፊኔ ኬኛን ፖለቲካ ከማራመድ ባሻገር የጃዋር መሐመድ ደጋፊ መሆናቸው የሚታወቅ ጽንፈኞች ሰሞኑን በ6 ኪሎ እና 4 ኪሎ ዮንቨርስቲ ካምፓሶች ያልተለመዱ የቡድንተኝነት እንቅስቃሴዎችን በቀንና በምሽት ሲያደርጉ መታየታቸው በሌሎች የዮንቨርስቲው ማኅበረሰብ ውስጥ ጥርጣሬ እንዲፈጠር ማስቻሉን ሪፖርተራችን ያነጋገራቸው የ6ኪሎ ካምፓስ ተማሪዎች ለኢትዮጵያ ነገ ገልጸዋል::

ዛሬ ሊካሄድ የታሰበው ኹከትና እንዲሆን የተፈለገው የአማራና የኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ግጭት ዋነኛ አስተባባሪ ከአራት ወር በፊት የባላደራው ምክር ቤት መግለጫን ያስተጓገለው እና የአዲስ አበባን ሕዝብ ” ዱርዬ” እያለ በመሳደብ ሲበጠብጥ የነበረው መንጋ አባል ኦብሳ የተሰኘው የአዲስ አበባ ዮንቨርስቲ ተማሪ መሆኑንም ኢትዮጵያ ነገ በሥፍራው የነበረውን ግርግር በተመለከተው ዘጋቢያችን አማካይነት አረጋግጧል::

በተደጋጋሚ ከጃዋር መሐመድ፣ ከታከለ ኡማ እና ከሌሎች የኦዴፓ እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት ጋር የሚታየውና ጠንካራ ግንኙነት እንዳለው የሚታወቀው ጽንፈኛው ኦብሳ በ6 ኪሎ ካምፓስ ውስጥ ለጃዋር መሐመድ ያላቸውን ድጋፍ ከግብረ አበሮቹ ጋር ለማንጸባረቅ እንቅስቃሴ በጀመረበት ቅፅበት መረጃው በደረሳቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት ቁጥጥር ሥር ውሏል::

የባላደራው ምክር ቤት ጋዜጣዊ መግለጫን ከግብረ አበሮቹና ጋር ካስበጠበጠ በኋላ ከኢንጂነር ታከለ ኡማ ጋር ያንን ድርጊት ከመፈጸሙ ከጥቂት ቀናት በፊት ጃንጥላ ተጠልለው ከአዲስ አበባ መስተዳደር ግቢ ከከንቲባው ቢሮ ሲወጡ የሚያሳየው ፎቶ በማኀበራዊ ሚዲያዎች ይፋ የተደረገበት ይህ ወጣት ጃዋር መሐመድ ድረሱልኝ በሚል ውዝግብ በፈጠረበት ወቅት መሣሪያ ታጥቆ በግቢው ውስጥ ለጥፋት መምህሩ ጥበቃ ሲያደርግ በኦ ኤምኤን ቴሌቪዥንና በፌስ ቡክ ላይበግልፅ መታየቱ ይታወሳል::

ይህ ግለሰብና ሌሎች ተማሪዎች ከሳምንታት በፊት አለቃቸው ተከብቢያለሁ ባለበት ጊዜ በመኖሪያ ቤቱ ከተሰባሰቡ ጭፍን ደጋፊዎቹ ጋር በመሆን ጥበቃ እናደርጋለን በማለት የትምህርት ገበታቸውን ጥለው ሕገ ወጥ መሣሪያ በመታጠቅ በሀገሪቱ ላይ ዕልቂትና ሽብር ላደረሰ ሰው ጥብቅና መቆማቸውን ያስታወሱት ኢትዮጵያ ነገ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ዮንቨርስቲ ተማሪዎች ጽንፈኛ ቄሮዎቹ ያሰቡት የዛሬው ብጥብጥ ቢሳካላቸው ኖሮ በሚፈጠረው ግርግር ጥቃት ሊያደርሱ የሚችሉ ከተለያዮ የኦሮሚያ ክልሎች የመጡ የመንጋ አባላትን ከግቢው ውጪ በብዛት አሠማርተው እንደነበር ገልጸዋል::

የዛሬው ዕልቂት ደጋሽ ቡድን አስተባባሪ እንዲሁም የጃዋር መሐመድ ተላላኪ ኦብሳ የተሰኘው የኢዲስ አበባ ዮንቨርስቲ ተማሪ ከጥቂት ግብረ አበሮቹ ጋር በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሆኖ ከግቢው የወጣ ቢሆንም ከዛ በኋላ ላሰበው የጥፋት ዕቅድ በህግ ስለመጠየቁ አንዳችም የተገለጸ ነገር የለም::

የኢትዮጵያ ነገ ሪፖርተር ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ እስከ ከቀኑ አስረ አንድ ሰዐት ድረስ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለሁለት ጊዜያት በመመላለስ ስለ ግለሰቡ መረጃ ቢጠይቅም እኛ ጋር አልመጣም የሚል ምላሽ ከዕለት ሪፖርት ምዝገባ ክፍል ተሰጥቶታል:: በተመሳሳይ ጽንፈኛውን ወጣት ወደያዘው ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በተደጋጋሚ ስልክ በመደወል መረጃ ቢጠይቅም “ምንም የምናውቀው ነገር የለም” የሚል አስገራሚ ምላሽ ተሰጥቶታል::

በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ ሽብርተኛ ተያዘ

ዛሬ ሃሙስ ህዳር 11 ቀን ከሰዓት በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ቡጁምቡራ ውስጥ ካረፈ በኋላ በሽብር ድርጊት የተጠረጠረ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የቡሩንዲ ባለስልጣናት ገለጹ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት በሆነው አውሮፕላን የተሳፈረ አንድ ግለሰብ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ገብቶ በመዝጋት በሰነዘረው ማስፈራሪያ፣ አውሮፕላኑ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ወደሚያርፉበት የቡጁምቡራ አየር ማረፊያ እንዲቆም እንደተደረገ ታውቋል።

አውሮፕላኑ ዛሬ በቀጥታ በረራ ከአዲስ አበባ ወደ ቡሩንዲ ዋና ከተማ ቡጁምቡራ እየበረረ ሳለ ነበር ችግሩ የተከሰተው። ስማቸው እንዳይጠቀስ ከጠየቁ የአየር መንገዱ ሠራተኛ ለቢቢሲ እንደገለፁት የተባለው ችግር እንዳጋጠመና ምንም ጉዳት ሳይደርስ አውሮፕላኑ ቡጁምቡራ አርፏል።

ጉዳዮን አስመልክተው ለቢቢሲ አስተያየታቸውን የሰጡየአየር መንገዱ ባልደረባ “አውሮፕላኑ በአየር ማረፊያው ወታደራዊ ክፍል ውስጥ እንዲያርፍ ተደርጎ ችግሩን የፈጠረው ግለሰብም በቁጥጥር ስር ውሏል” ብለዋል::

ይሁንና በአውሮፕላኑ ውስጥ ያጋጠመውን ችግር የፈጠረው ግለሰብ ፍላጎቱ ምን እንደሆነ እስካሁን የታወቀ ነገር አለመኖሩን ፣ግለሰቡ ፈንጂ መያዙን በመግለጽ አውሮፕላኑን እንደሚያፈነዳው ባስፈራራበት ወቅት ከፍተኛ ፍርሃት በተሳፋሪዎቹ ዘንድ መፈጠሩን ግን አልሸሸጉም።

የቡሩንዲ የደህንነት ሚኒስቴር በትዊተር ገጹ ላይ ክስተቱ ትክክል መሆኑን አረጋግጦ “በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ ተሳፍሮ የነበረ ተጠርጣሪ ሽብርተኛ ቡጁምቡራ አየር ማረፊያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሏል” ሲል ይፋ አድርጓል።

ጉግል በመላ ዓለም የፖለቲካ ማስታወቂያዎችን ሊያግድ እንደሆነ አስታወቀ።

ይህ እገዳ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ዩቲውብና ጉግል ሰርችን መራጭ ለማግኘት መጠቀም እንዳይቻል ያደርጋል ተብሏል።

ቢሆንም ግን አሁንም የምርጫ ቅስቀሳ እንቅስቃሴዎች ጉግልን ተጠቅመው የመራጭ እድሜ፣ፆታና አድራሻን ለማወቅ ይችላሉ።

ጉግል በመላ ዓለም ሊተገብረው ያቀደው ይህ እገዳ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ እንግሊዝ ውስጥ ይጀመራል ተብሏል።

የፖለቲካ ማስታወቂያዎችን ማገድ ብቻም ሳይሆን አሳሳች መረጃ በሚይዙ ሌሎች ማስታወቂያዎች ላይም እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል ጉግል።

ይህ እርምጃ ጉግልን ቀደም ሲል የፖለቲካ እጩዎች ወይም የምርጫ ቅስቀሳ ማስታወቂያዎች መረጃን እንደማያጣራ ካስታወቀው ፌስቡክ ጋር ግጭት ውስጥ ሊከትታቸው ይችላል ተብሎም ተሰግቷል።

የጉግል ዘርፍ ማናገጀር የሆኑት ስኮት ስፔንሰር ሰፊ የፖለቲካ ውይይት የዴሞክራሲ ወሳኝ ክፍል ስለሆነ ማንም እንደፈለገ የፖለቲካ ሃሳቦችን፣ ተቃራኒ ሃሳቦችን ሊያደላድል፤ እንዲሁም ሊመራና ሊቆጣጠር አይገባም ብለዋል።

“በቀጣይ እርምጃቸው የምንወስድባቸው የፖለቲካ ማስታወቂያዎች ምንም እንኳ ውስን ቢሆኑም እንቀጥልበታለን”ብለዋል

የአማራና የኦሮሞን ሕዝብ የሚያስተሳስር ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

የአማራና ኦሮሞ ህዝቦችን የህዝብ ለህዝብ ትስስር ማጠናከር የሚያስችል የሰላም ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው ተባለ።

በሁለት ሰፊ ማኅበረሰቦች ኮንፈረንስ ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ሌሎች የኀብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ መሆናቸውም እየተነገረ ነው።

በኮንፈረንሱ ሀገራዊ፣ ወቅታዊ ጉዳዮች እንዲሁም የኦሮሞ እና አማራ ህዝቦችን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር እየተደረገ ይገኛል። በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሁለቱ ብሔሮች መሀል ቅራኔ እንዲፈጠርና ለዓመታት በአክራሪ ኦሮሞ ብሔርተኞች ሲስተጋባ የኖረው ሀሰተኛ ተረክ ከፍ ብሎ ወደመተላለቅ እንዲያመራ የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎች በስፋት ተስተውለዋል::

ከለውጡ ማግሥት አንስቶ በተለያዮ የኦሮሚያ ክልልሎች ብዛት ያላቸው የአማራ ተወላጆች መገደላቸው የበለጠ በአማራ እና ኦሮሞ ማኅበረሰብ ተወላጆች መሀል የጥላቻ ፖለቲካን ለመዝራት ጽንፈኛ ብሔርተኞች እንደተጠቀሙበት ይታወሳሌ::

በጸጥታ ኃይሎች የታጀቡት የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣን ምዕራብ ወለጋ ላይ ተገደሉ

ከፍተኛ እና ግልፅ የሆነ ታጣቂው የኦነግ ቡድን ይንቀሳቀስበታል በሚባለው በምዕራብ ወለጋ ዞን አንድ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ባለስልጣን ፣ መንገድ ላይ በታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ መገደላቸው ታወቀ።

ትናንት ረቡዕ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ውስጥ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ቶላ ገዳ ለሥራ ጉዳይ ወደ ምዕራብ ወለጋ ቄለም ወለጋ ዞን እየሄዱ ባሉበት ወቅት፣ ላሎ አሳቢ ተብሎ በሚታወቀው ወረዳ ውስጥ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸውን ተረጋግጧል።

የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ኤሊያስ ኡመታ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ግድያው የተፈጸመው ላሎ አሳቢ ወረዳ ውስጥ ጋራ ቶሬ በሚባል ቦታ ላይ ረቡዕ ዕለት ጠዋት አምስት ሰዓት አካባቢ መሆኑን አስታውቀዋል። አቶ ቶላን የገደሉት ታጣቂዎች እየተጓዙበት በነበረው መኪና ላይ ከግራና ከቀኝ ሆነው በከፈቱት ተኩስ በመኪናው ውስጥ እየተጓዙ የነበሩ መንገደኞችን ኢላማ አድርገው በነበሩ ታጣቂዎች እንደተገደሉና አቶ ቶላ ገዳ የኦሮሚያ ክልል መስተዳደር የመንገዶች ባለስልጣን ኮምዩኒኬሽን ሓላፊ እንደሆኑ አስተዳዳሪው ገልጸዋል።

ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት ከአቶ ቶላ ጋር ለሥራ ጉዳይ ሌሎች ሰዎች በመኪናው ውስጥ ነበሩ:: ከእነርሱም መካከል፤ በመኪናው ውስጥ የቄለም ወለጋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ከጸጥታና አስተዳደር ጽህፈት ቤትም ሌሎች ሰዎች አብረዋቸው ነበሩ ተብሏል። በተጨማሪም የጸጥታ አካላት በመኪናው ውስጥ ከተጓዦቹ ጋር እንደነበሩና ጥቃቱ በተፈጸመበት ቅጽበት ፈጻሚዎቹን ለመያዝና ለመከተል ሙከራ ቢደረግም ሳይሳካላቸው እንደቀረም ተገልጿል።

ጥቃቱ በተፈጸመበት ጊዜ የአቶ ቶላን ሕይወት ለህልፈት የዳረገው ጥይት በመኪናው የፊት መስታወት በኩል የተተኮሰ ሲሆን፤ አቶ ቶላ በጥይት እንደተመቱ ጥቃቱ በተፈጸመበት ስፍራ ወዲያውኑ ሕይወታቸው ማለፉን አስተዳዳሪው ይናገራሉ። በተሽከርካሪው ላይ በታጣቂዎች በተከፈተው ተኩስ ከአቶ ቶላ ውጪ አብረዋቸው ይጓዙ በነበሩት ሰዎች ላይ ግን ምንም ጉዳት ሳይርስባቸው ሊተርፉ ችለዋል መባሉ አነጋጋሪ ሆኗል።

አቶ ቶላ ገዳ በጥቃቱ ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ አስከሬናቸው በአቅራቢያው ወደሚገኘው የአይራ ሆስፒታል እንደተላከና በኋላም ወደ ቤተሰቦቻቸው መሸኘቱን የጠቆሙት አስተዳዳሪው አቶ ኤሊያስ ፤ ይህ ጥቃት በማን እንደተፈጸመ በአሁኑ ወቅት የታወቀ ነገር ፣ ብሎምበአካባቢው ያሉ የጸጥታ አካላት በክስተቱ ፈጻሚዎች ዙሪያ ክትትልና ምርመራ እያደረጉ ስለሆነ ከምርመራው የሚገኘው ውጤት በወቅቱ ይፋ እንደሚደረግም አስረድተዋል::

በአቶ ቶላና በባልደረቦቻቸው መኪና ላይ ጥቃት በተፈጸመበት ስፍራ ላይ የሰዎች ሕይወት አይጥፋ እንጂ ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ድርጊት የተፈጸመበት መሆኑንም አስተዳዳሪው አስታውሰዋል። በቅርብ ጊዜያት ውስጥ በምዕራብ ወለጋና በቄለም ወለጋ ዞኖች ውስጥ የመንግሥት ባለስልጣናትን ኢላማ ያደረጉ ግድያና ጥቃቶች በተደጋጋሚ ሲፈጸም የቆየ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞችና በተለያዩ የግል ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ሰዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ከተለያዩ አካላት የተዋቀረ ኮማንድ ፖስት የአካባቢውን ጸጥታ ለማስጠበቅ ጥረት እያደረገ ቢሆንም ነዋሪዎችበተደጋጋሚ ስላለው የጸጥታ ስጋትና ችግር ቅሬታቸውን ለክልሉና ለፌደራል መንግሥት በማሰማት ላይ ናቸው።

አንዳንድ ወገኖች በአካባቢው ለሚፈጸመው ጥቃት ከኦነግ ተለይቶ የወጣው እና ራሱን ኦነግ ሸኔ ብሎ የሚጠራው በጃል መሮ የሚመራውን ጽንፈኛ ታጣቂ ቡድን ተጠያቂ በማድረግ ላይ ናቸው::

ኢትዮጵያ የዕፅዋት ሀብቷን በአጭር ጊዜ ውስጥ ልታጣ ትችላለች ተባለ

ሀገሪችን ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አገራት ከ40 በመቶ በላይ የዕፀዋት ሀብታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ አንድ ጥናት ጠቁሟል። ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በርካታ የምዕራብ አፍሪካ አገራት ታንዛኒያና ዴሞክራቲክ ኮንጎ ከአንድ ሦስተኛ በላይ ተፈጥሮ የለገሰቻቸውን የዕፀዋት ሀብታቸውን ያጣሉ ተብሎ ተገምቷል።

የመጥፋት አደጋ ከተጋረጠባቸው የዕፀዋት ዝርያዎች መካከል ዛፎች፣ ሐረጎች፣ የመድኃኒት ዕፀዋትና ሌሎችም የተፈጥሮ ሀብቶች ናቸው ተጠቃሽ ሳይንቲስቶች እንዳሉት ለእነዚህ ዕፅዋት መጥፋት አደጋን የደቀኑት በአገራቱ ውስጥ ያለው ከፍተኛ የደን ምንጣሮ፣ የህዝብ ቁጥር መጨመርና የአየር ሁኔታ መዛባት ዋነኞቹ ናቸው። ናቸው ።

“የተፈጥሮ ብዘሃ ሕይወት ለሰው ልጆች ተገልጸው የማያልቁ ጥቅሞችን የሚያበረክቱ ሲሆን፤ የእነሱ መጥፋትየምድራችንን ቀጣይነት አደጋ ላይ ይጥለዋል” ያሉትበፈረንሳይ ብሔራዊ የዘላቂ ልማት ተቋም ውስጥ አጥኚ የሆኑት ዶክተር ቶማ ኩቭረር ፤ የብዝሃ ሕይወት ሀብቶች መጥፋት በተለይ በትሮፒካል የአየር ንብረት ክልል ውስጥ በሚገኙ የአፍሪካ አገራት ላይ ከባድ ችግርን እንደሚፈጥር ጠቁመው ፣ “በዚህ አካባቢ አስደናቂ የብዘሃ ሕይወት ሃብት ቢኖርም ነገር ግን የሚስተዋሉት ወሳኝ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች እንዲሁም በመጪዎቹ አስርት ዓመታት ከሚጠበቀው የሕዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተዳምሮ ጉዳቱን ያከፋዋል” በማለት ቅድመ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

ሳይንስ አድቫንስስ በተባለው የሳይንሳዊ ጥናት መጽሔት ላይ የወጣው የባለሙያዎች ምርምር ውጤት ለመጥፋት የተጋለጡ የተፈጥሮ ሀብቶችን ለማወቅ ተከልሶ የተዘጋጀን የጥናት ዘዴን መሰረት አድርጎ የተሰራ እንደሆነም ቢቢሲ ዘግቧል።

ከዕፅዋቱ ሌላ በጥናቱ እስካሁን ድረስ ከ10 አጥቢ እንስሳት ዘጠኙ ፣ እንዲሁም ከአእዋፋት መካከል ደግሞ ሁለት ሦስተኞቹ ጥናት ተካሂዶባቸዋል። ከዕፅዋት መካከልም ከስምንት በመቶ በታች የሚሆኑት፣ ውሃና ድንጋይ ላይ የሚበቅሉ የአልጌ ዝርያዎችን ሳይጨምር፣ የሚያብቡና ሌሎች ዕፅዋትን ጥናቱ ዳስሷል።

ተመራማሪዎቹ 20 ሺህ የሚሆኑ የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸውን የዕፅዋት ዝርያዎች ላይ፣ ተመሳሳይ ግን በጣም የተፋጠነ ዘዴን ተጠቅመው ጥናታቸውን አካሂደዋል::

በጥናታቸውም 33 በመቶ የሚሆኑት ዝርያዎች ከፍተኛ የመጥፋት አደጋ እንደተጋረጠባቸው ሲያመለክቱ፣ በብዛት ከማይገኙ ሌሎች ዝርያዎች መካከል ደግሞ አንድ ሦስተኛው በቅርቡ የመጥፋት የስጋት ምድብ ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉም ነው የተነገረው።

የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ የዴሞክራሲያዊ የበላይነትን እንደሚያሳይ ጠ/ሚ/ር ጽ/ቤት ገለጸ

የሲዳማ በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ሕዝበ ውሳኔ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ፣ ልዩነትን በውይይትና በድምጽ መስጫ ሳጥን የመፍታት ዴሞክራሲያዊ ሂደት የበላይነቱ እንዲቀጥል የማድረግ አቋምን የሚያሳይ ነው ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገለፀ።

ጽሕፈት ቤቱ የሲዳማ በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ሕዝበ ውሳኔ የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በሰላማዊ መንገድ መጠናቀቁን አስመልክቶ ባወጣው መልዕክት ላይ ነው ከላይ የተጻፈውን ሃሳብ ያሰፈረው።

“የሲዳማ በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ሕዝበ ውሳኔ፣ የድምጽ አሰጣጥ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽዖ ያደረጋችሁ ዜጎች እና ተቋማት እንኳን ደስ ያላችሁ”  በማለትም ጽሕፈት ቤቱ በሕዝበ ውሳኔው የተሳተፉትን አመስግኗል።

ሃዋሳ ከተማን ጨምሮ በሲዳማ ዞን በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች፣ የህዝበ ውሳኔው የድምፅ አሰጣጥ በሰላማዊ መንገድ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንትና ምሽት ማስታወቁ አይዘነጋም።

የጀርመኑ ቮይዝ ካምፓኒ፣ ለግልገል ጊቤ 2 ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በአማካሪነት ተፈራረመ

የጀርመኑ “ቮይዝ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኩባንያ” ለግልገል ጊቤ ቁጥር 2 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በአማካሪነት ለመሥራት የሚያስችለውን ስምምነት መፈረሙ ታወቀ። ትናንት በጀርመን በርሊን በተካሄደው የቡድን 20 ሀገራት ኢንቨስትመንት ጉባኤ ጎን ለጎን ነው ስምምነቱ የተፈረመው።

ዘየውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እና የቮይዝ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኩባንያ ዋና ስራ አስኪያጅ ማርክ ክለሴን ህጋዊ ስምምነቱን በፊርማቸው አፅድቀውታል። የኮንትራት አገልግሎት ስምምነቱ ለሁለት ዓመት ይቆያል:: ይህም ፕሮጀክቱ የሚያመነጨውን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅም ለማሳደግ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

በስምምነቱ መሰረት ኩባንያው ዘመናዊ እና ዲጂታል የሆኑ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ጥገና አሠራሮች እና አገልግሎቶችን የሚዘረጋ መሆኑ ታውቋል። ከዚህ ባለፈም በዘርፉ የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር የሚያካሂድ እንደሆነም ተሰምቷል::

LEAVE A REPLY