የዛሬ ታህሳስ 2/2012 የመቀሌው የፍርድ ቤት ውሎ!!! || ደጀኔ አሰፋ

የዛሬ ታህሳስ 2/2012 የመቀሌው የፍርድ ቤት ውሎ!!! || ደጀኔ አሰፋ

በማንነታቸው ብቻ ታፍነው በመቀሌ ወህኒ ቤት በግፍ ታጉረው በትህነግ እየተሰቃዩ ያሉት የራያ ተወላጆች ዛሬም በመቀሌ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

የዛሬው ችሎት የሽብር ክስ የተመሰረተባቸውን የ 31 የራያ ተወላጆችን ጉዳይ የተመለከተ ሲሆን የ 24 ምስክሮችን የምስክርነት ቃል አድምጧል።

ዛሬ ችሎቱ ሲሰየም አቃቤ ህጉ << ምስክሮቼ ተሟልተው አልመጡልኝምና ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠኝ >> የሚል ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ዳኛው ግን << እስከመቼ ድረስ ምስክሮቼ አልተሟሉም በሚል ቀጠሮ እያራዘምን እንቀጥላለን? ስለዚህ ባሉት ቀጥል >> በማለት የአቃቤ ህጉን appeal ውድቅ አድርጎታል። በዚህም የ 24 ምስክሮች ቃል ተደምጧል።

ዛሬ የቀረቡት ሁሉም ምስክሮች በሚባል ደረጃ < ስለ ተከሳሾቹ ምንም አናውቅም ፣ አላየንም > ያሉ ሲሆን መረሳ የተባለ (ሰው ገድሎ ፖሊስ የተደረገ የራያ ጨርጨር ተወላጅ) ግን << ዳርጌ ከበደና ግደይ ዋዕሮ ጥቅምት 11/ 2011 በራያ አላማጣ በነበረው ተቃውሞ ሰልፍ ወንጭፍ ይዘው አይቻለሁ >> የሚል ምስክርነት ሰጥቷል።

ዳኛውም << በወንጭፉ ምን አደረጉበት? >> የሚል ጥያቄ የጠየቀው ሲሆን < ወንጭፍ መያዛቸውን እንጅ ሲያደርጉም ሆነ ማንን እንደመቱበት አላየሁም > በማለት መልሷል። የሚገርመው ደግሞ አንድ የምስኪን ቤተሰብ ታዳጊ ልጅንም (ስሙንና ቤተሰቡን መጥቀስ አልፈለኩም) ምስክር አድርገው በዳርጌ ላይ አቅርበዋል።

= ዳኛው ወደ ውሳኔ የመሄድ አዝማሚያ ያሳየ ቢሆንም አቃቤ ህግ < ምስክሮቼ 38 በመሆናቸው ችሎቱ የሁሉንም ቃል ያዳምጥልኝ፤ ነገ ምስክሮቼን አቀርባለሁ> በማለቱ ችሎቱ ነገ እንዲቀጥል ተወስኗል።

ነገ ከሚጠበቁት ምስክሮች መካከል… ግርማይ ሙቀቴ የተባለ ነፍሰ ገዳይ ፤ ዳንኤል ታምራት ፤ ታዲዎስ እና አፈወርቅ ገ/ሂዎት ይገኙበታል። ዳዊት ወልደሚካኤልም እንዲቀርብ ታዟል ተብሏል።

#ነገ ብይን ይሰጣል የሚል ተስፋ አለ። ሆኖም ግን አንዱ ምስክር ሲቀርብ አንዱ እየቀረ እየተናበቡ ስለሚያደርጉት ፍትህን ከነሱ መጠበቅ ከባድ ነው። ባይሆንማ ኖሮ ሁሉም ምስክሮች ቀርበው የሚያምኑበትን በመሰከሩ ነበር። ነገር ግን ፍትህን ለማጓተትና ወገኖቻችን እንዲሰቃዩ ለማድረግ ነው ይህንን የምስክርነት ሸፍጥ እየፈፀሙ የሚገኙት። ብቻ ነገ የሚሆነውን እንጠብቃለን!!!

ትህነግ እንደ ድርጅት የራያ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት መሆኑን ብናውቅም በግለሰብ ደረጃ ግን አሁንም ድረስ በቀላቸውን በራያ ህዝብ ላይ እየፈፀሙ ያሉትን መዝግበናል። ማን ምን እንደመሰከረ ይዘናል ወደፊትም እንይዛለን። ነገም ማን እንደሚቀርብ፣ ማን እንደሚቀር፣ ማን ምን እንደሚል እናያለን! እንሰማለን! እንመዘግባለን!!!!

ብቻ ግን. . . እልህ ይተናነቃል። ሲቃ ይሰንጋል። ውስጤ ሲቆጣና ሲበሳጭ ለሰውነቴ ይሰማኛል። የዚህን ያህል ግፍ በራያ ተወላጆች ላይ መፈፀምስ ለምን ፈለጉ እያልኩ እቃጠላለሁ። ይህ ስሜት የሁሉም የራያ ተወላጅ ጥልቅ ስሜት ነው። ሁሉም በቀሉን ለመመለስ ቀን እየጠበቀ ነው!!!

ይህ ግፍ ለራያ ህዝብ ትልቅ የማንቂያ ደወል ነው!!! ለስበር ራያ ደግሞ የመጨረሻ መልዕክት ነው!!!! በምንም ላንመለስ በምንም ላንዘናጋ ከውስጣችን ጋር እንማማላለን!!! የበለጠ ጨካኞች እንሆናለን!!!!

በቃ!!! በቃ!!!! በቃ!!!! . . . የተከፈለው ተከፍሎ ነፃነታችንን ማወጅ አማራጭ ሳይሆን ግዴታችን ነው!!!! ይነጋል!!!!

LEAVE A REPLY