የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ጥር 6 ቀን 2011 ዓ.ም

የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ጥር 6 ቀን 2011 ዓ.ም

ምርጫ ቦርድ ነሀሴ 10 የመራጮች ድምጽ የሚሠጥበት ቀን እንዲሆን ሀሳብ አቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እካሄደ በሚገኘው ምክክር የ2012ቱ ስድስተኛው ገራዊ ምርጫ ነሃ 10 ቀን 2012 ዓ.ም እንዲካሄድ ሀሳብ አቅርቧል፡፡ ቦርዱ በምርጫው ቀድሞ ከተያዘለት የወርሃ ግንቦት የጊዜ ሠሌዳ ለውጥ ያስፈለገበትን ምክንያት ሲገልፅገሪቱ ያለውን የላምና መረጋጋት ጥያቄ ምክንያት አድርጎ አቅርቧል፡፡

“መንግሥትም ሆነ የሚመለከታቸው አካላት ሰላማዊ ሁኔታ በገሪቱ ላይ እንዲፈጠር ሊሩ ይገባል” ሲል ቦርዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የምክክር መድረክ ላይ ገል፡፡ በመድረኩ በተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት መንግሥት የህዝብ ቆጠራ ማካሄድ አቅም ባጣበት ሁኔታ የህዝብን ድምጽ በአግባቡ ማስከበር ይችላል ወይ? በሚለው ላይ ጥያቄ እንዳላቸው በመግለፅቦርዱ አሁን ላይ ካስቀመጠው የምርጫ ሰሌዳም ተሻግሮ ምርጫውን እንዲያራዝም ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የምርጫ ተወዳዳሪ እጬዎቹን ሊመለምል ነው

በአዲስ አበባ ጉዳይ ከፍተኛ የማነቃቃት ሥራ ያካሄደው እና በእስክንድር ነጋ የሚመራው ባለአደራው ምክር ቤት የስም ለውጥ ከማድረጉ ባሻገር ወደ ፖለቲካ ፓርቲነት መቀየሩን አስታውቋል፡፡

ቀደም ሲል ባለአደራው ም/ቤት በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀሰው ሲቪክ ማበር የሕዝብ ግፊትን ተከትሎ ወደ ፖለቲካ ፓርቲነት እንደተቀየረና መጠሪያውንም ሀሳቡ ለመጀመሪያ ጊዜ በተተገበረበት፣ የሕዝብ አደራን በተቀበለበት “ባልደራስ አዳራሽ ስም እንዲጠራ አድርጓል፡፡

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የሚል ስያሜውን ይፋ ያደረገው አዲሱ ፓርቲ እሁድ ጥር 3 ቀን 2012 ዓ.ም የምስረታ ጉባዔውን አድርጎ መሪውን በመምረጥማግስቱ ጥር 4 ቀን ለምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ተገቢውን የምዝገባ ጥያቄ አቅርቧል፡፡

እሁድ ጥር 3 ቀን 2012 ዓ.ም በኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል ሊያካሂድ የነበረውን የምስረታ ጉባኤ የተከለከለው ባልደራሱ ለምርጫ ቦርድ ያቀረበውን ህጋዊ ጥያቄ ተከትሎ በአንድ ሳምንት ውስጥ የቅድመ ዕውቅና ሰርተፍተኬት እናገኛለን ብሎ እንደሚጠብቅ የፓርቲው መሪ እስክንድር ነጋ ለግዮን መጽሔት ገልል፡፡  

“ኢህአዴግ /ብልፅግና በአዲስ አበባ አንድም ወንበር እንዳያገኝ ጠንክረን እንሰራለን” ያለው እስክንድር ነጋ አዲስ አበባ ላይ ልዩ ጥቅም አለን የሚሉ ፓርቲና ተመሳሳይ እሳቤ ያላቸው ግለሰቦችን ያቀፉ ፓርቲዎችን እንዳይመርጥ  ማሳሰባችን ተከትሎ በርካቶች “ታዲያ ማንን እንምረጥ? የሚል ጥያቄዎች ማቅረባቸው ወደ ፖለቲካ ፓርቲነት ገፍቶናል ብሏል፡፡

እስክንድር ነጋ አሜሪካና አውሮፓ የነበረውን ቆይታና በቀጣይ በፓርቲ ምስረታው ዙሪያ ሊሰራቸው ስላሰባቸው ጉዳዮች ላነጋገረው የኢትዮጵያ ነገ የአዲስ አበባ ዘጋቢ አሁን ላይ ጠንካራ የአደረጃጀትና አባላትን የማጠናከር ሥራ እያካሄደ መሆኑን ገልጾ ጥር 15 ቀን 2012 ዓ.ም የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባዔውን የምርጫ ቦርድ ተወካዮች በተገኙበት ለማካሄድ ማቀዱን ገልጿል::

በቀጣይ በአስተሳሰብና በፖለቲካ አቅጣጫ (በተለይ በአዲስ አበባ ጉዳይ) ከሚመስሉን ፓርቲዎች ጋር ተጣምረን የምንሰራበት አጋጣሚ ሊኖር ይችላል ያለው እስክንድር ነጋ አሁን ላይ ለቀጣይ ምርጫ ፓርቲያቸው የሚያቀርባቸውን እጬዎች በመመልመል ጉዳይ ላይ ትኩረት በመስጠት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ተናግሯል::

የኢትዮጵያ ፣ ግብፅና ሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ተወያዮ

በአባይ ግድብና በውሃ አጠቃቀም ዙሪያ ያላቸው አለመግባባት እያየለ የመጣው የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ሚኒስትሮች ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ተወያዮ።

የሦስቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የውሃ ሚኒስትሮች በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በዋሽንግተን እያደረጉት ካለው ውይይት ጎን ለጎን የተካሄደ ነው የአሁኑ የሃገራቱ ምክክር።

አገራቱ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ በተለያዩ ዙሮች የሦስትዮሽ ስብሰባ ሲያደርጉ መቆየታቸው የሚታወስ ነው። በዚህም በግድቡ ውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ዙሪያ የመከሩ ሲሆን፤ በቅርቡ የተደረገው አራተኛ ዙር ስብሰባ ግብጽ በግድቡ የውሃ አሞላል ላይ ይዛ በቀረበችው አዲስ ሐሳብ ምክንያት ያለ ስምምነት መጠናቀቁም አይዘነጋም።

የአራተኛውን ዙር ስብባ መጠናቀቅ ተከትሎም እስካሁን ባደረጓቸው ድርድሮች የደረሱባቸውን ነጥቦች የሚገመግሙበት ስብሰባ በዋሽንግተን ዲሲ እያደረጉ ናቸው:: የአገራቱን አለመግባባት ለመቅረፍ ትኩረት ሰጥተው በአወያይነት እየሠሩ ያሉት አሜሪካና ዓለም ባንክ መሆናቸውን ተከትሎ የሦስቱን አገሮች ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና የውሃ ሚኒስትሮች ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አግኝተው አወያይተዋቸዋል:: ይሁን እንጂ እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳን በአባይ ዙሪያ መግባባት አልቻሉም ነው የተባለው::

የጋሞ አባቶችና ወጣቶች ከአርባ ምንጭ ወደ ጎንደር የሰላም ጉዞ ጀመሩ

በእርጥብ ሳራቸው ሰላምን ያወጁ የጋሞ አባቶች እና ወጣቶች ወደ ጎንደር የሚያደርጉትን ጉዞ ከአርባ ምንጭ መጀመራቸው ታወቀ፡፡ ረቡዕ ጥር 7 ቀን የጀመረው ጉዞ እስከ ጥር 14 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ የሚደረግ ሲሆን ከአርባ ምንጭ የተነሱት የጋሞ አባቶች እና ወጣቶች የተለያዩ ከተሞችን በማቋረጥ እስከ ጎንደር ከተማ ጉዞቸውን እንደሚያደርጉ ተገልል፡፡

አባቶ የአባቢያቸውን ሰላም እንዴት እንዳስጠበቁ የሚያሳይ ተሞክራቸውን በጉዞው ላይ የሚያካፍሉ ሲሆን የአርባ ምንጭ ዩንቨርሲቲ የሰላ ተምሳሌትነትም ለሌሎች የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተሞክሮነት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የጋሞ አባቶች በጉዞው የተለያዩ ከተሞችን የሚያቋርጡ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሚያርፍባቸው ከተሞችም ስለ ሰላምና አንድነት ይመካከራሉ፡፡ የሰላም ተጓዥ የሆኑት አባቶች እና ወጣቶች በአዲስ አበባ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ተገኝተው የአንድነት ፓርክን ይጎበኛሉ መባሉን ሰምተናል::

ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለሁለት የሥራ ሓላፊዎች ሹመት ሰጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ ለሁለት የሥራ ሓላፊዎች ሹመቶችን መስጠታቸው ተሰማ፡፡

ግልፅ ያልሆነውን የመደመር ፖለቲካንና ብልጽግና ፓርቲን ይዘው ብቅ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግሥታዊ መዋቅሮች ላይ ማስተካከያ እንደሚያደርጉ ጠቁመው ነበር:: በዚህ መሰረት አቶ አህመድ ቱሳ የነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትና ስርጭት ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል፡፡

በተጨማሪ አቶ ወልደአብ ደምሴ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሐፈት ቤት ዛሬ ይፊ አድርጓል::

ኢትዮ ቴሌኮም በግማሽ ዓመት ከ22 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አግኝቻለሁ አለ

ከመጠን በላይ የተጋነነ የክፍያ ሲስተምን በተጠቃሚዎቹ ላይ ጭኗል በሚል የሚታማው ኢትዮ ቴሌኮም በግማሽ ዓመቱ 22 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።

መ/ቤቱ የስድስት ወር  የሥራና የገቢ አፈጻጸሙን በተመለከተ ባወጣው ሪፖርት ፤ ባለፉት ስድስት ወራት 22 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር አጠቃላይ ገቢ በማግኘት የእቅዱን 104 በመቶ ማሳካቱን ይፋ አድርጓል::  ገቢው ካለፈው ዓመት አንጻር የ32 በመቶ እድገት አሳይቷል ነው የተባለው። በተጨማሪ ተቋሙ የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙ አገልግሎቶችም 73 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ማግኘቱንም ገልጿል።

የተሰበሰበው ገቢ ከሞባይል ድምጽ 50 ነጥብ 4 በመቶ፣ ከዳታና ኢንተርኔት 27 ነጥብ 3 በመቶ፣ ከዓለም ዐቀፍ ንግድ ገቢ 9 ነጥብ 8 በመቶ፣ እሴት ከሚጨምሩ አገልግሎቶች 8 ነጥብ 5 በመቶ እንዲሁም ከሌሎች አገልግሎቶች 3 በመቶ መሆኑን ከመግለጫው መረዳት ችለናል።

የደንበኞቹ ብዛት 45 ነጥብ 6 ሚሊየን መድረሱን የጠቀሰው የኢትዮ ቴሌኮም ሪፖርት ፤ ይህም ከእቅዱ የ99 በመቶ አፈጻጸም ያለው እና ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ10 ነጥብ 9 በመቶ እድገት ማሳየቱን ይመሰክራል።

በሌላ በኩል በአገልግሎት አይነት የሞባይል ድምፅ ተጠቃሚዎች ብዛት ከ44 ሚሊየን በላይ፣ የዳታ እና የኢንተርኔት ተጠቃሚ 22 ነጥብ 74 ሚሊየን፣ የመደበኛ ስልክ ከ1 ሚሊየን በላይ ደንበኞች ሲሆኑ ፤ አጠቃላይ የቴሌኮም  ሥርዐት መጠን ደግሞ 45 ነጥብ 4 በመቶ መድረሱ ተገልጿል፡፡

ተቋሙ በሪፖርቱ የደንበኞችን ሁለንተናዊ ተሞክሮ ለማሻሻልና በተለይም እያደገ የመጣውን የዳታ አገልግሎት ተጠቃሚነት ፍላጎት ማስተናገድ የሚያስችል የኔትወርክ አቅም የማሳደግ ሥራዎች በአዲስ አበባና በክልሎች እየተከናወነ መሆኑም ነው የተነገረው።

በተጨማሪም የደንበኞችን የቴሌኮም አጠቃቀም ለማሳደግና ተሞክሯቸውን ለማሻሻል የሚያስችሉ የኔትወርክ ማስፋፊያና የአገልግሎት ጥራትን ለመጨመር የሚያስችሉ ማሻሻያዎችን ማከናወኑንም ሪፖርቱ ያብራራል:: እንዲሁም ከመደበኛ የቴሌኮም አገልግሎቶች ባሻገር ሌሎች እሴት የሚጨምሩ 6 አዳዲስ እና 16 የተሻሻሉ የአገር ውስጥና የዓለም ዐቀፍ ምርትና አገልግሎቶችን ለገበያ ማቅረቡም ተጠቁሟል።

በዚህም ባሳለፍነው ስድስት ወራት ከተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች 759 ሺህ 741 ተጨማሪ ደንበኞችን ማስተናገድ የሚችል የሦስተኛ ትውልድ (3ጂ) እና 170 ሺህ 737 የሁለተኛ ትውልድ (2ጂ) ሞባይል ኔትወርክ አቅም መፍጠር መቻሉን የጠቀሰው ሪፖርት በሌላ በኩል በፍጥነት እያደገ ያለውን የዳታ አጠቃቀም ለማስተናገድ የሚያስችል የዓለም ዐቀፍ ጌትዌይ አቅምን በግማሽ ዓመቱ ከ71 በመቶ በላይ ማሳደግ ችያለሁ ብሏል። በተጨማሪም በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የአራተኛ ትውልድ (4ጂ) ኔትዎርክ ማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን ለመተግበር የሚያስችል ሥራ እየተሠራ መሆኑንኢትዮ ቴሌኮም ይፋ አድርጓል ።

መንግሥት  ልማት ፕሮጀክቶች አስተዳደር ችግር ላይ ወድቋል ተባለ

የፌደራል መንግሥት የልማት ፕሮጀክቶች አስተዳደር እና አመራር ረቂቅ አዋጅ የመንግሥት ሀብት በውጤታማ ዘርፎች ላይ ለማዋል ያስችላል ተባለ፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 77ኛ መደበኛ ስብሰባው በፕላንና ልማት ኮሚሽን ተዘጋጅቶ የቀረበውን የፌደራል መንግሥ የልማት ፕሮጀክቶች አስተዳደር እና አመራር ረቂቅ አዋጅ መልኩ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት መሰረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን ለኅብረተሰቡ ለማድረስ ከፍተኛ ሀብት በመመደብ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ያከናውናል ተብሏል፡፡ ከዚህ ባለፈም ገሪቱ ከምትከተለው የልማት አቅጣጫ አንር በግሉ ዘርፍ የልማት ራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

የመንግሥት ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው መርግብር የጥራት ደረጃ በጀት ባለመከናወናቸው በኢኮኖሚ ውስጥ ያመጣሉ ተብሎ የሚጠበቀውን ውጤት ማግኘት እንዳልተቻለ የፕላንና ልማት ኮሚሽን ገልል፡፡

እነዚህን ተግዳሮቶች በጥልቀት ለመለየት በፌደራል መንግሥት የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ተከታታይ ጥናት ቢደረግም፤ ከፕሮጀክት ጥናት አመራረጥ እና ውሳኔ አሰጣጥ እንዲሁም በትግበራ ላይ የሚታዩ የፕሮጀክት ኮንትራት አስተዳደር፣ አፈፃፀምና  ክትትል ችግር ፕሮጀክቶችን በውጤታማነት ለማስተዳደር እንቅፋት ሆነው ተገኝተዋል ተብሏል፡፡

ፒያሳ አራዳ ባርና አፍሪካ ካፌን ጨምሮ 7 ሱቆች በእሳት ተቃጠሉ

በተለምዶ ፒያሳ ተብሎ በሚጠራው አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አካባቢ የሚገኙ ሰባት የንግድ ቤቶች ላይ የእሳት አደጋ ደርሷል፡፡ የኢትዮጵያ ነገ የአዲስ አበባ ዘጋቢ በስፍራው ተገኝቶ በግልጽ እንዳስተዋለው ሁለት የፒያሳ አካባቢ መዝናኛና የብዙዎች መቀጣጠሪያና መገናኛ የሆኑት ቤቶች በእሳቱ አመድ ለመሆን መቻላቸውን ታዝቧል::

ዛሬ ረቡዕ ጥር 6 ቀን 4 ሰዓት ከ40 ላይ በተከሰተው የእሳት አደጋ ሰባት ሱቆች ላይ ቃጠሎ የደረሰ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ ሁለት የንግድ ቤቶች (አፍሪካ ካፌ እና አራዳ ባር)  ሙሉ ለሙሉ መውደማቸው ተረጋግጧል፡፡መንግሥታዊ አካላትም ቢሆኑ የጠፋውን ንብረት መጠን ለማወቅ ቢቸገሩም የንግድ ቤትቹ መውደማቸውን አልካደም::

የአዲስ አበባ የእሳት አደጋና ሥራ አመራር ኮሚሽን በስፍራው በመገኘት እሳቱ ተጨማሪ አደጋ ሳያስከትል መቆጣጠር የቻለ ሲሆን በአደጋው በሰው ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አለመድረሱም ተረጋግጧል፡፡ ከተቃጠሉት ድርጅቶች መሀል ምግብ ቤቶች የአልባሳት የመነጽር እና የመዋቢያ ቅባት መሸጫ ሱቆች ይገኙበታል፡፡      

LEAVE A REPLY