የኢትዮጵያ ነገ ዜናዎች ረቡዕ ጥር 20 || ቀን 2011 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ነገ ዜናዎች ረቡዕ ጥር 20 || ቀን 2011 ዓ.ም

የታገቱት ተማሪዎች ያሉበትን ቦታና በሕይወት መኖራቸውን መንግሥት ዛሬ ይፋ አደረገ

በደምቢ ዶሎ ከተማ አቅራቢያ በታጣቂዎች ስለታገቱት ተማሪዎች ሐሰተኛ መግለጫ ከቀናት በፊት ሰጥቶ የነበረው መንግሥት ጥፋቱን ለማድበስበስ የሞከረበትንና ተማሪዎቹ አሁንም በእገታ ስር መሆናቸውን ያረጋገጠ መግለጫ ዛሬ ሰጥቷል::

የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክቴሪያት አቶ ንጉሱ ጥላሁን በአገሪቱ በሚገኙ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንደተከሰተው ሁሉ በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲም ተመሳሳይ የጸጥታ ችግር እንደተከሰተ አስታውሰው፤ በዚህም ለደህንነታቸው የሰጉ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ለቀው ሲወጡ እንደነበረ ከመጠቆማቸው ባሻገር ተማሪዎች ትምህርታቸውን ጥለው እንዳይሄዱ ፌደራል ፖሊስ ከአካባቢው ማህብረሰብ ጋር የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርጉ ቆይተዋል ብለዋል።

የፌደራል ፖሊስ በአካባቢው ያለውን የጸጥታ መደፍረስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ጥለው ከወጡ ችግር ሊገጥማቸው እንደሚችል ሲያስጠነቅቅ እና መረጃ ሲሰጥ ነበረ ያሉት አቶ ንጉሡ “ተማሪዎች ግን በማይጠበቅ መንገድ በጋምቤላ በኩል ጉዟቸውን ቀጠሉ።” ሲሉ ተማሪዎች የመረጡት መንገድ እንደስህተት አቅርበዋል።

ቸአንፊሎ ወረዳ ሱዲ በምትባል ቦታ ላይ ተማሪዎች፣ ሌሎች ወጣቶች እና አንድ የአካባቢው አመራር ጭምር ህዳር 25፣ 2012 ላይ መያዛቸው መረጋገጡን ዘግይተው ያመኑት የብልጽግና አመራር ሰዎች መያዛቸው ሲሰማ መከላከያ ሠራዊት አሰሳ አካሂዶ 21 ተማሪዎችና ሌሎች ተጨማሪ ሰዎችን ማስለቀቁን ፤ 21ዱ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲው እንዲመለሱ መደረጉን ተናግረዋል። ” ጥር ቀን 2 ይህኑን መረጃ ለሕዝብ ማቅረባችን ይታወሳል፤ በእጃችን ላይ ያለን መረጃ ጥር 2 ላይ የሰጠነው መረጃ ትክክለኛነትን ያረጋግጣል” በማለትም ሕዝብን የዋሹበትን መግለጫ በትክክለኛነት ለማቅረብ ሞክረዋል::

“አንድ መጥራት ያለበት ጉዳይ መገናኛ ብዙሃንም ሆኑ በማህብራዊ ሚዲያ ላይ የሚነገረው የታገቱት ተማሪዎች ቁጥር 17 ስለመሆናቸው ነው። ይህ ቁጥር ሲጣራ ግን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ የሚያሳያው 12 የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ብቻ ናቸው። 5 ግን የዩኒቨርሲቲው ተማሪ ስለመሆናቸው መረጃ የለም” ሲሉ ለመከራከር ሞክረዋል። በአሁኑ ወቅት 800 የሚሆኑ ተማሪዎች የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ጊቢ ለቀው መውጣታቸውን አቶ ንጉ አረጋግጠዋል።

በተያያዘ ዜና የፌደራል ፖሊሰ ኮሚሽነር ጀነራል በበኩላቸው “በስፍራው አላንቀሳቅስ አላላውስ ብለው ሕዝብ የሚያስቸግሩ አካላት አሉ” ሲሉ ዘግየት ብለው የችግሩን ጥልቀት ገሀድ አውጥተዋል።

“በደምቢ ዶሎ አካባቢ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ኃይል ተደምስሷል። ተደምስሶ ግን አልቀረም። የተረፈው አሁን እራሱን አደራጅቶ በሽፍታ መልክ እየተንቀሳቀስ ነው። መንግሥት ዝም አላለም። እርምጃ እየወሰደ ነው።” ያሉት ኮሚሽነሩ እገታው የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ብቻ ሳይሆን፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችንና የአካባቢው ነዋሪዎችን እንዲሁም ነጋዴዎችን ይጨምራል በማለት የብዙኃኑን ሕዝብ ጥያቄ ለማቀዝቀዝ ያለመ መግለጫ ሰጥተዋል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲማሩ ዝግጅት እየተደረገ ነው የሚሉት ኮሚሽነሩ፤ “በእጃችን በቂ መረጃ አለ። እነዚህ መረጃዎች ተገቢ ክትትል እየተደረገባቸው ነው የሚገኙት። መረጃዎች ልጆቹ ላይ ከቀላል እስከ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል እየተባለ በሚወራው ጉዳይ እስካሁን በፖሊስ የተረጋገጠ አይደለም። በጉዳዩ ላይ ምረመራ እየተካሄደ ስለሆነ ዝርዝር መረጃ መስጠት አልፈለግንም። ሦስት ቡደን አደራጅተን ምርመራዎችን እያካሄድ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

እስክንድር ነጋ የቡናና የጊዮርጊስ ጨዋታን በስታዲየም እንዳይመለከት ሲታገድ ፣ስንታየሁ ቸኮል ታሰረ

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር እስክንድር ነጋ በቡናና ቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች የጋራ ግብዣ የዛሬውን የደርቢ ጨዋታ እንዲከታተል ከሁለት ሳምንት በፊት በቀረበለት ግብዣ መሠረት ዛሬ ከቀኑ አስር ሰዐት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ቢገኝም ፖሊስ ጨዋታውን እንዳይከታተል የቆረጠውን የመግቢያ ትኬት ውድቅ በማድረግ ከበር ላይ መልሶታል::

ፍጹም ህገ ወጥ በሆነ መልኩ በስታዲየም የመገኘት መብትን የገፈፈው ፖሊስ ግን የባልደራሱን የሁለቱን ደጋፊዎች ግብዣ በመጥለፍ ለተራ የፖለቲካ ፕሮፐጋንዳ ለማዋል የአዲስ ቲቪና ራዲዮ ጋዜጠኞችን ይዘው የተገኙትን ከንቲባ ታከለ ኡማን በክብር እንዲገቡ አድርጓል::

በአዲስ አበባ የባለቤትነት ጉዳይ ሰፊ እንቅስቃሴ በመድረግ የፊንፊኔ ኬኛን ፖለቲካ ገደል እየከተተው የሚገኘው እስክንድር ነጋን በሁለቱ የመዲናዋ ክለቦች ጨዋታ ላይ መጋበዙ በእጅጉ ያስደነገጣቸው ታከለ ኡማ ጥቂት ለሆዳቸው ያደሩ የቡናና የጊዮርጊስ ደጋፊዎችና አስጨፋሪዎችን  እንዲሁም የክለብ ሓላፊዎችን ትናንት በቢሮአቸው በመጋበዝ ለክለቦቹ ስታዲየም የቦታ ባለቤትነት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታን አስረክበው በጨዋታው እለት በይፋ ለመታደም ማሰባቸውን በመግለፅ ዜናው በመንግስት የመገናኛ ብዙኃን አማካይነት እንዲሰራጭ ባደረጉት መሠረት ዛሬ በሰው ወይም በሌላ ሰው ግብዣ ላይ ድንኳን ሰባሪ ሆነው ተገኝተዋል::

ታከለ ኡማ አጀንዳ በመጥለፍ መገኘታቸው ብቻ ሳይሆን አስክንድር ነጋ በስታዲየም እንዳይገኝ በውስጥ ትእዛዝ መመሪያ መስጠታቸውና ትእዛዙም በተግባር ላይ መዋሉን ባመኑ በርካታ ሕዝብን አበሳጭቷል::

እንዴት ትኬት የቆረጠ ሰው ወደ ስታዲየም መግባት አይችልም? ፖሊስም እከሌ ግባ አትግባ በሚል መከልከል ይችላል ወይ በሚል የኢትዮጵያ ነገ የአዲስ አበባ ዘጋቢ ጥያቄ ያቀረበላቸው የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት በቂ ማብራሪያ መስጠት ባይችሉም “እኛ መንም ማድረግ አንችልም እስክንድር ነጋና አብረውት የሚመጡ ደጋፊዎቹ እንዳይገቡ ከበላይ አካል መመሪያ ተሰጥቶናል” በማለት ተናግረዋል። 

እነ እስክንድር በስታዲየሙ በር ላይ እንዳይገቡ በተከለከሉበት ወቅት የነበረውን እንቅስቃሴ በሞባይል ስልክህ ቀርጸሃል በሚል የባልደራሱ የሕዝብ ግንኙነት ስንታየሁ ቸኮል በጸጥታ አካላት ተይዞ ለእስር ተዳርጓል::በሰኔ ወር በባህርዳር በተከሰተው ችግር በሽብርተኝነት ተይዞ ለአራት ወራት በግፍ ታስሮ የነበረው እና በኋላ በቀበሌ መታወቂያ ዋስትና ብቻ እንዲወጣ የተደረገው ስንታየሁ ቸኮልን ፖሊሶቹ ፎቶ ስላነሳኸን እንከስሃለን በማለት ከፍተኛ ውዝግብ ሲፈጥሩም ተስተውሏል። 

በቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ለባዶ አሸናፊነት የተጠናቀቀው የቅዱስ ጊዮርጊስና የቡና ጨዋታ ከመከናወኑ በፊት ከምሳ ሰዐት ጀምሮ የሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች ከየአካባቢያቸው በጋራ በመሆን “እስክንድር ጀግና” “ባልደራስ የእኛ” የሚሉ ዝማሬዎችን በማስተጋባት ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም ሲያመሩ እንደነበር ተመልክቷል።  

የእስክንድር ነጋ ወደ ስታዲየሙ እንዳይገባ መከልከሉ ያበሳጫቸው የሁለቱም ክለብ ደጋፊዎች በጨዋታው መሀል ስሙን እየጠሩ በጨዋ ደንብ ሲያሞግሱት አምሽተዋል::

በእንግሊዙ የኦሮሞ ኮንፍረንስ “ኢትዮጵያ ትበታተንያሉት የኦብፓ አባል እንግሊዛዊ ሆነው ተገኙ

የመከላከያ ሠራዊትን ከድተው ኦነግን፣ ኦነግን ጥለው ወደ ኦዴፓ በመከረባበት፣ የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ቢሮ ሓላፊ በመሆን ተሹመው የነበሩት /ጄነራል ከማል ገልቹ በመሰረቱት ኦብፓ ፓርቲ ውስጥ በአባልነት የተመዘገቡ አንድ ሰው ዜግነታቸው እንግሊዛዊ መሆኑን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

በተጠቀሰው ፓርቲ ውስጥ በአባልነት የተመዘገቡት አቶ ሊበን ዋቆ ምርጫ ቦርድ በብ/ጀነራል ከማል ገልቹ ለሚመራው ፓርቲ በፃፈው ደብዳቤ ላይ ግለሰቡ ዜግነታቸው እንግሊዛዊ መሆኑ ስለተደረሰበት፤ ፓርቲው ይህንን አምኖ በመቀበል አቶ ሊበን ዋቆን ከፓርቲ አመራርነት በማንሳት በሌላ አመራር እንዲተካ አሳስቦ ነበር፡፡

ፓርቲውም ከምርጫ ቦርድ የተላለፈለትን ትዕዛዝ በመቀበል ግለሰቡን ከነበራቸው ሓላፊነት በማንሳት በሌላ ሰው ተክቷል፡ ፡ምርጫ ቦርድም ይህን ማረጋገጡ ታውቋል፡፡

እንግሊዛዊ ዜግነት የያዙት አቶ ሊበን ዋቆ፤ በቅርቡኦሮሞ ነፃ እንዲወጣ ከተፈለገ ኢትዮጵያ ትበታተን፡፡ ኢትዮጵያ የኦሮሞ ዕዳ ነች” የሚል መልዕክት ማስተላለፋቸው አይዘነጋም፡፡

የጃዋር ዜግነትን በተመለከተ እስከ ጥር 29 ኦፌኮ ምላሽእንዲሰጥ 2 ጊዜ ተጠየቀ

በቅርቡ በመረራ ጉዲና የሚመራው ኦፌኮ (ኦሮሞ ፌደራላዊኮንግረስ) ፓርቲን የተቀላቀለው የጃዋር መሐመድን ዜግነትበተመለከተ ፓርቲው በአስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ ምርጫ ቦርድ ለኹለተኛ ጊዜ ደብዳቤ እንደፃፈ ተሰማ፡፡

በወ/ ብርቱካን ሚዴቅሳ የሚመራው ምርጫ ቦርድ፤ አሜሪካዊ ዜግነት ይዞ በኢትዮጵያዊነት ኦፌኮን እንዲቀላቀል የተደረገውጃዋር መሐመድን በተመለከተ ለኦፌኮ በድጋሚ በፃፈው ደብዳቤ እስከ ጥር 29 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ፣ የጃዋር መሀመድን የዜግነት ጉዳይ ኢትዮጵያ ለመሆኑ በማስረጃ ካላቀረበ እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል፡፡

ኦፌኮ በበኩሉ በህጉ መሠረት ከአባልነት እንሰርዘዋለን እያለ ነው፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ ቪኦኤ ጃዋርን ለማነጋገር ጥረት ቢያደርግም ጃዋር መሀመድ ግንበዚህ ጉዳይ ላይ ለቪኦኤ አማርኛ ኢንተርቪው አላደርግምሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ጃዋር በቅርቡ የእርሱን ሃሳብ በማስተጋባት በሚታወቀው ኤልቲቪ ከቤተልሄም ታፈሰ ጋር ባደረገው ቆይታ፣ ዜግነቱን በተመለከተ ለቀረበለት ጥያቄየዜግነቴ ጉዳይ በዚህ ሳምንት ውስጥ የሚያልቅ ነውየሚል ምላሽ መስጠቱ አይዘነጋም፡፡

በሶማሌ ክልል ህገ ወጥ መሣሪያ ሲያዘዋውር የነበሩ ተያዙ

በሶማሌ ክልል ውስጥ ህገ ወጥ የጦር መሳሪ ሲያዘዋውሩ የነበሩተጠርጣሪዎች ማክሰኞ ጥር 19 ቀን በቁጥጥር ሥር መዋላቸውተሰማ፡፡ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ከጅግጅጋ ከተማ በቅርብ ርቀትላይ በሚገኘው መጋሎ ቃረን መቆጣጠሪያ ጣቢያ ባደረገውድንገተኛ ፍተሻ በቶጎ ውጫሌ ድንበር በኩል በህገወጥ መንገድበተሽከርካሪ ተደብቆ ሊገባ የነበረ 39 ሽጉጥ ከተጠርጣሪዎቹ ጋርመያዙ ተገልጿል፡፡ ህገወጥ መሳሪያውን ይዘው የነበሩት ሦስትተጠርጣሪዎች እና አንድ ተሽከርካሪ መያዙንም የክልሉ ልዩ ኃይልአረጋግጧል፡፡

በአየር መንገድ ግቢ ታፍ ኦይልየአውሮፕላን ነዳጅ ማከማቻ ተገንብቶ ሥራ ጀመረ

በአገራችን ትልቁ አውሮፕላን ነዳጅ ማከማቺያ ዴፖ 2 ዓመታት የሥራ እና የግንባታ ግዜያትን ፈጅቶ በያዝነው ሳምንት የኢፌድሪ ትራንስፖርት ሚኒስትር ሚኒስትር ዴታ / ሙሉ /እግዚአብሔር እንዲሁም የኢፌድሪ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተካ ገብረ የሱስ እና የታፍ ኦይል ፕሬዚዳንትና ሌሎች አካላት በተገኙበት  በኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ጉምሩክ ግቢ ውስጥ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡

በዕለቱ የታፍ ኦይል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ትንሳኤ አክሊሉ እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ “450 ሚሊየን ብር ካፒታል ተገንብቶ 350 በላይ ቋሚ እና ግዜያዊ የሥራ ዕድል የፈጠረ፣ 6 ሚሊየን ሊትር ነዳጅ የመያዝ አቅም ያለው፣ ሁሉንም ዘመናዊ የጥራት መለኪያ መንገዶችን ያሟላ ዴፖ ገንብተን እነሆ በሥራ ላይ እንዲውል አድርገናልብለዋል፡፡ ዘመናዊ የሆኑ ከዴፖው ወደ አውሮፕላኑ የሚያመላልሱ እያንዳንዳቸው 20 ሚሊየን ብር የተገዙ ሪፊዩለሮች የዚህ ሥራ አካል መሆናቸውም በምረቃ ሥነሥርዓቱ ላይ ተገልጹዋል፡፡ ታፍ ኦይል ባለፉት 45 ዓመታት 74 ነዳጅ ማድያዎችን በመላው ኢትዮጵያ እያስተዳደረ ሲሆን፤ በቀጣይም 31 የነዳጅ ማደያዎች ወደ ሥራ እንደሚገቡና ቁጥሩም 105 እንደሚደርስ አቶ ትንሳኤ አክሊሉ ተናግረዋል፡፡

ኢየሩሳሌም የማትከፋፈል የእስራኤል ዋና ከተማ መሆኗንዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ

አወዛጋቢው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰላምስለራቀው መካካለኛው ምስራቅ እፁብ ድንቅ የሆነ እቅድ ይዣለሁ ሲሉ በከረሙት መሰረት፤የዘመኑ ታላቅ የሰላም እቅድያሉትን ሀሳብ ማክሰኞ ምሽት በቤንጃሚን ናታንያሁ ታጅበው ይፋ አድርገዋል፡፡

ትራምፕ ባደረጉት ንግግር ላይ፤ የፍልስጤሙ መሪ መሀመድ አባሽ በጭራሽ በቦታው አልነበሩም፡፡ በተጨማሪም ፍልስጤማውያኑን የሚወክል አካልም በቦታው አልተገኘም፡፡ የኦማንና የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ተወካዮች በታዛቢነት ተገኝተው ሊሆን ይችላል እየተባለ ነው፡፡

በርካቶች ለእስራኤል ያደላ ነው ያሉት ይህየክፍለ ዘመኑ የሰላም እቅድየዓለምን ትኩረት ስቦ አምሽቷል፡፡ የዶናልድ እቅድ ነፃ የፍልስጤምን አገርን የሚፈቅድ ቢሆንም፣ ለእስራኤል ህገ ወጥ ይዞታዎች በስፋት እውቅና የሚሰጥ ሆኗል፡፡ይህ እኔ ያመጣሁት እቅድ ካልሠራ ሌላ ምንም ነገር ሊሠራ አይችልምሲሉ ትራምፕም ተናግረዋል፡፡

በአንፃሩ የፍስልጤሙ ፕሬዝዳንት መሐመድ አባስአሻጥር ነውሲሉ የሰላም ሰነዱን ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርገውታል፡፡ የሰነዱንይፋ መሆን ተከትሎ ፕሬዚዳንት አባስ በራማላህ ባደረጉት ንግግር ለትራምፕና ናታንያሁ የምለው አለኝ፤ ኢየሩሳሌም ለገበያ አትቀርብም፤ መብቶቻችን ለሽያጭ አይቀርቡምብለዋል፡፡

ትራምፕ በምጣኔ ሐብት ለተንኮታከተችው ፍልስጤም፤ በታሪኳ አይታም ሰምታም የማታውቀው የኢንቨስትመንት ገንዘብ እንሰጣታለን ማለታቸውን ተከትሎ ነው መሐመድ አባስ ከላይ የሰፈረውን ሀሳብ የሰነዘሩት፡፡ አሜሪካ ፍልስጤም ሀሳቡን (ዕቅዱን) ከተቀበለች 50 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ይሰጣታል ነው የተባለው፡፡

የክፍለ ዘመኑ የሰላም ሰነድ ዶናልድ ትራምፕ በበላይነት ሲያረቁ ከነበሩት ሰዎች መሀል የትራምፕ ሴት ልጅ ኢቫንካ ትራምፕ ባል ጄርድ ኩሽነር ግንባር ቀደሙ ነበር፡፡ የሰላም ሰነዱ ይፋ መሆንን ተከትሎ በበርካታ የአረብ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ  የተካሄደ ሲሆን በጋዛ ሰርጥ ፍልስጤማውን የትራምፕ ምስል ሲያቃጥሉ ውለዋል፡፡

LEAVE A REPLY