ሁሉም ቢተባበር የት ይድረስ ነበር….?! | ታምሩ ገዳ

ሁሉም ቢተባበር የት ይድረስ ነበር….?! | ታምሩ ገዳ

አንዳንድ ጊዜ እኛ እጅግ አደግን፣ ተመነጠቅን ምድሩቱንም እንደ አሻን እንገዛታለን የምንል የሰው ልጆች እርስ በራሳችን ለመጨራረስ ስንሯሯጥ ፣እንዱን ለማጥፋት ጉድጓድ ስንምስ፣ ዘር፣ ብሔር፣ሀይማኖት እና ጾታ ለይተን የእኛኑ ወገንን ስናፍን፣ ስናሳፍን፣ ጭንቀት እና ሽብርን ስናበራክት፣ በተቃራኒው በቤታችን ይሁን በዱር የሚገኙ እንስሳት በደመ ነፍስ ተመርተው ከእኛ በእጅጉ የተሻለ፣ የሚያስገርም፣ ሁላችንም ቆም ብለን እንድናስብ የሚያደርግ እና ልብን የሚነካ ተግባራትን ሲከውኑ የስተዋላሉ።

. ቤሪአን፣ በኢንዶኔዢያ ውስጥ የሚገኝ ዝርያቸው እየተመናመነ የሚገኙ ስድስት መቶ ሀያ ዝንጀሮዎች በእንክብካቤ ተጠብቀው የሚኖሩበት ማእከል (foundation) ሲሆን በምስል ላይ የሚታየው ሰውም ጥብቅ ማእከሉን በእየእለቱ እንዲንከባከቡ ኃላፊነት ከተሰጣቸው አራት መቶ ስራተኞች መካከል አንዱ ሲሆን ሰሞኑን አራዊቱን ሆነ የሰው ልጆችን ሊተናኮል የሚችል ገዳይ እባብ አለ መባሉን ተከትሎ እባቡን እንዲያስወግድ ትእዛዝ ተሰጥቶት በወንዙ ውስጥ በስራ ገበታው ላይ ይገኛል።

ይህ እኤአ 1991 ተቋቁሞ ለጎብኝዎች ክፍት በሆነው ጥብቅ የእንሰሳት ማቆያ ማእከል ውስጥ ከጓደኞቹ ጋር በመጎብኘት ላይ የነበረው አኒል ፓራባከር የተባለ አማተር ፎቶግራፈር በምስል የሚታየው የአራዊቱ ማእከል ሰራተኛ በጭቃ መዋጡን የተመለከው ዝንጀሮ (ኦራንጉታ) “ምንም እንኳን በዘር፣ በሀይማኖት፣ በደም፣ በቋንቋ ባንዛመድም እኔን እና መስል ጓደኞቼን ከአጢቂዎቻችን የምትታደገን ልዩ ፍጡር መሆንህን በደመ ነፍስ አውቃለሁ” በሚል እሳቤ ዝንጆሮው ለአለቃው (የሰው ልጅ) የብዙዎችን ልብ የሚነካ የእርዳታ እጆቹን ሲዘረጋለት የተመለከተው ፎተግራፈሩ አኒል ከመ ቅጽበት አጋጣሚውን በካሜራው ለመቅረጽ ችሏል።

አጋጣሚውንም በርካታ አለማቀፋዊ ሚዲያዎች ሰሞነን “አጃይብ” ነው ብለውታል። እዚህ ላይ የሚገርመው ነገር ቢኖር ለአራዊቱ ሆነ ለስው ልጆች ጠንቅ የሆነው እባብን ለማስወገድ ከወገቡ በታች በጭቃ የተዋጠው የማእከሉ ሰራተኛ(የሰው ልጅ) ከዝንጀሮው የቀረበለትን የእርዳታ እጅን ያለመቀበሉ ጉዳይ ሲሆን ከፎቶ አንሺው እንል ለምን እምቢ አለክ የሚል ጥያቄ ብጤ ቀርቦለት ምላሹም “እርሱ እኮ ያው የዱር አውሬ ነው” የሚል ነበር።

በማእከሉ ድህረገጽ ላይ የሚገኘው አጭር መልእክት በበኩሉ “እዚህ የሚገኙት በተፈጥሯቸው ለሰው ልጆች በጣም ቅርበት ያላቸው ዝንጀሮዎች (ኦራንጉታዎች) በአስተሳስባቸው ምጡቅ፣ በተፈጥሯቸው ልዩ ሲሆኑ እነርሱን መርዳት ማለት እኛ የሰው ልጆችን፣ እጽዎቶችን እና እንሰሳቶችን መንከባባከብ ማለት ነው” ይላል።

LEAVE A REPLY