ህወሓት ከኤርትራ ጋር የመደራደር ፍላጎት እንዳለው ዶ/ር ደብረፂዮን አሳወቁ

ህወሓት ከኤርትራ ጋር የመደራደር ፍላጎት እንዳለው ዶ/ር ደብረፂዮን አሳወቁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የትግራይ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ያለው የድንበር ችግር በዘላቂነት መፍትሔ ሊያገኝ የሚችለው መሪዎች ተገናኝተን፣ በህግና በስርአት ተቋማዊ በሆነ መልኩ መፍትኄ ስናበጅለት ነው በማለት ተናገሩ::

ህወሓት የትጥቅ ትግል የጀመረበትን 45ኛ አመት ምክንያት በማድረግ “መቐሌ ትግራይ” ከተሰኘ የድረ ገጽ ጋዜጣ ጋር ሰሞኑን ልዩ ቃለ ምልልስ ያደረጉት ዶ/ር ደብረ ፂዮን፤ በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የድንበር ችግር በተፈለገው ፍጥነት መፍትሔ ያላገኘው መሪዎች ተገናኝተን፣ ባለመወያየታችንና በህግና ሥርዓት ጉዳዩን ለመቋጨት ባለመቻላችን ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የድንበሩን ጉዳይ እልባት ለማበጀት የኛ የመሪዎች ተገናኝቶ መነጋገር አስፈላጊ ነው ያሉት ዶ/ር ደብረፂዮን ከፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ አመራር ጋር ውይይት የማድረግ ፍላጐት በህወሓትም ሆነ በእርሳቸው ዘንድ መኖሩን ጠቁመዋል፡፡ “በሁለቱ አገሮች መካከል የነበረውን ሰላም ያደናቀፈው ህዝብ ሳይሆን መንግሥታት ናቸው፤ ህዝብ ሁሌም ሰላም ፈላጊ ነው፤ ችግር ያለው መሪዎች ጋ ነው” ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

በጦርነት መፍትሄ የሚያገኝ ጉዳይ እንደሌለ የተናገሩት ዶ/ር ደብረፂዮን “በሁለቱ አገራት የተጀመረው ሰላም ዘላቂ ሆኖ ዝምድናችን ወደ መደበኛነት እንዲሸጋገር በመጀመሪያ ያልተቋጩ የድንበር ጉዳዮች በህግና በሥርዓት፣ ተቋማዊ በሆነ መልኩ እንዲቋጩ ያስፈልጋል” ካሉ በኋላ ከአገረ ኤርትራ መሪዎች ጋር የመገናኘት ፍላጐት እንዳላቸውና አሁን ችግር የሆነው መገናኘቱ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ፤ ሰሞኑን በኤርትራ  የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ በባድመና አካባቢው ጉዳዩ በሠላም እንዳይፈታ የህወሓት አመራሮችና ጥቂት የውጭ ሃይሎች እንቅፋት መሆናቸውን በመግለጽ፣ በኢትዮጵያ ያለው የብሔር ፌደራሊዝምን ተገን በማድረግ ህወሓት ጉዳዩን እድሜ መግዣ እያደረገው ነው ሲሉ መቀሌ የመሸገውን ቡድን ሴራ መከሰሳቸው ይታወሳል፡፡

LEAVE A REPLY