በቻይና ያሉ 311 ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ከኮሮና ቫይረስ ነፃ ናቸው ተባ

በቻይና ያሉ 311 ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ከኮሮና ቫይረስ ነፃ ናቸው ተባ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በቻይና ሁቤይ ግዛት በሚገኙ 24 ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ 311 ኢትዮጵያውያን እስካሁን ድረስ በኮሮና ቫይረስ እንዳልተጠቁ ተነገረ።

በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ባወጣው መረጃ በውሃን እና ሌሎች ከተሞች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች በቫይረሱ እንዳልተጠቁ ጠቁሟል ።

ኤምባሲው ለእረፍት በኢትዮጵያ የሚገኙ በቻይና የሚማሩ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲያቸው ጋር ግንኙነታቸውን እንዲቀጥሉም ነው የመከረው።

ይህ ይሁን እንጂ ተጨማሪ መረጃ ይፋ እስከሚሆን ድረስ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዎቻቸው እንዳይመለሱ ያሳሰበው በቻይና የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ፤ በአገሪቱ ለሚገኙ ተማሪዎች ከቫይረሱ ራሳቸውን መከላከል እንዲችሉ የማስክ እና ሌሎች ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑንም ገልጿል።

LEAVE A REPLY