ኤርሚያስ አመልጋ፣ ክርስቲያን ታደለና ኮ/ል ቢንያምን ጨምሮ 63 ሰዎች ክሳቸው ተቋረጠ

ኤርሚያስ አመልጋ፣ ክርስቲያን ታደለና ኮ/ል ቢንያምን ጨምሮ 63 ሰዎች ክሳቸው ተቋረጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው በእስር ላይ ከሚገኙ ሰዎች መካከል ሥድሳ  ሦስቱ የተመሰረተባቸው ክስ እንዲቋረጥና ከእስር እንዲፈቱ መወሰኑን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ።

የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሓላፊዎች የሆኑት አቶ ፍቃዱ ፀጋና አቶ ዝናቡ ቱኑ  ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት እንዲለቀቁ ከተወሰነላቸው መካከል በሙስናና በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የተከሰሱ፣ ነገር ግን በአመራር ቦታዎች ላይ ያልነበሩ ሰዎች ናቸው።

በተጨማሪም በአዲስ አበባና በባሕር ዳር ከተሞች በሰኔ 15/2011 ዓ.ም ከተፈጸመው ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ግድያ፤ እንዲሁም በሶማሌ፣ በሲዳማና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ውስጥ ካጋጠሙ ግጭቶች ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎችም ይገኙበታል መባሉን ሰምተናል።

በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፌስቡክ ገጽ ላይ ክሳቸው እንዲቋረጥ የተደረጉ ግለሰቦች ስም ዝርዝር ይፋ የተደረገ ሲሆን፤ ሌተናንት ኮሎኔል ቢንያም ተወልደ፣ አቶ ኤርሚያስ አመልጋ እና አቶ ክርስቲያን ታደለ ይገኙበታል። በተጨማሪም ሌተናንት ኮሎኔል ሰላም ይሁን፣ ሌተናንት ኮሎኔል ጸጋዬ አንሙት፣ ሌተናንት ኮሎኔል ለተብርሀን ደሞዝ፣ ኮለኔል ሸጋው ሙሉጌታ፣ ወ/ሮ ራህማ አህመድ እና ወ/ሮ ዘምዘም ሀሰን ክሳቸው እንዲቋረጥ ከተደረገው መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

ቀደም ሲል የመረጃ መረብ ደኅንነት ተቋም ከፍተኛ ሓላፊና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቅርብ ጓደኛ የነበሩት ሌተናንት ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ ጠበቃ አቶ ኃይለሥላሴ ገብረመድህን፣ ሌተናነት ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደን ጨምሮ ሌሎች የሜቴክ ተከሳሾች ክሳቸው ይቋረጣል የሚል መረጃ እንዳላቸው ትናንት ተናግረው እንደነበር ይታወሳል።

በተጨማሪም አዲሱ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀ መንበር አቶ በለጠ ሞላ ለቢቢሲ እንደገለጹት ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ መንግሥት በእስር ላይ ያሉ አባሎቻቸውን እንዲፈታ መነጋገራቸውን አመልክተው ነበር። የድርጅቱ አመራር ከሆኑት መካከል በእስር ላይ ሳሉ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት እና ክሳቸው ከተቋረጡት አንዱ የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ናቸው::

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በሰጠው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው በእስር ላይ የቆዩት ተጠርጣሪዎች ክሳቸው ተቋርጦ እንዲለቀቁ የተወሰነው “ምንም ስላላጠፉ እና ማስረጃ ስላልተገኘባቸው ሳይሆን የተወሰኑት የጤና ችግር ስላለባቸው ሌሎቹ ደግሞ የወንጀል ተሳትፏቸው አነስተኛ ስለሆነ ነው” ሲል ገልጿል።

በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እና ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት በእስር ላይ የሚገኙ የቀድሞ የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮችና የፖለቲካ መሪዎች ጉዳያቸው በሕግ አግባብ ታይቶ ክሳቸው እንደሚቋረጥ ፍንጭ ሰጥተው ነበር። ይህንንም በተመለከተ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ትናንት ምሽት ላይ ባወጣው መግለጫ የሕግ አግባብን ተከትሎ በእስር ላይ ያሉ 60 ሰዎች ክሳቸው ተቋርጦ እንደሚለቀቁ አመልክቶ ነበር።

ሙሉ ስም ዝርዝራቸው ፡ –

1. ሌ/ኮ/ ቢኒያም ተወልደ
2. ሌ/ኮ/ል ሰላይ ይሁን
3. ሌ/ኮ/ል ጸጋዬ አንሙት
4. ኮ/ል ሸጋው ሙሉጌታ
5. ኮ/ል ግርማ ማንዘርጊያ
6. ኮ/ል ዙፋን በርሄ
7. ኮ/ል አሰመረት ኪዳኔ
8. ሻ/ል ይኩኖአምላክ ተሰፋዬ
9. አቶ አለም ፍጹም
10. አቶ ሰለሞን አብርሃ
11. አቶ ሰመረ ኃይለ
12. አቶ ክፍላይ ንጉሴ
13. ሌ/ኮ/ል መንግስቱ ከበደ
14. ሌ/ኮ/ል እሥራኤል አሰፋው
15. ሌ/ኮ/ል ከተማ ከበደ
16. ሌ/ኮ/ል ለተብርሃን ደሞዝ
17. አቶ ኡስማን ከበደ
18. ሌ/ኮ/ል ዋቅቶላ አዲሱ
19. ሌ/ኮ/ል ታቦር ኢዶሳ
20. ሻ/ል ዩሐንስ ትኬሳ
21. ወ/ሮ ወላንሳ ገ/ኢየሱስ
22. ሻ/ቃ ረመዳን ለጋስ
23. አቶ ሙሉጌታ ሰይድ
24. አቶ ዋሴዕ ሳድቅ
25. አቶ ሲሳይ ደበሌ
26. አቶ አክሊሉ ግርማይ
27. ወ/ሮ ራህማ መሀመድ
28. ወ/ሮ ዘምዘም ሀሰን
29. ኮ/ር ፋሩቅ በድሪ
30. አቶ አሳጥረው ከበደ
31. አቶ ሲሳይ አልታሰብ
32. አቶ አበበ ፋንታ
33. አቶ አሰቻለዉ ወርቁ
34. አቶ ተሾመ መለሰ
35. አቶ አለምነህ ሙሉ
36. አቶ ከድር ሰይድ
37. አቶ አዲስ አማረ
38. አቶ አማረ ብሌ
39. አቶ ክርስቲያን ታደሰ
40. አቶ በለጠ ካሳ
41. አቶ ሚፍታህ ሸምሱ
42. ዶ/ር ማቴ ማንገሻ
43. አቶ ታሪኩ ለማ
44. አቶ ጌታሁን ዳጉይ
45. አቶ በላይ በልጉዳ
46. ሪ/ፓ/ር አመሉ ጣሚሶ
47. አቶ ተፈራ ቄንፈቶ
48. ረዳት ፕሮፈሰር ተሰማ ኤልያስ
49. አቶ አማኑኤል በላይነህ
50. አቶ አዲሱ ቃሚሶ
51. ሱ/ኢ/ አሰገል ወ/ጊዩርጊስ
52. ሱ/ኢ/ አሰፋ ኪዳኔ
53. ሱ/ኢ/ ገ/እግዚአብኤር ገ/ሃዋርያት
54. አቶ ግርማ አቡ
55. አቶ አብዱልሙኒየር አብዱልጀሊስ
56. አቶ ቶፊቅ አብዱልቃድር
57. አቶ ከማል መሃመድ
58. ኮ/ር ኡስማን አህመድ
59. ኮ/ር ኤዶሳ ጎሽ
60. አቶ ባበከር ከሊፋ
61. ዋ/ሳ/ እቴነሽ አርፋይኔ
62. አቶ ኤርሚያስ አመልጋ
63. አቶ ሙሉጌታ ሰይድ

LEAVE A REPLY