ከፕ/ት ትራምፕ ጋር ፎቶ የተነሱት ሹም የኮሮና ተጠቂ ሆኑ || ታምሩ ገዳ

ከፕ/ት ትራምፕ ጋር ፎቶ የተነሱት ሹም የኮሮና ተጠቂ ሆኑ || ታምሩ ገዳ

የብራዚሉ ፕ/ት ጃየር ቦልሳልኖሮ ባለፈው ሳምንት ወደ አሜሪካ ተጉዘው ከአሜሪካው አቻቸው ከፕ/ት ትራምፕ ጋር ሲወያዩ አብረዋቸው የነበሩት እና ከትራምፕ እና ከምክትላቸው ጋር የመታሰቢያ ፎቶ ግራፍም የተነሱት ብራዚላዊ ባለስልጣን በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ተነገረ።

በማራ አ ሎጎ በሚገኘው የፕሬዜዳንቱ የግል መዝናኛ ስፍራ ባለፈው ሳምንት በተካሄው የሁለቱ አገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ውይይት ላይ የተገኙት የብራዚሉ ፕ/ት የኮሙኒኬሽን ሹም የሆኑት ፋቢዮ ዋንግርትልን በአሜሪካ ቆይታቸው ከትራምፕ ጎን ቆመው ፎቶግራፍ የተሱ ሲሆን” ብራዚልን ዳግም ታላቅ አገር እናድርጋት/Make Brazil great again” የሚል ኮፍያ ያደረጉት ፋቢዮ ይህንኑ የመታሰቢያ ፎቶ ግራፍ በወዳጆች መረብ ኢንስትግራም ገጻቸው ላይ ለጥፈውት ይታያል።

ዛሬ ሐሙስ ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ ያደረጉት ፕ/ት ትራምፕ የብራዚሉ ባለስልጣን ምርመራ እንደተደረገላቸው ገልጸው”አልፈራም”ብለዋል።

ከዋይት ሀውስ ቤተመንግስታቸው የወጣው መግለጫ እንዳተተው ከሆነ “ፕ/ት ትራምፕ ሆኑ ምክትላቸው ማይክ ፔንስ ከብራዙሉ ባለስልጣን ጋር የተቀራረበ ንክኪ ባለማድረጋቸው፣የኮሮና በሽታ ምልክቶች ስላልታየባቸው በደመ ነፍስ ምርመራ አይደረግባቸውም” ሲል አቋሙን ገልጿል።

የብራዚል መንግስት በበኩሉ ፕ/ቱን እና በስራቸው ያሉትን ባለስልጣናት ጤንነትን ለመጠበቅ ተገቢው እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል ።የብራዚሉ ከፍተኛ ሹም ፋብዮ በኩላቸው እራሳቸውን ከማንኛውም ማህበራዊ ግንኙነት አግደው እንደሚገኙ ታውቋል።

እስከ አሁን ድረስ መድኃኒት አልባ በሆነው በኮሮና ቫይረስ እስከ አሁን ድረስ በአሜሪካ ውስጥ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዋች የተለከፉ ስሆን በብራዚል እንዲሁ ሀምሳ ሁለት ሰዎች መጠቃታቸውን አለማቀፉ የጤና ተቋም ገልጿል።

LEAVE A REPLY