ሳዑዲ አረቢያ የአመታዊውን ሃጂ ጉዞ እንዲዘገይ ጠየቀች

ሳዑዲ አረቢያ የአመታዊውን ሃጂ ጉዞ እንዲዘገይ ጠየቀች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሳዑዲ አረቢያ የእስልምና እምነት ተከታዮች አመታዊውን ሃጂ ጉዟቸውን እንዲያዘገዩት ጠየቀች። ሳዑዲ አረቢያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ቁርጡ እስኪታወቅ ድረስ የጉዞ ወኪሎች ትኬት መቁረጣቸውን ገታ እንዲያደርጉ አሳስባለች።

በየዓመቱ ሐምሌና ነሐሴ ወር ወደ መካና መዲና ከሁለት ሚሊየን በላይ ሙስሊሞች ይጓዛሉ።

ይህ ጉዞ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በሕይወት ዘመናቸው ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጡት ሃይማኖታዊ ጉዞ ነው።

በሳዑዲ እስካሁን ድረስ በኮቪድ-19 1,563 የተያዙ ሲሆን 10 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።

LEAVE A REPLY