በኒው ዮርክ የኮሮና ቫይረስ በነብር (እንስሳ)ላይ መገኘቱ ተገለጸ

በኒው ዮርክ የኮሮና ቫይረስ በነብር (እንስሳ)ላይ መገኘቱ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኮሮና ቫይረስ ልክፍት መሰራጨቱንና ማወዛገቡን ቀጥሏል። ዛሬ ደግሞ ከወደ ኒውዮርክ ከተማ ስጋትና ተስፋን የቀላቀለ ዜና ተሠምቷል። እስካሁን የነበረን መረጃ ቫይረሱ እንስሳትን እንደማያጠቃ ነበር።

በኒውዮርክ ብሮንክስ መካነ አራዊት ስድስት ነብሮችና አናብስት መታመማቸውን ተከትሎ በተደረገ ምርመራ ናዲያ የተባለች የአራት ዓመት ነብር ቫይረሱ ተገኝቶባት የመጀመሪያዋ እንሰሳ ሆና ተመዝግባለች።

ቫይረሱ ምልክት ካላሳየ አንድ አቃቤ አራዊት ሳይተላለፍባቸው እንዳልቀር ቢጠረጠርም ምን አልባት በአሜሪካ የቫይረሱ መነሻ አራዊቱ ሊሆኑ እንደሚችሉም እየተገመተ ይገኛል።

ቫይረሱ ከእንስሳት ወደ ሠው እንደማይተላለፍ መረጃዎች የሚያመለክቱ ቢሆንም የነናዲያ ጉዳይ ግን ነገሩ ተጨማሪ ምርምር የሚጠይቅ እንደሆነ አመላክቷል ።

አራዊቱ ጤንነታቸው አስጊ ባይሆንም እንስሳት ቫይረሱን ወደ ሰው የሚያስተላልፉ ከሆነ በሽታውን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት የሚያወሳስበው መሆኑ ስጋት ፈጥሯል። በሌላ በኩል ደግሞ መድኃኒት እና/ወይም ክትባት ለማግኘት ለሚደረገው ጥረት ትልቅ ተስፋ የሚጣልበት እንደሆነም የኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል።

LEAVE A REPLY