የፖፕ ንግሥቷ ቢዮንሴ ኮሮናን ለመከላከል 6 ሚሊዮን ዶላር ልትለግስ ነው  

የፖፕ ንግሥቷ ቢዮንሴ ኮሮናን ለመከላከል 6 ሚሊዮን ዶላር ልትለግስ ነው  

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ||  የፖፕ ሙዚቃ ንግሥቷ ቢዮንሴ ለኮሮና ቫይረስ መከላከል 6 ሚሊዮን ዶላር ልትለግስ እንደሆነ  እየወጡ ያሉ መረጃዎች ጠቁመዋል።

“ቢጉድ” በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የቢዮንሴ እርዳታ ድርጅት እንደገለፀው  ከሆነ ገንዘቡ በአሜሪካ ግዛቶች በማኅበረሰብ ደረጃ ለሚሠሩ ድርጅቶች የሚከፋፈል ነው።

አድናቂዎቿ ‘ክዊን ቢ’ እያሉ የሚጠሯት ቢዮንሴ ቫይረሱ ጥቁር አሜሪካዊያን ላይ እያደረሰ ያለው ተፅዕኖ እንደሚያሳስባት ገልጻለች:: “አብዛኛዎቹ ጥቁር አሜሪካውያን ከቤታቸው ሆነው የመሥራት አቅም የላቸውም። በዚያ ላይ አፍሪካ አሜሪካዊ ማኅበረሰቦች በቫይረሱ እጅጉን ተጎድተዋል”  በማለትም በኢንስታግራም ገጿ ላይ አስፍራለች።

በዓለም ዝናዋ የናኘው የፖፕ ሙዚቃ ንግሥቷ ቢዮንሴ “ቫይረሱ ጥቁሮችን በሚያሳስብ ሁኔታ እየጎዳ ነው። እባካችሁ ተጠንቀቁ። አንድ ቤተሰብ ነን። ታስፈልጉናላችሁ።” ስትልም ተማፅናለች::

LEAVE A REPLY