116 ሰዎች ተሰብስበው ሺሻ ሲያጨሱ በፖሊስ ተያዙ

116 ሰዎች ተሰብስበው ሺሻ ሲያጨሱ በፖሊስ ተያዙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || መንግሥት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የጣለውን ክልከላ በመጣስ በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ተሰብስበው ሺሻ ሲያጨሱ አገኘኋቸው ያላቸውን 116 ሰዎችን መያዙን የከተማው ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ቃል አቀባይ የሆኑት ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ ግለሰቦቹ ለጤና አደገኛ በሆነ ሁኔታ በአንድ ቦታ ላይ ተሰብስበው መገኘታቸውን አስታውሰው ፣ በሁለት ቀናት ውስጥ  ለተቋሙ በደረሰ ጥቆማ መሰረት ሰሜን ማዘጋጃ በሚባለው አካባቢ በተደረገ አሰሳ  ፤ በአንደኛው ቤት 81፣ በሌላኛው ቤት ደግሞ 35 ሰዎች በድምሩ 116 ሰዎች ተሰብስበው ሺሻ ሲያጨሱ መያዛቸውን አብራርተዋል።

የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ለመቆጣጠር መንግሥት በደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሰረት ተሰብስቦ ጫት መቃምና ሺሻ ማጨስ ከተከለከሉት ድርጊቶች መካከል ዋነኞቹ መሆናቸው ይታወቃል። በአዋጁ የተደነገጉ እገዳዎችን የጣሰ ማንኛውም ሰው እስከ ሦስት ዓመት በሚደርስ ቀላል እስር ወይም ከ1 ሺህ እስከ 2መቶ ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልበት መደንገጉም አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY